በህገ ወጥ ንግድ ስራ ላይ በተሰማሩ ከ60 ሺህ በላይ ነጋዴዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ መዉሰዱን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ፡፡ቢሮዉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀዉ ባለፉት 10 ወራት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ በነበሩ 60 ሺህ 3 መቶ 45 ነጋዴዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ ወስጃለሁ ብሏል፡፡
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መስፍን አሰፋ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸዉ ቆይታ፣ የኑሮ ዉድነቱ አዲስ አበባ በሚሰሩ የንግዱ ማህበረሰብ ላይ ህጋዊ እርምጃዎች እየወሰድን ነዉ ብለዋል፡፡ለዋጋ ንረቱ መባባስ የህገ ወጥ ነጋዴዎች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ያነሱት አቶ መስፍን ፤በዚህም ከፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እስከ ማገድ ድረስ የሚደርስ እርምጃ ተወስዶባቸዋል ነዉ ያሉት፡፡
በዚህም 1 መቶ 9 ነጋዴዎች ታግደዋል፤ 2 መቶ 18 ክስ ተመስርቶባቸዋል፤ ከ19ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ታሽገዋል ተብሏል፡፡በተጨማሪም ከ39 ሺህ በላይ በሚሆኑት ላይ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸዉም ምክትል ሓላፊዉ ነግረዉናል፡፡ባጠቃላይ የኑሮ ዉድነቱ እንዲባባስና የዋጋ ንረቱ እንዲጨምር ሲያደርጉ በነበሩ 60 ሺህ 3 መቶ 45 ነጋዴዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ ተወስዷል፡፡
በአሁኑ ወቅት በከተመዋ የሚስተዋለዉን የኑሮ ዉድነት ለማረጋጋት ከሸማች ህብረት ስራዎች ጋራ በቅርበት እየተሰራ እንደሚገኝ የገለፁት አቶ መስፍን፣ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ለሸማች ማህበራት በማመቻቸት ወደ ስራ እንደገቡም ታወቋል፡፡ከዚህ በተጨማሪም እንደ አገር ከዉጭ በሚገቡ የዘይት፤ ስንዴ፤ ሩዝ፤ ስኳርና የሕጻናት ወተት ለ6 ወራት ከታክስ ነፃ እንዲገቡ ስለመደረጉም አቶ መስፍን አስታዉሰዋል፡፡
ከህገወጥ ነጋዴዎች በተጨማሪ የምርታማነት ችግርና ኮቪድ 19 ለኑሮ መወደድ የራሳቸዉ አስተዋፅኦ እንዳለቸዉ የተገለፀ ሲሆን፣ ህብረተሰቡ ከሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት እንዲጠቀሙ መክረዋል፡፡ቢሮዉ ከ1 መቶ ሺህ ኩንታል በላይ የጤፍ ምርት ለሸማች ማህበራት ማከፋፈሉን የተገለጸ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት መንግስት በድጎማ ከዉጭ ያስገባዉን የስንዴ ምርት ከሸማች ስራ ማህበራት በ 2ሺህ 5 መቶ 40 ብር ማግኘት እንደሚቻልም ኃላፊዉ ተናግረዋል፡፡
- ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር ውስጥ ናት፤ በጾሙ ማቅ ለብሰው በንስሃ ችግራቸውን ይፍቱየኢትዮጵያ ታሪክ ቁንጮ እንደሆነች የሚመሰከርላትና እጅግ ውብ ስብዕና ያላቸው አባቶች የሚጠቀሱላት ዕድሜ ጠገብቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር መተብተቧ እየተጠቆመ ነው። በተጀመረው የአብይ ጾም ማቅ ለብሰውና አመድ… Read more: ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር ውስጥ ናት፤ በጾሙ ማቅ ለብሰው በንስሃ ችግራቸውን ይፍቱ
- ሕብረቱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ግዢ ሊያውል ነውየአውሮፓ ሕብረት በአባል ሀገራቱ እንዳይንቀሳቀሱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ዩክሬንን ጦር መሳሪያ ለማስታጠቅ ሊያውል መሆኑ ተሰምቷል፡፡ More stories ትህነግ እየተቃረመ ነው – ውጊያ የለምJune 19, 2021 የስንዴ… Read more: ሕብረቱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ግዢ ሊያውል ነው
- ሳኡዲ የምታስገነባው አዲስ ከተማ – “ኒዮም ሲቲ” (Neom City)በረሃን ወደ ከተማነት የመቀየር ጥበብ ልንለው እንችላለን፡፡ ከ1 ትሪሊየን ዶላር በላይ የሚፈጅ ውድ ሥራም ነው፡፡ ከገንዘቡ ባሻገር ብዙ እውቀቶች ፈሰውበታል፤ አዳዲስ ነገሮች ተዋውቀውበታል፡፡ ዓለምን እጅ በአፍ አስጭኗል…. “ኒዮም… Read more: ሳኡዲ የምታስገነባው አዲስ ከተማ – “ኒዮም ሲቲ” (Neom City)
- Ethiopia, Somalia dispute won’t transform into turmoil for the Horn of Africadeal between Ethiopia and Somaliland has sent waves of debates throughout the region, has even raised questions about the stability of the Horn of Africa and resulted in… Read more: Ethiopia, Somalia dispute won’t transform into turmoil for the Horn of Africa
- በአማራና ትግራይ ክልል ያሉ የወሰን ይገባኛል ጥያቄ በህዝብ ውሳኔ እንዲቋጭ ስምምነት ተደረሰትህነግ በበላይነት የሚመራው ኢህአዴግ ከፈርሰ በሁዋላ የተነሳውን ጦርነት ተከትሎ የአማራ ክልል ” ነጻ ወጡ” ባላቸው አካባቢዎች ለዓመታት የቆየ ውዝግብ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመቋጨት ህገመንግስቱ በሚያዘው መሰረት በህዝበ ውሳኔ… Read more: በአማራና ትግራይ ክልል ያሉ የወሰን ይገባኛል ጥያቄ በህዝብ ውሳኔ እንዲቋጭ ስምምነት ተደረሰ