“ክትባቱየ CIA ሴራ አለመሆኑንስ በምን እናዉቃለን?”

ለጥንቃቄ ያክል!

አሜሪካ የኢትዮጵያውያንን ምርጫ በማጣጣል በመዋጮ ስም ተላላኪ መንግስት በኢትዮጵያ ላይ ለመሾም ጡረተኛ ፖለቲከኞችን እያሰባሰበች ትገኛለች። የህዳሴ ግድብን እንዳንሞላ ከጠላቶቻችን ጋር ወግናለች! ኢትዮጵያን ማፍረስ ዋነኛ ዓላማዉ ያደረገዉን ጁንታ በሞራልና በማቴሪያል ደግፋለች። በኢትዮጵያ ውስጥ የወረዳና የቀበሌ ድንበሮችን ለመወሰን ከጅላለች! የኢትዮጵያ ህዝብ በዚሁ ምክንያት ቂም መያዙን ታዉቃለች። ቂሙን ለማረሳሳት ከትላንት ወድያ “የኮረና ክትባት ለኢትዮጵያ ሰጥቻለሁ” ብላ በሚዲያ እንዲወራላት ጠይቃለች። ትንሽ ነገር አድርጋ ብዙ አስወርታለች! “ኢትዮጵያውያን የመረጡትን ጠልቼ ኢትዮጵያዉያንን እወዳለሁ” ብላለች!

ጥያቄዎች ደግሞ አሉ። የኢትዮጵያዉያንን ምርጫና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የማያከብር ሀገር ለምን እርዳታ ይሰጠናል? እርዳታ መስጠቱስ በሚዲያ እንዲዘገብለት ለምን ይፈልጋል? ሚዲያችንስ እርዳታ መቀበላችንን እንደ ታላቅ ድል ለምን ይዘግባል? እኛስ ለምን ከጠላታችን እጅ እርዳታ እንቀበላለን? ክትባቱ ራሱ ኮረናን በኢትዮጵያ ለማስፋፋት የCIA ሴራ አለመሆኑንስ በምን እናዉቃለን? በኔ እምነት ከሞራልና ከጤና አኳያ ክትባቱን አለመቀበል ይበጀናል! በነፃነት መሞት ይሻላል!

Via Taye dendea Fb

Leave a Reply