ትናንት በአፋር በኩል ትንኮሳ ፈጽሞ ሜይዴይ የሚባለው ሀይሉ የተደመሰሰበት አሸባሪው ህወሓት ህጻናትን በጦርነቱ ማሳለፉን የሚያረጋግጥ ተጨማሪ መረጃዎች እየወጡ ነው። በጌታቸው ረዳ ቅስቀሳ እየተማገዱ ያሉ ሕጻናትን ያዩ የትግራይ ተወላጆች ቁጣቸውን እያሰሙ ነው።
በትናንትናው እለት በአፋር ክልል አለሌ ሱሉላ በኩል የመጣውና የጁንታው ሜይደይ ተብሎ የሚጠራ ሀይል በሙሉ መደምሰሱ የተለጸ ሲሆን፤ ጁንታው ህጻናትን በጦርነቱ አሰልፎ እንደነበር በቁጥጥር ስር ከዋሉ ህጻናት ምርኮኞች ማረጋገጥ ተችሏል።
በቆቦ በኩል ሲተነኩስ የነበረው የአሻባሪው ሀይል እንደተደመሰሰ፤ ጁንታው ያሰማራቸው በርካታ ህፃናትም መማረካቸውን ምንጮቹን ጠቅሶ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ትናንት ምሽት ላይ መዘገቡ ይታወሳል። በዚህ ግንባር ተሰልፈው በሀገር መከላከያ ሰራዊትና በአፋር ልዩ ሃይል ከተያዙ ህጻናት መካከል የተወሰኑት ህጻናት ምስል ከስር ተያይዞ ቀርቧል።
ጁንታው ህጻናትን ለጦርነት እያሰለፈ መሆኑ በተደጋጋሚ እየተገለጸ ቢሆንም ዓለም አቀፉ ማህበሰብ እስካሁን በይፋ ያለው ነገር የለም። ትናንት ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ አሸባሪው ህወሓት ህጻናትን ለውትድርና እየተጠቀመ መሆኑን በመጥቀስ የባይደን አስተዳደር ምን ምላሽ አለው በሚል ጥያቄ የተነሳላቸው የአሜሪካ የነጩ ቤተመንግስት ቃል አቀባይ ጥያቄውን ሳይመልሱት ማለፋቸው ይታወሳል።
ዞባ ተምቤን እንዳለው ጌታቸው ረዳ ለፍርድ መቅረብ አለበት። ሲያስረዳም “የትግራይ ህጻናት ለምን ይጨፈጨፋሉ? ተጠያቂው እሱ ነው” ብሏል። ዞባ ይህን ይበል እንጂ ትህነግ ሓጻናትን ለጦርነት ሲያበረታታና ሲያዘገጅ የነበረው አስቀድሞ በመሆኑ ሁሉም የዚህ ወንጀል ተተያቂ መሆን እንዳለባቸው ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችና ተሰሚነት ያላቸው ወገኖች ቀስ እያሉ ተቃውሞ ከሚያሰሙት ጎን እየሆኑ ነው።
- ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር ውስጥ ናት፤ በጾሙ ማቅ ለብሰው በንስሃ ችግራቸውን ይፍቱየኢትዮጵያ ታሪክ ቁንጮ እንደሆነች የሚመሰከርላትና እጅግ ውብ ስብዕና ያላቸው አባቶች የሚጠቀሱላት ዕድሜ ጠገብቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር መተብተቧ እየተጠቆመ ነው።… Read more: ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር ውስጥ ናት፤ በጾሙ ማቅ ለብሰው በንስሃ ችግራቸውን ይፍቱ
- ሕብረቱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ግዢ ሊያውል ነውየአውሮፓ ሕብረት በአባል ሀገራቱ እንዳይንቀሳቀሱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ዩክሬንን ጦር መሳሪያ ለማስታጠቅ ሊያውል መሆኑ ተሰምቷል፡፡ More stories “ኦነግ ሸኔ በዝቋላ… Read more: ሕብረቱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ግዢ ሊያውል ነው
- ሳኡዲ የምታስገነባው አዲስ ከተማ – “ኒዮም ሲቲ” (Neom City)በረሃን ወደ ከተማነት የመቀየር ጥበብ ልንለው እንችላለን፡፡ ከ1 ትሪሊየን ዶላር በላይ የሚፈጅ ውድ ሥራም ነው፡፡ ከገንዘቡ ባሻገር ብዙ እውቀቶች ፈሰውበታል፤ አዳዲስ ነገሮች… Read more: ሳኡዲ የምታስገነባው አዲስ ከተማ – “ኒዮም ሲቲ” (Neom City)
- Ethiopia, Somalia dispute won’t transform into turmoil for the Horn of Africadeal between Ethiopia and Somaliland has sent waves of debates throughout the region, has even raised questions about the stability of the… Read more: Ethiopia, Somalia dispute won’t transform into turmoil for the Horn of Africa
- በአማራና ትግራይ ክልል ያሉ የወሰን ይገባኛል ጥያቄ በህዝብ ውሳኔ እንዲቋጭ ስምምነት ተደረሰትህነግ በበላይነት የሚመራው ኢህአዴግ ከፈርሰ በሁዋላ የተነሳውን ጦርነት ተከትሎ የአማራ ክልል ” ነጻ ወጡ” ባላቸው አካባቢዎች ለዓመታት የቆየ ውዝግብ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ… Read more: በአማራና ትግራይ ክልል ያሉ የወሰን ይገባኛል ጥያቄ በህዝብ ውሳኔ እንዲቋጭ ስምምነት ተደረሰ