ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የተፃፈ ደብዳቤ በማስመሰልና ጉቦ ለመስጠት የሚውል ገንዘብ በቼክ በማዘጋጀት በፖሊስ ቁጥጥር ስር የነበረ ፌሮ ብረት ክምችት ለማስለቀቅ የሞከሩ ተጠርጣሪዎችን መያዙን የፌዴራል ፖሊስ ገለጸ። ባሕር ዳር:ሐምሌ 25/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ሐሰተኛ ማስረጃ በማቅረብና ጉቦ በመስጠት በፖሊስ ቁጥጥር ስር የነበረ ፌሮ ብረት ክምችት ለማስለቀቅ የሞከሩ ተጠርጣሪዎችን መያዙን የፌዴራል ፖሊስ ገልጿል።
በተጠርጣሪዎቹ ለማስለቀቅ የተሞከረው በቦሌ ክፍለ ከተማ ቡልቡላ አካባቢ በአንድ መጋዝን ውስጥ በሕገ-ወጥ መንገድ ተከማችቶ በፌዴራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለና በምርመራ ሂደት ላይ ያለ የፌሮ ብረት ነው።
ተጠርጣሪዎቹ ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የተፃፈ በማስመሰል “ሕጋዊነቱ ስለተረጋገጠ በቦታው የሚገኘው የፖሊስ ጥበቃ ተነስቶላቸው ወደ ፈለጉበት ማንቀሳቀስ እንዲችሉ ፈቅደናል” የሚል ሐሰተኛ ደብዳቤ አዘጋጅተው በመያዝና ጉቦ ለመስጠት የሚውል ገንዘብ በቼክ አዘጋጅተው ብረቱን በአምስት ተሽከርካሪ ጭነው ሊወጡ ሲሉ ሦስት ተጠርጣሪዎች በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ፣ በአዲስ አበባ ፖሊስና በፋይናንስ ኢንተለጀንስ ጠንካራ ክትትል ሊያዙ ችለዋል።
ባለፈው ሳምንት የተያዘው ብረት ባለቤት ነኝ ከሚል ተክላይ ከሚባልና አሜሪካን ሀገር ነዋሪ ነው ተብሎ ከሚነገረው ግለሰብ ጋር ሦስቱ ተጠርጣሪዎች የጥቅም ትስስር በመፍጠር በኤግዚቢትነት ተይዞ በምርመራ ሂደት ላይ ያለውን የፌሮ ብረት በጥበቃ ላይ ላሉት የፖሊስ አባላትና አመራሮች 500 ሺህ ብር ጉቦ ለመስጠት በአቢሲኒያ ባንክ አዲስ አካውንት ከፈተው ያስገቡ መሆኑም ነው የተገለፀው።
በተመሳሳይ ለሌሎች የጸጥታ አካላት 400 ሺህ ብር በባንክ እና የ25 ሚሊዮን ብር ቼክ አዘጋጅተው ብረቱ እንደሚለቀቅ ከተስማሙ በኋላ የፖሊስና የጸጥታ አካላቱ ጉዳዩን ሚስጥራዊ በሆነ መንገድ ለበላይ ኀላፊ በማሳወቅ ሂደቱ እንዲቀጥል በመደረጉ፤ ብረቱን በአራት ሲኖትራክ እና በአንድ ክሬን ለመጫን ተስማምተው በሁለት ሲኖትራክ እንደተጫነ ባንክ የገባው ብር እና ቼኩ፣ እንዲሁም የተፃፈው ሐሰተኛ ደብዳቤ እና ሦስቱ ተጣርጣሪዎች ከተዘጋጁት ተሽከርካሪዎች ጋር ከነአሽከርካሪዎቻቸው በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል።
ተጠርጣሪዎቹ ለጸጥታ አካላት በርካታ ገንዘብ ሰጥተው በማማለል ለሕገ-ወጥ ድርጊት ፖሊስ ተባባሪ እንዲሆን ያደረጉትን ጥረት በማክሸፍና ለሕግና ለመንግሥት ፍፁም ታማኝ በመሆን ወንጀሉ ለሕግ እንዲቀርብ በማድረግ የአሸባሪው ጁንታን እኩይ ሴራ ማክሸፍ መቻላቸውን ፌዴራል ፖሊስ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል። ኅብረተሰቡ አሁንም በዚህ አይነት የወንጀል ተግባር ላይ ለመሳተፍ የሚጥሩ የአሸባሪው ጁንታና ከጁንታው ጋር ግንኙነት ፈጥረው ሀገሪቱ ላይ የሚያሴሩ ባንዳ ግለሰቦችን እየጠቆመ አስፈላጊውን እገዛ እንዲያደርግ ፌዴራል ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል።
ምንጭ አዲስ አበባ ዜና አገልግሎት
- የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ለትግራይ ሕዝብ ጥሪ አቀረበ፤ “አማራ ልዩነትህን ወደጎን አድርግ፤ዳግም በጅምላ አንቀበርም”“የትግል አደራ አይታጠፍም፤ ዳግም በጅምላ አንገደልም!” በሚል ርዕስ የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ባሰራጨው መግለጫ ትህነግን አስጠንቅቆ ” የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ ፍትሐዊ እና ሕጋዊ ብቻ ሳይሆን፤ የትግሉ አስኳልና የ2010ሩ የፖለቲካ ለውጥ… Read more: የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ለትግራይ ሕዝብ ጥሪ አቀረበ፤ “አማራ ልዩነትህን ወደጎን አድርግ፤ዳግም በጅምላ አንቀበርም”
- በዝቋላ ገዳም የሆነው ይህ ነው!!More stories ” አልፎ እንዳይቆጨን … እድል እንዳያመልጥ ” ቁ. 1April 10, 2024 በዝቋላ ገዳም የሆነው ይህ ነው!!April 19, 2024 ዐቢይ አሕመድ ከትግራይ ህዝብ ተወካዮች ጋርApril 1, 2024 የባህር በር ህልውናችን!! አብይ አህመድ “መተንፈሻ ወደብ… Read more: በዝቋላ ገዳም የሆነው ይህ ነው!!
- Kenya’s military chief dies in a helicopter crash, Nairobi declares three days of national mourningKenya’s military chief Gen. Francis Ogolla died in a helicopter crash west of the country, President William Ruto announced Thursday and declared three days of national mourning. The helicopter was carrying 11 people, including Gen.… Read more: Kenya’s military chief dies in a helicopter crash, Nairobi declares three days of national mourning
- U.S. stops UN from recognizing a Palestinian state through membershipCGTN – The United States on Thursday stopped the UN from recognizing a Palestinian state by casting a veto in the Security Council to deny Palestinians full membership of the world body. It vetoed a… Read more: U.S. stops UN from recognizing a Palestinian state through membership
- Israel launches missile attacks on Iran: reportCGTN – Israeli missiles have hit a site in Iran, ABC News reported late on Thursday, citing a U.S. official, while Iranian state media reported explosions, days after Iran launched a retaliatory missile and drone… Read more: Israel launches missile attacks on Iran: report