ለሜቻ ግርማ ” ካሁን በሁዋላ ዋጋ የለውም፤ መወዳደር አይችልም” በሚል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽ የህክምና ባለሙያና ቴክኒክ ክፍሉ ያሟርተበትና ያባረረው አትሌት ነው። ፌዴሬሽኑ በቅርቡ በሰጠው መግለጫ “ህዝባችን ይወቅልን” ሲሉ ካነሳቸው ጉድዮች አንዱ የለሜቻ ወደ ኦሊምፒክ መጓዝን ነበር። ዛሬ ከቶኪዮ የሚወጡ ሪፖርቶች እንደሚሉት አትሌቱ የርቀቱ ኮከቦች ለሆኑት ኪንያውያን ስጋት እንደሆነ ተደርጎ ነው።
የለሜቻን ጉዳይ አንስተን በዛው አክሉ ባለሙያዎች የሰማነውን ምስክረነት መዘገባችን ይታወሳል። ለሜቻ አትሊቲክስ ፌዴሬሽን ” ዋጋ የለህም ” በሚል ባባረረው ሳምንት ጊዜ ውስጥ ሞናኮ ዳይመንድ ሊግ ተሳትፎ 8፡07 በመሮጥ ሪከርድ አስመዝግቦ ቢያሸንፍም ፌዴሬሽኑ ” ሞቼ እገኛለሁ” ብሎ አቋሙን እንደማይቀይር አስታወቀ። ባደርግነው ማጣራት የለሜቻ አሰልጣኝ አሁን የብሄራዊ ቡድኑ የ3000 ሜትር መሰናክል ኮች ነው ” እባካችሁን ይህን ልጅ እድል ስጡት” ቢልም ሊሰሙት አልቻሉም።
በመጨረሻ እነ አሃይሌ ገብረስላሴ ያሉበት የኦሊምፒክ ኮሚቴ የቴክኒክ ቡድን ከባለሙያዎች ጋር መክሮ ለሜቻን አስመዘገበና ቶኪዮ ወሰደ። በዛሬው ምሽት እንደታየው ለሜቻ ሜዳሊያ ውስጥ እንደሚገባ ሰፊ ግምት ያገኝበትን ውድድር አድርጎ ለቀታዩ ፉክክር አልፏል። ባልደረባው ጌትነት ዋለም በጥሩ ብቃት ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፉን ተከትሎ ሁለቱም ኪንያዊያኖቹን እንደሚፈትኑ እየተነገረላቸው ነው።
ማምሻውን በተካሄደው ማጣሪይ ምድብ አንድን አትሌት ለሜቻ ግርማ በአንደኝነት ሲያተናቅቅ፣በምድብ ሁለት የተወዳደረው አትሌት ጌትነት ዋለ ሁለተኛ ሆኖ ጨርሷል። ከውድድሩ በሁዋላ ለሜቻ ግርማ ከፍ ያለ ግምት የተሰጠው አትሌት ሆኗል።
ተክለ ሰውነቱ፣ ልጅነቱና ጉልበቱ ከ3000 መሰናክል ብቁ ተወዳዳሪ እንደሚያደርገው ተነግሮት በዛው የቀጠለው ለሜቻ በ3ሺህ ሜትር የኢትዮጵያ ክብረወሰን ባለቤት እንደሆነ መረጃዎች ያመልክታሉ።
ከውድድሩ በሁዋላ ኢዜአ “አትሌቱ እአአ 2019 ኳታር ዶሃ በተከናወነው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ ይታወሳል::አትሌት ጌትነት ዋለ በበኩሉ በዚህ ውድድር ትልቁ ውጤቱ እአአ 2016 በተካሄደ የዓለም ከ20 አመት በታች ውድድር ሶስተኛ በመውጣት የነሃስ ሜዳሊያ ያሸነፈበት ነው። ኬንያ እአአ ከ1984 ጀምሮ በዘጠኝ ተከታታይ ኦሊምፒክ መደረኮች የወርቅ ሜዳሊያዎችን በማሸነፍ የበላይነቱን ይዛለች::በዚህም 3 ሺህ ሜትር መሰናክል የኬንያ የባህል ስፖርት ተብሎ እስከመጠራት ደርሷል” ሲል ቅድመ ውጤታቸው ጽፎላቸዋል።
በዘንድሮው የቶክዮ 2020 ውድድር ግን ኬንያውንያኑ አትሌቶች በተለይም ከኢትዮጵያ እና ከሞሮኮ አትሌቶች ጠንካራ ፉክክር እንደሚጠብቃቸው ተነግሯል::የአፍሪካ ተወካዮቹ ኢትዮጵያ ፤ኬንያ እና ሞኮሮ በፍጻሜው ውድድር ላይ በሁለት ሁለት አትሌቶች የተወከሉ ሀገራት ናቸው።የ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ውድድሩ ሰኞ ሐምሌ 26 -2013 ከቀኑ በ9:15 ይካሄዳል።
- ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር ውስጥ ናት፤ በጾሙ ማቅ ለብሰው በንስሃ ችግራቸውን ይፍቱየኢትዮጵያ ታሪክ ቁንጮ እንደሆነች የሚመሰከርላትና እጅግ ውብ ስብዕና ያላቸው አባቶች የሚጠቀሱላት ዕድሜ ጠገብቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር መተብተቧ እየተጠቆመ ነው።… Read more: ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር ውስጥ ናት፤ በጾሙ ማቅ ለብሰው በንስሃ ችግራቸውን ይፍቱ
- ሕብረቱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ግዢ ሊያውል ነውየአውሮፓ ሕብረት በአባል ሀገራቱ እንዳይንቀሳቀሱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ዩክሬንን ጦር መሳሪያ ለማስታጠቅ ሊያውል መሆኑ ተሰምቷል፡፡ More stories የአዲስ አበባ ከተማ… Read more: ሕብረቱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ግዢ ሊያውል ነው
- ሳኡዲ የምታስገነባው አዲስ ከተማ – “ኒዮም ሲቲ” (Neom City)በረሃን ወደ ከተማነት የመቀየር ጥበብ ልንለው እንችላለን፡፡ ከ1 ትሪሊየን ዶላር በላይ የሚፈጅ ውድ ሥራም ነው፡፡ ከገንዘቡ ባሻገር ብዙ እውቀቶች ፈሰውበታል፤ አዳዲስ ነገሮች… Read more: ሳኡዲ የምታስገነባው አዲስ ከተማ – “ኒዮም ሲቲ” (Neom City)
- Ethiopia, Somalia dispute won’t transform into turmoil for the Horn of Africadeal between Ethiopia and Somaliland has sent waves of debates throughout the region, has even raised questions about the stability of the… Read more: Ethiopia, Somalia dispute won’t transform into turmoil for the Horn of Africa
- በአማራና ትግራይ ክልል ያሉ የወሰን ይገባኛል ጥያቄ በህዝብ ውሳኔ እንዲቋጭ ስምምነት ተደረሰትህነግ በበላይነት የሚመራው ኢህአዴግ ከፈርሰ በሁዋላ የተነሳውን ጦርነት ተከትሎ የአማራ ክልል ” ነጻ ወጡ” ባላቸው አካባቢዎች ለዓመታት የቆየ ውዝግብ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ… Read more: በአማራና ትግራይ ክልል ያሉ የወሰን ይገባኛል ጥያቄ በህዝብ ውሳኔ እንዲቋጭ ስምምነት ተደረሰ