ብ.ጄ ተፈራን ጭምሮ አምራ ክልል ለበርካታ ከፍተኛ መኮንኖች ሹመት ሰጠ – “ሲዋጉ ወታደሮች ሲገደሉ ሲቪሎች”

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር የክልሉን ሃይል ለማጠናከርና አደረጃጀቱን ብቁ ለማድረግ ልምድና ችሎታ ላላቸው ለተለያዩ ጄኔራሎችና ከፍተኛ የጦር መኮንኖች የሥራ ምደባና ሹመት ሰጥተዋል። በዚህም መሰረት፦

1ኛ. ብ/ጀ ተፈራ ማሞ የልዩ ሃይል አዛዥ፣

2ኛ. ብ/ጀ መሰለ በለጠ ም/አዛዥ ለኦፕሬሽናል፣

3ኛ.ኮሚ/ ቢሰጥ ጌታሁን ም/ አዛዥ ለኦፕሬሽን፣

4ኛ. ኮሚ/ አርአያ ካሴ ም/ አዛዥ ለኦፕሬሽናል፣

5ኛ. ጀኔራል ማሞ ግርማይ ም/ አዛዥ ለሎጀስቲክስ፣

6ኛ.ጀኔራል ዘዉዱ እሸቴ ም/አዛዥ ለሎጀስቲክስ፣

7ኛ. ጀኔራል አበራ ተ/ዮሃንስ ም/አዛዥ ለአስተዳደር፣

8ኛ. ረ/ ኮሚሽነር መለሰ ደገፋዉ ም/ አዛዥ ለአስተዳደር፣

9ኛ. ጀኔራል አዳምነህ መንግስቴ የሰላምና ደህንነት ቢሮ ሃላፊ ልዩ ረዳት ሆነው ተመድበዋል።

በሌላ ዜና

ሲዋጉወታደሮችሲገደሉሲቪሎች“….‼

አሸባሪው ህወሓት አስቀድሞ በመሪው ደብረጽዮን በኩል “ጦርነቱን ህዝባዊ እናደርጋለን፤ አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር ልዩ ሀይላችንን አንጠቀምም ከህጻን እስከ ሽማግሌ ያሉ አቅማቸው በፈቀደው ሁሉ በጦርነቱ ይሳተፋሉ” ማለቱ አይዘነጋም።

ባለፉት ወራት በህግ ማስከበር ዘመቻው የታየውም ይሄው ነው። አሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎቹን በሲቪል ልብስ ወደ ጦርነቱ አስገብቶ ሲያበቃ ሲገደሉበት ሲቪሎች ተገደሉብኝ በሚል ድረሱልኝ ይላል። እንደ ማርቲን ፕላውት ያሉ የድርጀቱ አክቲቪስቶችም ጩህቱን ተቀብለው ያስተጋባሉ።

በተቃራኒው መከላከያ ሰራዊት አካባቢውን ለቆ በወጣባቸው ከተሞች ጁንታው ሲገባ ደግሞ “ጀግና ወታደሮች” በሚል ከታች የቀረቡ ፎቶዎችን በመልቀቅ አየሩን ለመቆጣጠር፣ ደጋፊዎቹንም ለማስጨፈር ይሞክራል።

አንድ አንድ ምዕራባዊያን አገራትና ግለሰቦች ይህንን እውነታ ቢያውቁም አይተው እንዳላዩ ሰምተው እንዳልሰሙ ሆነዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከሰሞኑ በሰጡት መግለጫ፤ በብዙ ምክንያቶች ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ይህ ጦርነት እንዲቆም ይፈልጋል ወይ የሚል ጥያቄ እንድናነሳ እየተገደድን ነው ሲሉ መናገራቸውም አይዘነጋም።

አሸባሪው ህወሓት ሲዋጉ ጀግና ሲገደሉ ሲቪሎች የሚላቸው ታጣቂዎቹ ምስሎች ለአብነት ከማህበራዊ ሚዲያዎችና ከራሱ ከቡድኑ ደጋፊ ሚዲያዎች ተሰብስበው እንዲህ ቀርበዋል። Ena


Leave a Reply