Site icon ETHIOREVIEW

ባለሃብቱ ወርቁ አይተነው “ለመስዋዕትነት ዝግጁ ነኝ” አሉ

በቀርቡ ትልቅ የተባለ የዘይት ፋቢካ ያቋቋሙት ባለሃብቱ አቶ ወቅነህ አይተነው ” ወራሪዉ የትህነግ ታጣቂ በአስቸኳይ ከሰላም ወዳዱ የአማራ ህዝብ ወሰን ለቅቆ እንዲወጣ፤ ይህ ካልሆነም ወጣቱ ተደራጅቶ እንዲጠብቀኝ፤ እኔም እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ሌትና ቀን በከባድ መሳሪያ ከሚደበደበዉ ህዝብ ጋር በግንባር ፊት ለፊት በመሰለፍ ማንኛዉንም መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኔን አረጋግጣለሁ” ሲሉ ጥሪና ቃለ መሃላ አኖሩ። ከታች እንዳለ ቀርቧል።

የህወሓት ታጣቂዎች በአማራ ህዝብ ላይ የፈፀሙት ወረራ፣ በሰዉና በቁስ ላይ እያደረሱ ያሉት ዘግናኝ ወንጀል መወገዝ ያለበት ድርጊት ነው። ይህ ድርጊት በተባበበረ ክንዳችን እንዲቆም ሰላም ወዳድ የሆነ ሁሉ ሊሳተፍበት የሚገባ አስቸኳይ ተግባር ነዉ፡፡

ጁንታዉ በሀገር መከላከያ ሰራዊቱ ላይ በፈፀመዉ ክህደት ሀገራችን መልማት በሚገባት ጊዜ ጦርነትን መምረጡ ሳያንስ በፌደራል መንግስቱ የተወሰደዉን የተኩስ አቁም ስምምነት በመጣስ በአማራ ክልል የሚገኙ ዉስን ወረዳዎችን በመዉረር ዝርፊያ፣ ግድያና ማፈናቀል እየፈፀመ ይገኛል፡፡ ህዝብ ከምንግዜዉም በበለጠ ተደራጅቶና ተግባብቶ፣ አቅመ ደካማ ሆኖ መሳሪያ ያለዉም መሳሪያዉን ለወጣቱ በመስጠት ይሄንን አሸባሪ ቡድን ጠራርጎ በማስወጣት ነፃነቱን ማስመለስ ይኖርበታል፡፡

የአማራ ህዝብ በቁመህ ጠብቀኝና ክላሽ እየተዋጋ፥ አሸባሪዉ ሃይል ደግሞ በታንክ፥ በዙ ፥ በሞርታርና ዲሽቃ ንፁህ የአማራ ገበሬዎችን እየጨፈጨፈ መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም፡-

እግዚአብሔር ከኛ ጋር ነዉ! ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! አቶ ወርቁ አይተነዉ ሐምሌ 30 ቀን 2013 ዓ.ም

Exit mobile version