በህገ ወጥ ንግድ ስራ ላይ በተሰማሩ ከ60 ሺህ በላይ ነጋዴዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ መዉሰዱን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ፡፡ቢሮዉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀዉ ባለፉት 10 ወራት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ በነበሩ 60 ሺህ 3 መቶ 45 ነጋዴዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ ወስጃለሁ ብሏል፡፡
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መስፍን አሰፋ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸዉ ቆይታ፣ የኑሮ ዉድነቱ አዲስ አበባ በሚሰሩ የንግዱ ማህበረሰብ ላይ ህጋዊ እርምጃዎች እየወሰድን ነዉ ብለዋል፡፡ለዋጋ ንረቱ መባባስ የህገ ወጥ ነጋዴዎች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ያነሱት አቶ መስፍን ፤በዚህም ከፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እስከ ማገድ ድረስ የሚደርስ እርምጃ ተወስዶባቸዋል ነዉ ያሉት፡፡
በዚህም 1 መቶ 9 ነጋዴዎች ታግደዋል፤ 2 መቶ 18 ክስ ተመስርቶባቸዋል፤ ከ19ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ታሽገዋል ተብሏል፡፡በተጨማሪም ከ39 ሺህ በላይ በሚሆኑት ላይ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸዉም ምክትል ሓላፊዉ ነግረዉናል፡፡ባጠቃላይ የኑሮ ዉድነቱ እንዲባባስና የዋጋ ንረቱ እንዲጨምር ሲያደርጉ በነበሩ 60 ሺህ 3 መቶ 45 ነጋዴዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ ተወስዷል፡፡
በአሁኑ ወቅት በከተመዋ የሚስተዋለዉን የኑሮ ዉድነት ለማረጋጋት ከሸማች ህብረት ስራዎች ጋራ በቅርበት እየተሰራ እንደሚገኝ የገለፁት አቶ መስፍን፣ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ለሸማች ማህበራት በማመቻቸት ወደ ስራ እንደገቡም ታወቋል፡፡ከዚህ በተጨማሪም እንደ አገር ከዉጭ በሚገቡ የዘይት፤ ስንዴ፤ ሩዝ፤ ስኳርና የሕጻናት ወተት ለ6 ወራት ከታክስ ነፃ እንዲገቡ ስለመደረጉም አቶ መስፍን አስታዉሰዋል፡፡
ከህገወጥ ነጋዴዎች በተጨማሪ የምርታማነት ችግርና ኮቪድ 19 ለኑሮ መወደድ የራሳቸዉ አስተዋፅኦ እንዳለቸዉ የተገለፀ ሲሆን፣ ህብረተሰቡ ከሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት እንዲጠቀሙ መክረዋል፡፡ቢሮዉ ከ1 መቶ ሺህ ኩንታል በላይ የጤፍ ምርት ለሸማች ማህበራት ማከፋፈሉን የተገለጸ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት መንግስት በድጎማ ከዉጭ ያስገባዉን የስንዴ ምርት ከሸማች ስራ ማህበራት በ 2ሺህ 5 መቶ 40 ብር ማግኘት እንደሚቻልም ኃላፊዉ ተናግረዋል፡፡
- የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ለትግራይ ሕዝብ ጥሪ አቀረበ፤ “አማራ ልዩነትህን ወደጎን አድርግ፤ዳግም በጅምላ አንቀበርም”“የትግል አደራ አይታጠፍም፤ ዳግም በጅምላ አንገደልም!” በሚል ርዕስ የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ባሰራጨው መግለጫ ትህነግን አስጠንቅቆ ” የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ ፍትሐዊ እና ሕጋዊ… Read more: የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ለትግራይ ሕዝብ ጥሪ አቀረበ፤ “አማራ ልዩነትህን ወደጎን አድርግ፤ዳግም በጅምላ አንቀበርም”
- በዝቋላ ገዳም የሆነው ይህ ነው!!More stories የባህር በር ህልውናችን!! አብይ አህመድ “መተንፈሻ ወደብ ያስፈልገናል” ሲሉ አወጁDecember 30, 2023 ዐቢይ አሕመድ ከትግራይ ህዝብ ተወካዮች ጋርApril 1, 2024 በዝቋላ ገዳም የሆነው ይህ ነው!!April 19,… Read more: በዝቋላ ገዳም የሆነው ይህ ነው!!
- Kenya’s military chief dies in a helicopter crash, Nairobi declares three days of national mourningKenya’s military chief Gen. Francis Ogolla died in a helicopter crash west of the country, President William Ruto announced Thursday and declared three days of national mourning. The… Read more: Kenya’s military chief dies in a helicopter crash, Nairobi declares three days of national mourning
- U.S. stops UN from recognizing a Palestinian state through membershipCGTN – The United States on Thursday stopped the UN from recognizing a Palestinian state by casting a veto in the Security Council to deny Palestinians full membership… Read more: U.S. stops UN from recognizing a Palestinian state through membership
- Israel launches missile attacks on Iran: reportCGTN – Israeli missiles have hit a site in Iran, ABC News reported late on Thursday, citing a U.S. official, while Iranian state media reported explosions, days after… Read more: Israel launches missile attacks on Iran: report