ማንኛውም የተቀመጠውን መመሪያ የሚጥስ የአውሮፕላን አብራሪም ሆነ ኦፕሬተር ለሚደርሰው አደጋ ሃላፊነት እንደሚወስድ የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ አስጠንቅቋል፡፡

Ethiopia Current Issues Fact Check  የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ በማህበራዊ ትስስስ ገጹ ላይ ባሰፈረው ጽሁፍ፣ ቀደም ሲል ሰኔ 23 ቀን 2013 ዓ.ም የአየር በረራ መረጃ ማሳወቂያ (NOTAM& AIP SUP) ቁጥር A0166/21 እና AIP SUP A04 ,2021) መተላለፉን አስታውሷል፡፡

በተላለፈው መመሪያ መሠረትም ማንኛውም የአውሮፕላን አብራሪም ሆነ ኦፕሬተር የተቀመጠውን መመሪያ ከጣሰ ለሚደርሰው አደጋ ሃላፊነቱ የራሱ የጣሰው አካል መሆኑንን መግለጫው አስታውቋል።በስምምነቱና ማስታወቂያው መስረት በኮድና በቁጥር ተሰፍሮ በቀረበው ማሳወቂያ፣ መንግስት ይህን በማያከብሩ ላይ ለሚወሰደው እርምጃ ሃላፊነት እንደማይወስድ ለምን እንዳስታወቀ ምክንያቱን አላብራራም።

በማስታወሻው በይፋ ባይገለጽም በርዳታ ስም በቀጥታ ወደ ትግራይ በረራ እንዲደረግ ተደጋጋሚ ጥያቄ መቅረቡ ይታወሳል። መንግስት ጥያቄውን ተቀብሎ፣ ትብብር እንደሚያድርግ አስታውቆ እንዳለው ” ማንኛውም በረራ አዲስ አበባ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሶ ፍተሻ እንዲደረገበት በተደረሰው ስምምነት መሰረት የሚከናወን ነው። በዚሁ መግባቢያ መሰረት የዓለሙ የምግብ ድርጅት አውሮፕላን ከአንዴም ሁለቴ አስፈላጊው ፍተሻ ተደርጎበት መቀለ ደርሶ መመለሱ መዘገቡ ይታወሳል።

ስምምነቱ ይህ ሆኖ ሳለ ለምን መንግስት ይህን መግለጫ ለማውጣት እንደፈለገ ግልጽ ባያድረግም ስምምነቱን የመጣስ ሙከራ ስለመኖሩ አመልካች እንደሆነ ከግምት በላይ አስተያየት እየተሰጠ ነው። መንግስት መመሪያውን በጣሱ አካላት ላይ እርምጃ ከውሰደ ለጣልቃ ገብነት መነሻ ምክንያት ለማድረግ ታስቦ እንደሆንም ተመልክቷል።

It is to be recalled that as of June 30th 2021, a NOTAM& AIP SUP has been issued with reference number (A0166/21 and AIP SUP A 04 2021) by the Ethiopian Civil Aviation Authority. Therefore, violations against the above NOTAM will result in high risk to any operators and/or pilots. Entities violating the issued NOTAM therefore assumes full responsibility for any related actions.

Donate Button with Credit Cards

Leave a Reply