የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በአፋር ግንባር ትህነግ ላይ የተቀናጀ ጥቃት ሲከፈት በአካል ተገኝተው አመራር መስጠታቸው ታወቀ። የደንነት ዳይሬክተር አቶ ተመስገንን፣ ኤታማዦር ሹማቸውንና የአየር ሃይል አዛዥን ይዘው በስፍራው አመራር ሲሰጡ የሚያሳዩ ምስሎች ይፋ ሆነዋል።

ዝርዝር መረጃ ያልተነገረበት መረጃ እንደሚያመልክተው ጦርነቱን በቅርብ መምራት የሚያችሉ ዘመን አፈራሽ መሳሪያዎች ታይተዋል። ጭፍራን ተቆጣጥሮ የጅቡቲን መንገድ እንደሚዛጋ በይፋ ያስታወቀው ትህነግ ያለው ሳይሆን በስፍራው ጠቅላይ ሚኒስትሩና የጦር መሪዎች በስፍራው ከአፋር ክልል ፕሬሲዳንትና አመራሮች ጋር በስፍራው አመራር ሲሰጡ መታየቱ የሰሞኑንን ዜና ያመከነ እንደሆነ ተመልክቷል።

አብዛኛውን የአፋርን ክልል እንደተቀጣጠረ ሲያስታውቅ ለነበረው ትህነግ ደጋፊዎች እጅግ አስደንጋጭ የሆነው የስዕል ዜና ” ሰፊ መሬት ይዘን የመንግስትን እጅ እንጠመዝዛለን” ሲሉ ለነበሩት የትህነግ አመራሮች የተግባር ምላሽ ሆኖባቸዋል።

“አሸባሪ” ሲል መንግስት ለሰየመው ቡድን በየቀኑ ምላሽ መስጠቱ አስፈላጊ ባለመሆኑ ለሁለት ሳምንት አቶ ጌታቸው “አክተር” ሆነው ሲሰጡ የነበረውን ማብራሪያና የትህነግ “የላቀ ወታደራዊ ምትሃት” አድናቆት ስፍራው ላይ ሆነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያስተላለፉት ምስል በዜሮ አባዝቶታል።

ዛሬ ላይ መከላከያ ከድካም አገግሞ፣ በሰው ሃይል ተጠናክሮ፣ ሰንጋ እየቀርበለት፣ ጀርባውን የሚያስደግፍበት ደጀን አግኝቶ ከተደላደለና ወታደራዊ እርምቶችን ወስዶ ራሱን ያዘጋጀ በመሆኑ አጣድፎ እጅ ለመጠምዘዝ የሚደረገው ሙከራ ካሁን በሁዋላ እንደማይታሰብ ስለጉዳይ ቅርበት ያላቸው አመልክተዋል።

በግንባር ቅርብ ሆኖ በዘመናዊ ዲጂታል መሳሪያዎች ጠላትን እያዩ በማጥቃት የተይዙትን ስፍራዎች በሙሉ የአፋር ልዩ ሃይልና ሚሊሻ፣ መከላከያ ሰራዊትና አየር ሃይል በጣምራ አስለቅቀው ስፍራው ላይ ሆነው ላስተላለፉት የምስል ዜና አቶ ጌታቸው ያሉት ነገር የለም። አብይ አህመድን እግር ተግር እየሄዱ የሚሳደቡት አቶ ጌታቸው ይህ እስከታተመ ድረስ ቲውተራቸውም ዝም እንዳለ ነው።

በሌላ ዜና ‹‹በምዕራብ ትግራይ በኩል መተላለፊያ ኮሪደር ይከፈት የሚለው ግፊት ተቀባይነት የለውም›› ሲሉ አቶ ምትኩ ካሳ የብሄራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር አስታውቀዋል።

በትግራይ ክልል ሰብአዊ ድጋፍ ለሚሹ ተረጂዎች እርዳታ ለማቅረብ በሚል አንዳንድ ምዕራባዊያንና ተቋሞቻቸው በምዕራብ ትግራይ በኩል መተላለፊያ ኮሪደር ይከፈት የሚለው ግፊታቸው ተቀባይነት እንደሌለው ይፋ አድርገዋል።

