ትናንት በአፋር በኩል ትንኮሳ ፈጽሞ ሜይዴይ የሚባለው ሀይሉ የተደመሰሰበት አሸባሪው ህወሓት ህጻናትን በጦርነቱ ማሳለፉን የሚያረጋግጥ ተጨማሪ መረጃዎች እየወጡ ነው። በጌታቸው ረዳ ቅስቀሳ እየተማገዱ ያሉ ሕጻናትን ያዩ የትግራይ ተወላጆች ቁጣቸውን እያሰሙ ነው።
በትናንትናው እለት በአፋር ክልል አለሌ ሱሉላ በኩል የመጣውና የጁንታው ሜይደይ ተብሎ የሚጠራ ሀይል በሙሉ መደምሰሱ የተለጸ ሲሆን፤ ጁንታው ህጻናትን በጦርነቱ አሰልፎ እንደነበር በቁጥጥር ስር ከዋሉ ህጻናት ምርኮኞች ማረጋገጥ ተችሏል።
በቆቦ በኩል ሲተነኩስ የነበረው የአሻባሪው ሀይል እንደተደመሰሰ፤ ጁንታው ያሰማራቸው በርካታ ህፃናትም መማረካቸውን ምንጮቹን ጠቅሶ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ትናንት ምሽት ላይ መዘገቡ ይታወሳል። በዚህ ግንባር ተሰልፈው በሀገር መከላከያ ሰራዊትና በአፋር ልዩ ሃይል ከተያዙ ህጻናት መካከል የተወሰኑት ህጻናት ምስል ከስር ተያይዞ ቀርቧል።
ጁንታው ህጻናትን ለጦርነት እያሰለፈ መሆኑ በተደጋጋሚ እየተገለጸ ቢሆንም ዓለም አቀፉ ማህበሰብ እስካሁን በይፋ ያለው ነገር የለም። ትናንት ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ አሸባሪው ህወሓት ህጻናትን ለውትድርና እየተጠቀመ መሆኑን በመጥቀስ የባይደን አስተዳደር ምን ምላሽ አለው በሚል ጥያቄ የተነሳላቸው የአሜሪካ የነጩ ቤተመንግስት ቃል አቀባይ ጥያቄውን ሳይመልሱት ማለፋቸው ይታወሳል።
ዞባ ተምቤን እንዳለው ጌታቸው ረዳ ለፍርድ መቅረብ አለበት። ሲያስረዳም “የትግራይ ህጻናት ለምን ይጨፈጨፋሉ? ተጠያቂው እሱ ነው” ብሏል። ዞባ ይህን ይበል እንጂ ትህነግ ሓጻናትን ለጦርነት ሲያበረታታና ሲያዘገጅ የነበረው አስቀድሞ በመሆኑ ሁሉም የዚህ ወንጀል ተተያቂ መሆን እንዳለባቸው ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችና ተሰሚነት ያላቸው ወገኖች ቀስ እያሉ ተቃውሞ ከሚያሰሙት ጎን እየሆኑ ነው።
- የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ለትግራይ ሕዝብ ጥሪ አቀረበ፤ “አማራ ልዩነትህን ወደጎን አድርግ፤ዳግም በጅምላ አንቀበርም”“የትግል አደራ አይታጠፍም፤ ዳግም በጅምላ አንገደልም!” በሚል ርዕስ የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ባሰራጨው መግለጫ ትህነግን አስጠንቅቆ ” የወልቃይት ጠገዴ… Read more: የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ለትግራይ ሕዝብ ጥሪ አቀረበ፤ “አማራ ልዩነትህን ወደጎን አድርግ፤ዳግም በጅምላ አንቀበርም”
- በዝቋላ ገዳም የሆነው ይህ ነው!!More stories የባህር በር ህልውናችን!! አብይ አህመድ “መተንፈሻ ወደብ ያስፈልገናል” ሲሉ አወጁDecember 30, 2023 አዲሱ ሚኒስትር “የሰላም እጦት”February 23, 2024 ካለፈ በሁዋላ… Read more: በዝቋላ ገዳም የሆነው ይህ ነው!!
- Kenya’s military chief dies in a helicopter crash, Nairobi declares three days of national mourningKenya’s military chief Gen. Francis Ogolla died in a helicopter crash west of the country, President William Ruto announced Thursday and declared… Read more: Kenya’s military chief dies in a helicopter crash, Nairobi declares three days of national mourning
- U.S. stops UN from recognizing a Palestinian state through membershipCGTN – The United States on Thursday stopped the UN from recognizing a Palestinian state by casting a veto in the Security… Read more: U.S. stops UN from recognizing a Palestinian state through membership
- Israel launches missile attacks on Iran: reportCGTN – Israeli missiles have hit a site in Iran, ABC News reported late on Thursday, citing a U.S. official, while Iranian… Read more: Israel launches missile attacks on Iran: report