ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የተፃፈ ደብዳቤ በማስመሰልና ጉቦ ለመስጠት የሚውል ገንዘብ በቼክ በማዘጋጀት በፖሊስ ቁጥጥር ስር የነበረ ፌሮ ብረት ክምችት ለማስለቀቅ የሞከሩ ተጠርጣሪዎችን መያዙን የፌዴራል ፖሊስ ገለጸ። ባሕር ዳር:ሐምሌ 25/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ሐሰተኛ ማስረጃ በማቅረብና ጉቦ በመስጠት በፖሊስ ቁጥጥር ስር የነበረ ፌሮ ብረት ክምችት ለማስለቀቅ የሞከሩ ተጠርጣሪዎችን መያዙን የፌዴራል ፖሊስ ገልጿል።
በተጠርጣሪዎቹ ለማስለቀቅ የተሞከረው በቦሌ ክፍለ ከተማ ቡልቡላ አካባቢ በአንድ መጋዝን ውስጥ በሕገ-ወጥ መንገድ ተከማችቶ በፌዴራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለና በምርመራ ሂደት ላይ ያለ የፌሮ ብረት ነው።
ተጠርጣሪዎቹ ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የተፃፈ በማስመሰል “ሕጋዊነቱ ስለተረጋገጠ በቦታው የሚገኘው የፖሊስ ጥበቃ ተነስቶላቸው ወደ ፈለጉበት ማንቀሳቀስ እንዲችሉ ፈቅደናል” የሚል ሐሰተኛ ደብዳቤ አዘጋጅተው በመያዝና ጉቦ ለመስጠት የሚውል ገንዘብ በቼክ አዘጋጅተው ብረቱን በአምስት ተሽከርካሪ ጭነው ሊወጡ ሲሉ ሦስት ተጠርጣሪዎች በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ፣ በአዲስ አበባ ፖሊስና በፋይናንስ ኢንተለጀንስ ጠንካራ ክትትል ሊያዙ ችለዋል።
ባለፈው ሳምንት የተያዘው ብረት ባለቤት ነኝ ከሚል ተክላይ ከሚባልና አሜሪካን ሀገር ነዋሪ ነው ተብሎ ከሚነገረው ግለሰብ ጋር ሦስቱ ተጠርጣሪዎች የጥቅም ትስስር በመፍጠር በኤግዚቢትነት ተይዞ በምርመራ ሂደት ላይ ያለውን የፌሮ ብረት በጥበቃ ላይ ላሉት የፖሊስ አባላትና አመራሮች 500 ሺህ ብር ጉቦ ለመስጠት በአቢሲኒያ ባንክ አዲስ አካውንት ከፈተው ያስገቡ መሆኑም ነው የተገለፀው።
በተመሳሳይ ለሌሎች የጸጥታ አካላት 400 ሺህ ብር በባንክ እና የ25 ሚሊዮን ብር ቼክ አዘጋጅተው ብረቱ እንደሚለቀቅ ከተስማሙ በኋላ የፖሊስና የጸጥታ አካላቱ ጉዳዩን ሚስጥራዊ በሆነ መንገድ ለበላይ ኀላፊ በማሳወቅ ሂደቱ እንዲቀጥል በመደረጉ፤ ብረቱን በአራት ሲኖትራክ እና በአንድ ክሬን ለመጫን ተስማምተው በሁለት ሲኖትራክ እንደተጫነ ባንክ የገባው ብር እና ቼኩ፣ እንዲሁም የተፃፈው ሐሰተኛ ደብዳቤ እና ሦስቱ ተጣርጣሪዎች ከተዘጋጁት ተሽከርካሪዎች ጋር ከነአሽከርካሪዎቻቸው በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል።
ተጠርጣሪዎቹ ለጸጥታ አካላት በርካታ ገንዘብ ሰጥተው በማማለል ለሕገ-ወጥ ድርጊት ፖሊስ ተባባሪ እንዲሆን ያደረጉትን ጥረት በማክሸፍና ለሕግና ለመንግሥት ፍፁም ታማኝ በመሆን ወንጀሉ ለሕግ እንዲቀርብ በማድረግ የአሸባሪው ጁንታን እኩይ ሴራ ማክሸፍ መቻላቸውን ፌዴራል ፖሊስ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል። ኅብረተሰቡ አሁንም በዚህ አይነት የወንጀል ተግባር ላይ ለመሳተፍ የሚጥሩ የአሸባሪው ጁንታና ከጁንታው ጋር ግንኙነት ፈጥረው ሀገሪቱ ላይ የሚያሴሩ ባንዳ ግለሰቦችን እየጠቆመ አስፈላጊውን እገዛ እንዲያደርግ ፌዴራል ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል።