እርዳታ አቅርቦቶች በፌዴራል መንግስትና በአፋር ክልል ከፍተኛ ጥረት ለትግራይ ህዝብ እየደረሰ መሆኑን ገለጹ።አቶ ምትኩ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፣ መንግስት ያሳለፈውን የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔ ባለመቀበል በአማራ እና በአፋር ክልሎች ላይ ትንኮሳ እየፈጸመ ያለው አሸባሪው ህወሓት ለትግራይ ክልል ተረጂዎች የሚቀርብን እርዳታ የያዙ ከ170 በላይ ተሽከርካሪዎችን አግቶ በማቆየቱ በክልሉ ያሉ ተረጂዎች ለከፍተኛ አደጋ ተጋልጠዋል።

ይህንን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም አንዳንድ ምዕራባዊያን አገራትና ተቋሞቻቸው ከሱዳን ቀጥታ እርዳታ ለማስገባት በሚል በምዕራብ ትግራይ በኩል መተላለፊያ ኮሪደር ይከፈት የሚል ጥያቄዎችን ማቅረባቸውን ጠቁመዋል።አንዳንድ ምዕራባዊያን አገራትና ተቋሞቻቸው ይህንን ይበሉ እንጂ መንግስት ለተረጂዎቹ እርዳታ ለማቅረብ የጅቡቲው መስመር በቂ መሆኑን በማሳወቅ ተጨማሪ ኮሪደር እንደማይከፈት ማሳወቁን በዚህም የጸና አቋም እንዳለው ማስታወቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

“በተደራጀ ሌብነትና ሙስና ላይ የተጀመረው እርምጃ ሀገርን ከዘረፋ የማዳን ህዝባዊ ትግል ነው”

በተደራጀ ሌብነትና ሙስና ላይ የተጀመረው እርምጃ ሀገርን ከዘረፋ የማዳን ህዝባዊ ትግል መሆኑን የፌደራል ስነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነርና የጸረ-ሙስና ብሔራዊ ኮሚቴው አባል ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ ገለጹ። በኢትዮጵያ ከኑሮ ውድነትና ስራ አጥነት ቀጥሎ የአገር ደህንነት ስጋት የሆነውን ሙስና ለመከላከል ብሔራዊ ፀረ ሙስና ኮሚቴ […]

ዜና ሌብነት – ደህንነትን የሌብነት ዜና ዳር ዳር እያለው ነው፤ በማይወራረድ ብር ዘረፋ መኖሩ ተሰምቷል

ሌብነትን እንዲያመክን የተቋቋመው የፋይናንስ አገለግሎት ደህነንት ሃላፊ በሌብነት ወንጀል ተጠርጥረው መታሰራቸው ይፋ መሆኑን፣ ቀደም ሲል በብሄራዊ ደህንነት የሎጂስቲክ ዋና መምሪያ ምክትል ዳይሬክተር ላይ የተከፈተውን ክስ ተከትሎ በአገር መረጃና ደህንነት አገልግሎት የማይወራረድ በሚባል ወጪ ከፍተና ሃብት እየተዘረፈ መሆኑ ሙሉ መረጃ ለአቶ ተመስገን […]

በኦሮሚያ በሌብነት ጉዳይ አናቱ ተፈርቷል፤ በ289 ሺህ ካሬ.ሜ.መሬት ላይ ማጣራት ተጀምሯል

ትህነግ ይከተል በነበረው “አበስብስ” የሚባል ለውጭ የተግኮረጀ ስልት በርካታ በስልጣን ላይ ያሉ ሃላፊዎች ከሌብነት የጸዱ እንዳልሆነ መረጃዎች ያረጋግጣሉ። በተለይ ኦሮሚያ ላይ ሌብነት ገሃድ እንደሆነ ማሳያዎችም አሉ። ሰሞኑንን ይፋ የሆነውን የሌብነት ዘመቻ ተከትሎ ኦሮሚያ ሌቦች ላይ መዝመቱን ይፋ አድርጓል። ዋናው የሌብነቱ አናቱ […]

የብልጽግና ማዕ/ኮ መምከር መጀመሩ ተሰማ

ገዢው ፓርቲ ብልጽግና አራት ቀን እንደሚፈጅ የተነገረለትን የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ጀመረ። ይህ ስብስባ መንግስት በሌብነት ላይ በገሃድ ዘመቻ መጀመሩን ካስታወቀና ከትህነግ ጋር የሰላም አማራጭ ስምምነት ከፈጸመ በሁዋላ የመጀመሪያ እንደሆነ ተመልክቷል። ስብሰባው በተለይም ሌብነትን አስመልክቶ ጥብቅ ውይይት እንደሚደረግ ይገመታል። የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ […]

Loading…

Something went wrong. Please refresh the page and/or try again.

Leave a Reply