በተሽከርካሪ አካል ውስጥ ተደብቀው ወደ አዲስ አበባ የገቡ ከዘጠኝ ሺህ በላይ ጥይቶች ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ።
የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 B-13357 አ/አ የሆነ አይሱዙ ተሽከርካሪ በህገ ወጥ መንገድ ጥይቶችን ጭኖ ሲንቀሳቀስ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና የአ/አ ፖሊስ በጋራ ባደረጉት ክትትል በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 4 ልዩ ቦታው 18 ማዞሪያ መብራት ሀይል ቀለበት መንገድ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
በወቅቱ አራት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራ መሆኑን የገለፀው የአዲስ አበባ ፖሊስ በተሽከርካሪው ላይ በተደረገ ፍተሻ 8ሺህ 400 የክላሽን-ኮቭ ጠብመንጃ እና 998 የኢኮልፒ ሽጉጥ በአጠቃላይ 9ሺህ 398 ጥይቶች በጥይት ማሸጊያ ሳጥን እና በጨርቅ ተጠቅልለው እስኮርት (ቅያሪ) ጎማ ውስጥ እንዲሁም በተሽከርካሪው የፊተኛው ክፍል ተደብቀው ተይዘዋል፡፡
ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር በሃገር እና በህዝብ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ሁለንተናዊ ጉዳት ከግምት ውስጥ በማስገባት ህብረተሰቡ በዚህ እና በሌሎች ከፀጥታ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች የሚሰጠውን ጥቆማ አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን ማቅረቡን ኢዜአ ዘግብቧል
- ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር ውስጥ ናት፤ በጾሙ ማቅ ለብሰው በንስሃ ችግራቸውን ይፍቱየኢትዮጵያ ታሪክ ቁንጮ እንደሆነች የሚመሰከርላትና እጅግ ውብ ስብዕና ያላቸው አባቶች የሚጠቀሱላት ዕድሜ ጠገብቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር መተብተቧ… Read more: ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር ውስጥ ናት፤ በጾሙ ማቅ ለብሰው በንስሃ ችግራቸውን ይፍቱ
- ሕብረቱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ግዢ ሊያውል ነውየአውሮፓ ሕብረት በአባል ሀገራቱ እንዳይንቀሳቀሱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ዩክሬንን ጦር መሳሪያ ለማስታጠቅ ሊያውል መሆኑ ተሰምቷል፡፡ More stories በሕገ-ወጥ… Read more: ሕብረቱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ግዢ ሊያውል ነው
- ሳኡዲ የምታስገነባው አዲስ ከተማ – “ኒዮም ሲቲ” (Neom City)በረሃን ወደ ከተማነት የመቀየር ጥበብ ልንለው እንችላለን፡፡ ከ1 ትሪሊየን ዶላር በላይ የሚፈጅ ውድ ሥራም ነው፡፡ ከገንዘቡ ባሻገር ብዙ እውቀቶች ፈሰውበታል፤… Read more: ሳኡዲ የምታስገነባው አዲስ ከተማ – “ኒዮም ሲቲ” (Neom City)
- Ethiopia, Somalia dispute won’t transform into turmoil for the Horn of Africadeal between Ethiopia and Somaliland has sent waves of debates throughout the region, has even raised questions about the stability… Read more: Ethiopia, Somalia dispute won’t transform into turmoil for the Horn of Africa
- በአማራና ትግራይ ክልል ያሉ የወሰን ይገባኛል ጥያቄ በህዝብ ውሳኔ እንዲቋጭ ስምምነት ተደረሰትህነግ በበላይነት የሚመራው ኢህአዴግ ከፈርሰ በሁዋላ የተነሳውን ጦርነት ተከትሎ የአማራ ክልል ” ነጻ ወጡ” ባላቸው አካባቢዎች ለዓመታት የቆየ ውዝግብ ለአንዴና… Read more: በአማራና ትግራይ ክልል ያሉ የወሰን ይገባኛል ጥያቄ በህዝብ ውሳኔ እንዲቋጭ ስምምነት ተደረሰ