በመንግስት የሚሰጡ መግለጫዎች ሁሉ የሚያመለክቱት የትግራይን ህዝብ ሳይሆን ወንጀለኛውን ህወሓት ብቻ ነው– ወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ

የፌዴራል እና የክልል መንግስታት የሚሰጧቸው መግለጫዎች ሁሉ የሚያመለክቱት የኢትዮጵያ ማህበራዊ ውቅር አንድ አካል የሆነውን የትግራይ ህዝብ ሳይሆን ወንጀለኛውን ህወሓትን ብቻ መሆኑን የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ አስታውቋል፡፡

የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ እንዳስታወቀው የህወሓት ፕሮፓጋንዳ አራማጆች እና አጋሮቻቸው የፌዴራል እና የክልል አመራሮች የሚናገሩትን በመጠምዘዝ ለብዙ ወራት ሲሸርቡ ከቆዩት የሐሰት ዜናዎች እና አጀንዳዎቻቸው ጋር ለማጣጣም መሞከራቸውን እንደቀጠሉ ነው፡፡
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህወሃት አሸባሪ ድርጅት እንደ ሆነ ማወጁን በማገናዘብ፣ የፌዴራል እና የክልል መንግስት የሚሰጧቸው መግለጫዎች ሁሉ የሚያመለክቱት የኢትዮጵያ ማህበራዊ ውቅር አንድ አካል የሆነውን የትግራይ ህዝብ ሳይሆን፣ ወንጀለኛውን ህወሓትን ብቻ መሆኑን በጥብቅ አስገንዝቧል፡፡

Leave a Reply