ጅቡቲ አንድም ወታደር ወደ ኢትዮጵያ ድንበር እንዳላስጠጋች የፋይናንስና ኢኮኖሚ ሚኒስትሩ አስታወቁ። ሚኒስትሩ ይን ያሉት ራሺድ አብዲ የሚባሉት የምስራቅ አፍሪቃ ተንታኝ “ጅቡቲ በከፍተኛ ደረጃ የታጠቀ ጦሯን ከኢትዮጵያ ጋር ወደሚያዋስናት ድንበር አሰማርታለች” በሚል ላሰራጩት ዜና ዚመልሱ
“ምንጭዎን አልቀበልም” ያሉት Ilyas Dawaleh ሊያስ ዳዋለህ ” አንድም ወታደርም ሆነ የትኛውም የታጠቀ ሃይል ወደ ድንበር እንዳልተሰማራም” የሚል መልስ ብበቲውተር ገጻቸው አስፍረዋል። ” ይህንን ላረጋግጥልዎት እችላለሁ” ሲሉ አስረግጠው ሚኒስትሩ ነግረዋቸዋል። ” ይህን እንድናስብና ጦር እንድናሰማራ የሚያደርገን አንዳችም አደጋ አላጋጠመንም” ሲሉም አክለው ለ” ተንታኙ ቲዊት ምላሽ ሰጥተዋል። በሌላ አነጋገር ” አትቀደድ” ብለዋቸዋል።
የምስራቅ አፍሪቃ አጥኚ፣ ተመራማሪ፣ የፖለቲካ አዋቂ እንደሆኑ በገለ ታሪካቸው ያስቀመጡት ራሺድ አብዲ 136.4 ሺህ ተከታታይ ባላቸው የቲውተር አምዳቸው ላይ ” ጅቡቲ የታጠቁ ወታደሮቿን ከኢትዮጵያ ጋር ወደሚያዋስናት ድንበር አሰማርታለች” ሲሉ የጀምራሉ። አያይዘውም ” ከኢትዮጵያ ጋር የሚያገናኘውን የባቡርና የአውቶሞቢል መንገድ ለመከላከል ጅቡቲ ሃይሏን አስፍራለች” ብለዋል። ዘጠና አምስት በመቶ ኢትዮጵያ በጅቡቲ ወደብ አማካይነት እቃዎችን ወደ አገር ቤት እንደምታስገባ አውስተው ” የትህነግ ሃይል አሁን አፋር ውስጥ ነው። ቡድኑ የትራንስፖርት መስመሩን ሊቆርተው ይችላል” የሚል ሟርት ጽፈው ነበር።
እሳቸው ብቻ ሳይሆኑ ሮይተርስን ጨምሮ በርካታ የውጭ ሚዲያዎችና የተገዙ ኢትዮጵያዊያንም ይህንኑ ሟርት ሲያስተጋቡ ነበር። የጅቡቲው የፋይናንስና ኢኮኖሚ ሚኒስትር ” ምንጭህን ተወውና” ሲሉ ጅቡቲ ወታደር ሰማንቀሳቀስ ጭራሽ አለማሰቧን ያስረዱት።
ትህነግ በያዘው እቅድ መሰረት የጅቡቲን መንገድ በዚህ ሳምንት በቁጥጥር ስር በማድረግ የመደራደሪያ አቅም ለማስፋት ታስቦ እንደንበር ደጋፊዎቻቸው በስፋት ሲናገሩ ነበር። ይሁን እንጂ ዛሬ መከላከያ ዛሬ በሰተው መግለቻ አፋር ዘልቆ የነበረው የትህነግ ሃይል ሙሉ በሙሉ መደምሰሱ አስትውቋል። የትህነግ አመራሮችም አላስተባበሉም።
የአማራ ክልል ኮሙኒኬጭን ቢሮ በበኩሉ አላማጣና ቆቦን እንደያዘ አድርጎ አሸባሪው ቡድን የሚያወራው ሃሰት መሆኑንን ቢያንስ ነዋሪዎች ይታዘባሉ ሲል የክልሉ ሚሊሻና ልዩ ሃይል ድል ማስመዝገቡንና ጥቃቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል። መከላከያ በበኩሉ ትንኮሳ ሲኖር እርምጃ እንደሚወስድ፣ ከዚህ ውጪ መንግስት ሲወስን ሙሉ ማጥቃት የማድረግ አቅምና ዝግጁነት እንዳለው ይፋ አድርጓል።
የኢትዮጵያ አየር ሃይልም በበኩሉ ከመቼውም ጊዜ በላይ ማናቸውንም ጥቃት ለመዘንዘር ዝግጅቱ እንዳለውና የመንግስትን ትእዛዝ ብቻ እንደሚተብቅ አመልክቷል። ይህ በንዲህ እንዳለ የአፋር ኮሙኒኪሽን ቢሮና የአፋር ልዩ ሃይል በበኩላቸው በርካታ ሕሳናት መማረካቸውን አመልክተዋል። ምስክሮች እንደሚሉት ከሆነ አፋር ክልል ዘልቆ የገባው የትህነግ ሃይል በሄሊኮፕተር በተደረገ ዘመቻ ክፉኛ መጎዳቱ ታውቋል።
