የዓለም ምግብ ፕሮግራም ከአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም ዓቀፍ አየር ማረፊያ ወደ መቐለ 2ኛውን በረራ አደረገ። ሁለት ሰዎች ያልተፈቀደ የመድሃኒት ስንቅ ይዘዋል በሚል በፍተሻ ተረጋግጦ ከጉዞ መቀነሳቸው ተሰማ።
የኢትዮጵያ መንግስት የተናጠል ተኩስ አቁም ካወጀ ወዲህ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ 2ኛውን የአውሮፕላን በረራ እንደሚያደርግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጠቅሶ ፋና ዘግቦ ነበር።
በዚህ በ2ኛው የዓለም ምግብ ፕሮግራም በረራ ከ30 በላይ የሚሆኑ ግለሰቦች እና የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ሰራተኞች እንደተካተቱም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።
ይህ ዜና ከተላለፈ በሁዋላ በረራው ከመካሄዱ በፊት በተደረገ ፍተሻ ሁለት የእርዳታ ድጋፍ ሰጪ ናቸው የተባሉ ሰዎች ያልተፈቀደ መድሃኒት ጭነው በመያዛቸው ከበረራ መታገዳቸው ታውቋል።
ግዕዝ ሚዲያ ታማኝ የሚላቸውን የመረጃ ሰዎች ተቅሶ እንዳለው የተገኘው መድሃኒት ቢሆንም ተጨማሪ የተከለክሉና ከዕርዳታ ተግባሩ ጋር የማይገናኝ ቁሳቁስ መያዙ ተሰምቷል። ይህን አስመልክቶ መንግስት እስካሁን በይፋ ያለው ነገር የለም። ይሁን እንጂ በዕርዳታ ስም የማስታጠቅና የ1977ቱን ድርጊት የመድገም ሙከራዎች መያዙን ማስታወቁ አይዘነጋም።
- ብልጽግናና ትህነግ ሶስተኛ ውይይት አደረጉ፤ ማናቸውንም ግጭቶች በጋራ ለመከላከል ተስማሙየትግራይ ኃይሎችን ትጥቅ የማስፈታት፣መበተንና ወደ ማህበረሰቡ መልሶ የማዋሃድ የቅድመ ማስጀመሪያ ምክክር በትግራይ መጀመሩ በተሰማ ማግስት በብልፅግና ፓርቲና በሕወሃት መካከል የተጀመረው የፓርቲ ለፓርቲ ፓለቲካዊ ውይይት በመቐለ ከተማ መካሄዱ… Read more: ብልጽግናና ትህነግ ሶስተኛ ውይይት አደረጉ፤ ማናቸውንም ግጭቶች በጋራ ለመከላከል ተስማሙ
- በትግራይ በጊዚያዊ አስተዳደሩና በትህነግ መካከል የስልጣን ሽኩቻ ውጥረቱ ከሯል፤ አንድ መኮንን ተገደሉበትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደርና በትህነግ መካከል ያለው የስላጣን ሽኩቻ ተካሮ አንዱ በአንዱ ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻው በግላጭ እየተካሄደ ከመሆኑም አልፎ ጎራ ለይተው እስከመገዳደል እንዳይደረስና የተገኘው አንጻራዊ ሰላም እንዳይደፈርስ… Read more: በትግራይ በጊዚያዊ አስተዳደሩና በትህነግ መካከል የስልጣን ሽኩቻ ውጥረቱ ከሯል፤ አንድ መኮንን ተገደሉ
- የአባይ ድልድይ ተመረቀ፤ ፋኖ ኢላማውን የጠበቀ ጥቃት ሰነዘርኩ አለ፤ አብይ አሕመድ “መገዳደል ይብቃ” አሉበተመረጡ ቦታዎች፣ የግልና የመንግስት ተቋማት ላይ ቦንብ ማፈንዳቱን ፋኖ አስታወቀ። ይህን ያስታወቀው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የአባይ ድልድይን ለመመረቅ ወደ ባህር ዳር እንዳይመጡ ለ”ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ” በሚል በተለያዩ… Read more: የአባይ ድልድይ ተመረቀ፤ ፋኖ ኢላማውን የጠበቀ ጥቃት ሰነዘርኩ አለ፤ አብይ አሕመድ “መገዳደል ይብቃ” አሉ
- ኢትዮጵያ በአሜሪካ የሚኖሩ “ተፈላጊዎች” ተላልፈው እንዲሰጧት ጥያቄ አቀረበችአሜሪካ ተቀምጠው የኢትዮጵያን ሰላም የሚያውኩ ተፈላጊዎችን ሀገሪቱ አሳልፋ በመስጠት ትብብር እንድታደርግ የፌደራል ፖሊስ መጠየቁ ተገለጸ። በጀርመን በተመሳሳይ ስራ መጀመሩ የሚታወስ ነው። ኢትዮጵያ በአሜሪካ የሚኖሩ “ተፈላጊዎች” ተላልፈው እንዲሰጧት… Read more: ኢትዮጵያ በአሜሪካ የሚኖሩ “ተፈላጊዎች” ተላልፈው እንዲሰጧት ጥያቄ አቀረበች
- ሃሰተኛ የተባሉ የዩቲዩበር ባለቤቶች ተያዙ፤ በአንድ ተጠርጣሪ ብቻ ስምንት የዩቲዩብ ቻናል ተከፍቷልፈቃድ ሳይኖራቸው በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት አማረ እና ቤተሰቦቹ በተባለ ህንፃ ላይ ቢሮ ተከራይተው ሃሰተኛና የፈጠራ ወሬ ሲያሰራጩ ነበሩ የተባሉ ተጠርጣሪዎች መያዛቸው ተገለጸ። ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት በህዝብ… Read more: ሃሰተኛ የተባሉ የዩቲዩበር ባለቤቶች ተያዙ፤ በአንድ ተጠርጣሪ ብቻ ስምንት የዩቲዩብ ቻናል ተከፍቷል