Site icon ETHIOREVIEW

“ህወሓት መቶ ፐርሰንት እቅዱ ከሽፏል ተሸንፏልም “

ውጤት የሚገመገመው ካስቀመጡት ግብ አንፃር ነው። መንግስት ትግራይን ከለቀቀ በኋላ ህወሀት ወደ ሙሉ ማጥቃት ሲገባ አራት የውጊያ ስትራቴጂዎችን ነድፎ ነው።

ንድፍ አንድ:- ከመቀሌ አለማጣ ቆቦ ወልደያን በመቆጣጠር ወልደያ ላይ አቅምን አጠናክሮ በደሴ ኮምቦልቻ ሸዋ ሮቢትን ይዞ በሁለት ክንፍ ወደ አዲስ አበባ መገስገስ ነበር። ሆኖም በዚህ መስመር ወደ አዲስ አበባ መገስገስ ይቅርና ወልደያን መያዝ አልተቻለም። ክሽፈት ወይንም ሽንፈት አንድ ይሏል።

ንድፍ ሁለት:- በትግራይ ጨርጨር ባለው ሰፊ ግንባር የአፋር ክልልን ተቆጣጥሮ በሚሌ አቅጣጫ የኢትዮ ጂቡቲን መቆጣር ነበር። በዚህም ወፍ የለም። አፋርን መቆጣር ይቅርና ጭራሹኑ ሺዎቹን ገብሮ ወደ ተነሳበት ትግራይ ጨርጨር መስመር ተመልሶ መፈርጠጥ ግድ ብሎታል። ክሽፈት ሁለት ይላል።

ንድፍ ሶስት:-ወልደያን የዘጋው ሀይል ተጨማሪ ሀይል አግኝቶ በሳንቃ ሰሜን ወሎ መቄት…. ጎንደር መስመር ጨጨሆ ….ክምር ዲንጋይ… ጋሳኝ ደብረታቦር አድርጎ ሰሜን ጎንደርን ከደበብ ጎንደር እንደዚሁም …… ከጎጃም አዲስ አበባ መቁረጥ ነበር። እዚጋርም ቢሆን ህወሀት …በማይመለከተው አቅጣጣጫ በግዳን ወረዳ በከንቱ ከመማሰን ወጪ ቢያንስ ጋይንት ድረስ ሊገፋ የሚችልበትን አቅም አላገኘም።
ከሽፈት ሶስት ተብሎ ይመዝገብ ።

በነገራችን ላይ በዚህ አቅጣጫ በቅዱ መሰረት ቢሂድ ኖሮ በአንድ አቅጣጫ በወልደያ ደሴ መስስመር በሌላ አቅጣጫ በደብረታቦር በሀርዳር ወደ አዲስ አበባ ይገሰግስ ነበር። ይህ ብቻ አይደለም በትግራይ ጨርጨር በአፋር የተወረወረው የህወሀት ሀይልም በአዋሽ ናዝሬት አዳማ አቅጣጫ ዞሮ አዲስ አበባን በመድፍ ርቀት ቀለበት ስር ባስገባት ነበር። እዚህ ጋርም በዜሮ የተባዛ እቅድ ነው የሆነው። አልተሳካምምምምም።

ንድፍ አራት:- በሰሜን ምዕራብ አቅጣጪ ሰፊ የማጥቃት ግንባርን በመክፈት ወልቃይት ጠገዴን ሁመራን በመቆጣጠር በሱዳን ያለውን መስመር ማስከፈት ሌላኛው የህወሀት የጦርነቱ ንድፍ ነበር ።

በዚህም የታቀደው እቅድ መቶ ፐርሰንት ከሽፏል። ህወሓት በዚህ አቅጣጫ 12 ጌዜ ማጥቃት ከፍቶ ቢያንሱ አንዱ እንኳን አልተሳካም። ክሽፈት አራት ተብሎ ይመዝገብ።

ይህ ሁሉ ሲሆን መንግስት እየተከላከለ እንጂ እያጠቃ አለመሆኑ እዚህ ጋር በደንብ ይመዝገብ።

በዚህ ሁሉ ሂደት ህወሀት ጭንቅ ቢለው ከወታደራዊ ስትራቴጂ አንፃር ምንንም አይነት ጠቀሜታ የሌላትን ላሊበላን ተቆጣጠረ። በእርግጥ ላሊበላ ታሪካዊ ከተማ በመሆኗ የከተማዋ በህወሓት ቁጥጥር ስር መውደቅ በአለም አቀፍ መገናኛ ብዙኋን ብዙ ተብሎለታል።

በዚህም ህወሓት የሞራል ደስታን አግኝቷል።
እንግዲህ ህወሀት በዚህ መልኩ በዚህ ክረምት ሸዎችን በየማሳው ገብሮ ከእቅዱ አንፃር 10 በመቶ ውጤት ሳያስመዘግብ መንግስት መከላከሉን ጨርሱ ወደ ሙሉ ማጥቃት የገባው። እውነት ለመናገር ህወሓት ያመሰን በፕሮፓጋንዳው ነው።
አሁን ህወሓት እያሸነፈ ነው የምትል ሰው ሰነድህን አምጣና እቅድ ከተግባር ጋር እያመሳከርክ ተከራከር።

Tsegaw Melaku face book

Exit mobile version