በሌላ ዜና አንቶኒ ብሊንከን የወቅቱን የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር በስክል ስለ ትግራይና አባይ ግድብብ ጉዳይ ማነጋገራቸውን መስሪያ ቤታቸው አስታውቋል። መግለጫው ዝርዝር የውይይቱን ሃሳብ በጥልቅ ባይዘረዝርም አፍሪካ ሕዝብረት ኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲያድረግ የተጀመረው ዘመቻ አካል መሆኑን ያመላክታል።
- “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”“የሚሊሻ ኀይሉን በተመለከተ የሚዘዋወረው መረጃ ፍጹም መሠረተ ቢስ ነው” ሲሉ ኮሎኔል ግርማ ገሰሰ አስታወቁ። “ቅጥፈት ነው” ያሉትና በፕሬዚዳንቱ ስምና ፊርማ የተሰራጨው ደብዳቤ የሚሊሻ ሃይሉ… Read more: “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”
- “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን“የትግራይ ተወላጆች ትህነግ ለፈጸመው ወረራ፣ ዘረፋ፣ ማፈናቀልና የግድያ ተግባራት የተቀናጀ የፖለቲካና የሚዲያ ድጋፍ ሰጥተዋል። በተለይም በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ ሮማናት አደባባይ ላይ የተለመደው አይነት… Read more: “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን
- “ትህነግ ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው ” የዜናው ሰም፣ ወርቅና የትህነግ ‘ ሃሰት ነው’ ማስተባበያለአንድ ቀን ከጮኸና አየሩን ሁሉ ከተቆጣጠረ በሁዋላ ውሃ የተቸለሰበት “ሕወሓት ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው” የሚለው የዋዜማ ዜና ፖለቲካውን ለሚረዱ የዜናው ሰምና ወርቅ ትርጉም… Read more: “ትህነግ ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው ” የዜናው ሰም፣ ወርቅና የትህነግ ‘ ሃሰት ነው’ ማስተባበያ
- National Dialogue, Transitional Justice And Rehabilitation Process Pillars of Lasting Peace, Prosperity: CouncilThe Ethiopian National Security Council has issued a statement on latest developments in the country. In its statement, the Council underscored the need to… Read more: National Dialogue, Transitional Justice And Rehabilitation Process Pillars of Lasting Peace, Prosperity: Council
- ቀሲስ በላይ በተጠረጠሩበት ወንጀል ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረቡ ዋስትና ተከለከሉየፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት የቀሲስ በላይ መኮንንን ጨምሮ የ3 ግለሰቦችን ጊዜ ቀጠሮ መዝገብን ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ተመልክቷል። ቀሲስ በላይ… Read more: ቀሲስ በላይ በተጠረጠሩበት ወንጀል ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረቡ ዋስትና ተከለከሉ