ምንጭ አዲስ አበባ ዜና አገልግሎት
- ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር ውስጥ ናት፤ በጾሙ ማቅ ለብሰው በንስሃ ችግራቸውን ይፍቱየኢትዮጵያ ታሪክ ቁንጮ እንደሆነች የሚመሰከርላትና እጅግ ውብ ስብዕና ያላቸው አባቶች የሚጠቀሱላት ዕድሜ ጠገብቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር መተብተቧ እየተጠቆመ ነው። በተጀመረው የአብይ ጾም ማቅ ለብሰውና አመድ ነስንሰው ችግራቸውን ሊፈቱ እንደሚገባ ምክር እየተሰጠ ነው።… Read more: ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር ውስጥ ናት፤ በጾሙ ማቅ ለብሰው በንስሃ ችግራቸውን ይፍቱ
- ሕብረቱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ግዢ ሊያውል ነውየአውሮፓ ሕብረት በአባል ሀገራቱ እንዳይንቀሳቀሱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ዩክሬንን ጦር መሳሪያ ለማስታጠቅ ሊያውል መሆኑ ተሰምቷል፡፡ More stories ግብርና ሚኒስቴር በአማራና አፋር ክልሎች ድጋፍ ሰጠJune 4, 2022 የአማራና የትግራይ ህዝብ ወደ ሰላማዊ ግንኙነትJune 11,… Read more: ሕብረቱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ግዢ ሊያውል ነው
- ሳኡዲ የምታስገነባው አዲስ ከተማ – “ኒዮም ሲቲ” (Neom City)በረሃን ወደ ከተማነት የመቀየር ጥበብ ልንለው እንችላለን፡፡ ከ1 ትሪሊየን ዶላር በላይ የሚፈጅ ውድ ሥራም ነው፡፡ ከገንዘቡ ባሻገር ብዙ እውቀቶች ፈሰውበታል፤ አዳዲስ ነገሮች ተዋውቀውበታል፡፡ ዓለምን እጅ በአፍ አስጭኗል…. “ኒዮም ሲቲ” (Neom City) በሳውዲው ልዑል መሀመድ ቢን… Read more: ሳኡዲ የምታስገነባው አዲስ ከተማ – “ኒዮም ሲቲ” (Neom City)
- Ethiopia, Somalia dispute won’t transform into turmoil for the Horn of Africadeal between Ethiopia and Somaliland has sent waves of debates throughout the region, has even raised questions about the stability of the Horn of Africa and resulted in a similar deal struck between Somalia and Türkiye recently.… Read more: Ethiopia, Somalia dispute won’t transform into turmoil for the Horn of Africa
- በአማራና ትግራይ ክልል ያሉ የወሰን ይገባኛል ጥያቄ በህዝብ ውሳኔ እንዲቋጭ ስምምነት ተደረሰትህነግ በበላይነት የሚመራው ኢህአዴግ ከፈርሰ በሁዋላ የተነሳውን ጦርነት ተከትሎ የአማራ ክልል ” ነጻ ወጡ” ባላቸው አካባቢዎች ለዓመታት የቆየ ውዝግብ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመቋጨት ህገመንግስቱ በሚያዘው መሰረት በህዝበ ውሳኔ እንዲቋጭ በይፋ ስምምነት ላይ መደረሱ ተረጋገጠ። ተፈናቃዮች… Read more: በአማራና ትግራይ ክልል ያሉ የወሰን ይገባኛል ጥያቄ በህዝብ ውሳኔ እንዲቋጭ ስምምነት ተደረሰ