ዐቃቤ ሕግ በእነ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ መዝገብ ጀነራል ገብረፃድቃን ገ/ትንሣኤን ጨምሮ በ74 ሰዎች ላይ ክስ መመስረቱን በይፋ ማህበአዊ ገጹ ይፋ አድርጓል። ሰነዶችንም አያይዟል።
የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በተከሳሾች ላይ ክስ የመሰረተዉ ተከሳሾች የፌዴራል መንግስትን በሀይል ለመለወጥ በማሰብ በሽብርተኝነት ከተፈረጀዉ ከህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ አመራሮች ተልእኮ በመቀበል ጥቃት ለማድረስ የሚችል የትግራይ ማእከላዊ ወታደራዊ ኮማንድ በማደራጀትና በመምራት በትግራይ ክልል በተለያዩ ቦታዎች ላይ በሚገኙ የሰሜን እዝ የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ፣በፌዴራል ፖሊስ እና በፌዴራል የመንግስት ተቋማት ላይ እንዲሁም በአማራ እና በአፋር ክልሎች በተጨማሪም በኤርትራ ላይ ጥቃት በማድረሳቸዉ ነዉ፡፡
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በ 1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)(ለ)፣33፣35፣38 እና የሽብርን ወንጀል ለመከላከል ለመቆጣጠር በ2012 ዓ.ም የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1176/2012 አንቀፅ 3(2) የተመለከተውን ድንጋጌ ተላልፈዉ በመገኘታቸዉ የሽብር ወንጀል ክስ መስርቶባቸዋል፡፡
ዐቃቤ ህግ ክስን ያስረዱልኛል ያላቸዉን ከ500 በላይ የሰዉ ምስክሮችን፣ ከ5ሺህ ገፅ በላይ የሆነ የሰነድ ማስረጃዎችን እንዲሁም የቴክኒክና የቪዲዮ ማሰረጃዎችን አያይዞ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡ክሱ የቀረበለት የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ተኛ የፀረ ሽብር ወንጀል ችሎት በመዝገብ ቁጥር 272829 የሽብር መዝገቡ ተከፍቶ ጉዳዩን እየተመለከተዉ ይገኛል፡፡
ሰነዶቹን እዚህ ላይ ይመልከቱ ፊስ ቡክ ገጽ
- አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎችባንኩ የክፍያ ሰነድ ቀረበለት። ማጣሪያ ጥያቄ ለህብረቱ አቀረበ። ሃሰት ሆኖ ተገኘና ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ያዘ። ጉዳዩ ወደ ህግ አመራ። አሁን ምኑ… Read more: አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎች
- የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋልየኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከንግድ ባንክ 300 ቢሊዮን ብር ዕዳ እንዳለበት ተገለጸ። የዕዳ ጫናውን ለማቃለል የባንክ ወልዱም ጭምር ተፅእኖ እያሳደረ መሆኑም… Read more: የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋል
- ዋና ዋና የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ይዘቶች – ሲጨመቁመግቢያ ሽግግር ፍትህ ጉልህ የመብት ጥሰቶች በተፈፀመባቸው ሀገራት ተጠያቂነትን ለማስፈን እና ተበዳዮችን ለመካስ ጥቅም ላይ ሲውል ቆይቷል፡፡ በሀገራችንም የሽግግር ፍትህ… Read more: ዋና ዋና የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ይዘቶች – ሲጨመቁ
- “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”“የሚሊሻ ኀይሉን በተመለከተ የሚዘዋወረው መረጃ ፍጹም መሠረተ ቢስ ነው” ሲሉ ኮሎኔል ግርማ ገሰሰ አስታወቁ። “ቅጥፈት ነው” ያሉትና በፕሬዚዳንቱ ስምና ፊርማ… Read more: “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”
- “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን“የትግራይ ተወላጆች ትህነግ ለፈጸመው ወረራ፣ ዘረፋ፣ ማፈናቀልና የግድያ ተግባራት የተቀናጀ የፖለቲካና የሚዲያ ድጋፍ ሰጥተዋል። በተለይም በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ ሮማናት… Read more: “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን