በተሽከርካሪ አካል ውስጥ ተደብቀው ወደ አዲስ አበባ የገቡ ከዘጠኝ ሺህ በላይ ጥይቶች ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ።
የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 B-13357 አ/አ የሆነ አይሱዙ ተሽከርካሪ በህገ ወጥ መንገድ ጥይቶችን ጭኖ ሲንቀሳቀስ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና የአ/አ ፖሊስ በጋራ ባደረጉት ክትትል በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 4 ልዩ ቦታው 18 ማዞሪያ መብራት ሀይል ቀለበት መንገድ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
በወቅቱ አራት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራ መሆኑን የገለፀው የአዲስ አበባ ፖሊስ በተሽከርካሪው ላይ በተደረገ ፍተሻ 8ሺህ 400 የክላሽን-ኮቭ ጠብመንጃ እና 998 የኢኮልፒ ሽጉጥ በአጠቃላይ 9ሺህ 398 ጥይቶች በጥይት ማሸጊያ ሳጥን እና በጨርቅ ተጠቅልለው እስኮርት (ቅያሪ) ጎማ ውስጥ እንዲሁም በተሽከርካሪው የፊተኛው ክፍል ተደብቀው ተይዘዋል፡፡
ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር በሃገር እና በህዝብ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ሁለንተናዊ ጉዳት ከግምት ውስጥ በማስገባት ህብረተሰቡ በዚህ እና በሌሎች ከፀጥታ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች የሚሰጠውን ጥቆማ አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን ማቅረቡን ኢዜአ ዘግብቧል
- የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ለትግራይ ሕዝብ ጥሪ አቀረበ፤ “አማራ ልዩነትህን ወደጎን አድርግ፤ዳግም በጅምላ አንቀበርም”“የትግል አደራ አይታጠፍም፤ ዳግም በጅምላ አንገደልም!” በሚል ርዕስ የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ባሰራጨው መግለጫ ትህነግን አስጠንቅቆ ”… Read more: የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ለትግራይ ሕዝብ ጥሪ አቀረበ፤ “አማራ ልዩነትህን ወደጎን አድርግ፤ዳግም በጅምላ አንቀበርም”
- በዝቋላ ገዳም የሆነው ይህ ነው!!More stories ዐቢይ አሕመድ ከትግራይ ህዝብ ተወካዮች ጋርApril 1, 2024 አብይ አህመድና ተቀናቃኝ ድርጅቶችApril 3, 2024 ካለፈ በሁዋላ … እንዳይቆጨን… Read more: በዝቋላ ገዳም የሆነው ይህ ነው!!
- Kenya’s military chief dies in a helicopter crash, Nairobi declares three days of national mourningKenya’s military chief Gen. Francis Ogolla died in a helicopter crash west of the country, President William Ruto announced Thursday… Read more: Kenya’s military chief dies in a helicopter crash, Nairobi declares three days of national mourning
- U.S. stops UN from recognizing a Palestinian state through membershipCGTN – The United States on Thursday stopped the UN from recognizing a Palestinian state by casting a veto in… Read more: U.S. stops UN from recognizing a Palestinian state through membership
- Israel launches missile attacks on Iran: reportCGTN – Israeli missiles have hit a site in Iran, ABC News reported late on Thursday, citing a U.S. official,… Read more: Israel launches missile attacks on Iran: report