የዓለም ምግብ ፕሮግራም ከአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም ዓቀፍ አየር ማረፊያ ወደ መቐለ 2ኛውን በረራ አደረገ። ሁለት ሰዎች ያልተፈቀደ የመድሃኒት ስንቅ ይዘዋል በሚል በፍተሻ ተረጋግጦ ከጉዞ መቀነሳቸው ተሰማ።
የኢትዮጵያ መንግስት የተናጠል ተኩስ አቁም ካወጀ ወዲህ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ 2ኛውን የአውሮፕላን በረራ እንደሚያደርግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጠቅሶ ፋና ዘግቦ ነበር።
በዚህ በ2ኛው የዓለም ምግብ ፕሮግራም በረራ ከ30 በላይ የሚሆኑ ግለሰቦች እና የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ሰራተኞች እንደተካተቱም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።
ይህ ዜና ከተላለፈ በሁዋላ በረራው ከመካሄዱ በፊት በተደረገ ፍተሻ ሁለት የእርዳታ ድጋፍ ሰጪ ናቸው የተባሉ ሰዎች ያልተፈቀደ መድሃኒት ጭነው በመያዛቸው ከበረራ መታገዳቸው ታውቋል።
ግዕዝ ሚዲያ ታማኝ የሚላቸውን የመረጃ ሰዎች ተቅሶ እንዳለው የተገኘው መድሃኒት ቢሆንም ተጨማሪ የተከለክሉና ከዕርዳታ ተግባሩ ጋር የማይገናኝ ቁሳቁስ መያዙ ተሰምቷል። ይህን አስመልክቶ መንግስት እስካሁን በይፋ ያለው ነገር የለም። ይሁን እንጂ በዕርዳታ ስም የማስታጠቅና የ1977ቱን ድርጊት የመድገም ሙከራዎች መያዙን ማስታወቁ አይዘነጋም።
- ቀሲስ በላይ ከ 6.5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ወንጀል ታስረው ፍርድ ቤት ቀረቡMore stories “ ምርጫ ውስጥ ለመሳተፍ እየተቸገርን ነው” ኦፌኮFebruary 4, 2021 የሞተር አሽከርካሪዎች ተሳፋሪ እንዳይጭኑ እገዳ ተጣለ- ከ6 ሺህ ሊትር በላይ ሕገወጥ ናፍጣ በቁጥጥር ስር ዋለApril 14,… Read more: ቀሲስ በላይ ከ 6.5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ወንጀል ታስረው ፍርድ ቤት ቀረቡ
- “ንገሩዋቸው፣ ምከሩዋቸው” ሌላ ጦርነት እብደትሰሞኑንን ለይቶለት ይፋ ሆነ እንጂ ውስጥ ውስጡን የጦርነት እንቅስቃሴ ሲደረግ እንደነበር መረጃዎች ከበቂ በላይ ነበሩ። ለዚህም ይመስላል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ” ንገሩዋቸው፣ ምክሩዋቸው” ሲሉ ከትግራይ ህዝብ ተወክለው… Read more: “ንገሩዋቸው፣ ምከሩዋቸው” ሌላ ጦርነት እብደት
- የባህር ወንበዴ ሲሳዮች – በገሃነም የሚመሰለው ስቃይየ34 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ ከአውሮፕላኑ ሲወርድ እግሮቹ ቆስለው መራመድም ሆነ መቆም አቅተውታል። ብርክ ይዞት ይንገዳገዳል፡፡ ይህ ሰው የተሻለ ህይወት ይኖረናል ብለው በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ሳኡዲ ዓረቢያ በባህር… Read more: የባህር ወንበዴ ሲሳዮች – በገሃነም የሚመሰለው ስቃይ
- ትህነግ ለአራተኛ ጊዜ የአማራ ህዝብ ላይ ወረራ በመፈጸሙ አማራ ክልል ህዝቡን ለመከላከል እንደሚገደድ አስታወቀ፤ ፌደራል መንግስት ጥያቄ ቀርቦለታል“ህወሓትና የግብረ አበሮቹ ፖለቲካዊ ግልሙትና እና ደም አፋሳሽ ጦርነት ለማድረግ ከመሞከር እንዲታቀቡ ይገባል” ሲል አማራ ክልል አሳሰበ። ስም ጠቅሶ ለአራተኛ ጊዜ ወረር የተፈጸመባቸውን ስፍራዎች አስታወቀ። መላው የኢትዮጵያ… Read more: ትህነግ ለአራተኛ ጊዜ የአማራ ህዝብ ላይ ወረራ በመፈጸሙ አማራ ክልል ህዝቡን ለመከላከል እንደሚገደድ አስታወቀ፤ ፌደራል መንግስት ጥያቄ ቀርቦለታል
- የራያ አላማጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞላ ደርበው ሲገደሉ ሌሎች ሃላፊዎች ሸሽተዋል፣ ግድያውን ማን ፈጸመው?የራያ አላማጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞላ ደርበው መገደላቸውን እና ሌሎች የወረዳው እና የከተማዋ ኃላፊዎች አካባቢውን ለቅቀው ወደ ሌሎች የራያ ወረዳዎች መሸሻቸው ተሰማ። ገዳያቸውን ለመግለጽ ፈቃደኛ እንዳልሆኑ… Read more: የራያ አላማጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞላ ደርበው ሲገደሉ ሌሎች ሃላፊዎች ሸሽተዋል፣ ግድያውን ማን ፈጸመው?