የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል ተመሥገን ጥሩነህ አሸባሪውን የትህነግ ቡድን ለመጨረሻ ጊዜ ለማጥፋት የፌዴራል መንግሥት ከክልሎች ጋር እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አሸባሪው ቡድን አፈንግጦ ትግራይ ክልል በመመሸግ የፌዴራልና የክልል መንግሥታትን በመተንኮስ ለማፍረስ ያደረገውን ሙከራ አንስተዋል፡፡ አሸባሪውን ቡድን በአጭር ጊዜ እስከወዲያኛው ለመንቀል የፌዴራልና የክልል መንግሥታት በጋራ እየሠሩ ነው።
በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት በማድረስ የከፈተውን ግልጽ ጦርነት በአጭር ጊዜ ውስጥ ድል ማድረግ እንደተቻለ ገልጸዋል፡፡ ይሁን እንጂ ቡድኑ በአሁኑ ወቅት የማወናበድ ተግባሩን ተጠቅሞ ሕዝቡን በማነሳሳት በየቦታው ጥቃትና ወረራ እየፈጸመ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ የሽብር ቡድኑ በሌሎች አካባቢዎች ያሉ የሽብር ቡድኖችን ለመጠቀም ጥረት እያደረገ እንደሚገኝም አመላክተዋል፡፡
በተሳሳተ ፖለቲካ የትግራይ ሕዝብን ለጦርነት በመማገድ ጦርነቱን ሕዝባዊ አድርጎታል ያሉት አቶ ተመሥገን ሕዝቡ ከኢትዮጵያውያን ጋር መጋጨት እንደማይፈልግ ቢገልጽም የአንድ ሳምንት ስልጠና በመስጠት በግዳጅ ለጦርነት አሰልፏል ብለዋል፡፡
በትግራይ ክልል ልጅ ያለው ሁሉ ልጁን ወደ ግንባር እንዲልክ እየተገደደ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ ይህንን አሸባሪ ቡድን በአጭር ጊዜ ለማጥፋት የፌዴራልና የክልል መንግሥታት በጋራ እየሠሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ቡድኑን ከአማራና ከአፋር ክልሎች ለማስወጣት ብቻ ሳይሆን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት መሆኑንም ዳይሬክተር ጀነራሉ አስታውቀዋል፡፡
ለዚህም ኢትዮጵያውያን የተጠናከረ ድጋፍ እያደረጉ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል፡፡ የትግራይን ሕዝብ ከሽብር ቡድኑ ነጻ ለማውጣት ጭምር እንደሚሠራም አመላክተዋል፡፡
የአማራ ሕዝብ ወረራውን ለመቀልበስ እየተረባረበ ነው፤ የኢትዮጵያ ሠራዊትም በሙሉ ዝግጅትና ቁርጠኝነት ሕዝቡን ለመጠበቅ እየሠራ ነው፡፡ ሕግ የማስከበር ተግባሩ በፌዴራልና በክልል ሳይታጠር በጋራ የሚሠራ ነው ብለዋል።
በአማራና በአፋር ግንባር የፌዴራል የደኅንነትና የጸጥታ መዋቅር በስፋት ስምሪት መውሰዳቸውንም ጠቅሰዋል፡፡ ከፍተኛ የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ክልል ልዩ ኀይል፣ አድማ ብተና፣ ፋኖ፣ ሚሊሻ እና የፖለቲካ አመራር ስምሪት መደረጉንም አስገንዝበዋል፡፡
ሠራዊቱ በወልድያና አካባቢዋ ትልቅ ገድል እየፈጸመ መሆኑንም አንስተዋል፡፡ ይሁን እንጂ መከላከያ ሠራዊት ሕዝባዊ ድጋፍ እንዳይኖረው የሽብር ቡድኑ ሐሰተኛ መረጃ እያናፈሰ ይገኛል፡፡
አንዳንድ ጤናማ ያልሆኑ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎችና በብልሹ አሠራራቸው የተባረሩ ሰዎች ሕዝቡን እያወናበዱት እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡ በነዚህ አካላት ላይ ርምጃ ይወሰዳል ብለዋል።
ሕዝብ እንዳይጎዳ እየተዋጋ ያለውን የመከላከያ ሠራዊት ተጋድሎ የአካባቢው ነዋሪዎች በትክክል እንደሚመሰክሩም ጠቅሰዋል፡፡ አሸባሪ ቡድኑ በእኩይ ድርጊቱ በሕዝብ ትግል ከስልጣን እንደተወገደ ኹሉ በሕዝብ ትግል እንቀብረዋለን፤ ለዚህም ስትራቴጂ ተነድፎ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡
ሁሉም አካል ባለው አቅም ከተንቀሳቀሰ በአጭር ጊዜ ውስጥ ቡድኑን ማጥፋት ይቻላል ብለዋል። ሕዝቡም ይህንን በመገንዘብ ትግሉን እንዲያጠናክር ጥሪ አቅርበዋል።
አቶ ተመሥገን የመከላከያ ሠራዊቱን በማዘመን ይበልጥ የማደራጀት ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
- “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን“የትግራይ ተወላጆች ትህነግ ለፈጸመው ወረራ፣ ዘረፋ፣ ማፈናቀልና የግድያ ተግባራት የተቀናጀ የፖለቲካና የሚዲያ ድጋፍ ሰጥተዋል። በተለይም በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ ሮማናት አደባባይ ላይ የተለመደው አይነት… Read more: “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን
- “ትህነግ ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው ” የዜናው ሰምና ወርቅና የትህነግ ማስተባበያለአንድ ቀን ከጮኸና አየሩን ሁሉ ከተቆጣጠረ በሁዋላ ውሃ የተቸለሰበት “ሕወሓት ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው” የሚለው የዋዜማ ዜና ፖለቲካውን ለሚረዱ የዜናው ሰምና ወርቅ ትርጉም… Read more: “ትህነግ ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው ” የዜናው ሰምና ወርቅና የትህነግ ማስተባበያ
- National Dialogue, Transitional Justice And Rehabilitation Process Pillars of Lasting Peace, Prosperity: CouncilThe Ethiopian National Security Council has issued a statement on latest developments in the country. In its statement, the Council underscored the need to… Read more: National Dialogue, Transitional Justice And Rehabilitation Process Pillars of Lasting Peace, Prosperity: Council
- ቀሲስ በላይ በተጠረጠሩበት ወንጀል ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረቡ ዋስትና ተከለከሉየፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት የቀሲስ በላይ መኮንንን ጨምሮ የ3 ግለሰቦችን ጊዜ ቀጠሮ መዝገብን ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ተመልክቷል። ቀሲስ በላይ… Read more: ቀሲስ በላይ በተጠረጠሩበት ወንጀል ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረቡ ዋስትና ተከለከሉ
- መንግስት ክትግስት በኋላ የሚከሰት ሕግ ማስከበር ውጤቱ አስከፊ እንደሚሆን አስታውሶ ጦርነት ናፋቂዎች አደብ እንዲገዙ አሳሰበ“ካለፈው ስሕተታቸው ሳይማሩ ዛሬም ተመሳሳይ ችግር ለመፍጠር የሚከጅሉትን ሁላችንም ተባብረን አደብ ማስገዛት ይኖርብናል። ከትዕግሥት በኋላ የሚከሠት ሕግ የማስከበር ሥራ የሚኖረውን አስከፊ ውጤት ከቅርቡ ታሪካችን… Read more: መንግስት ክትግስት በኋላ የሚከሰት ሕግ ማስከበር ውጤቱ አስከፊ እንደሚሆን አስታውሶ ጦርነት ናፋቂዎች አደብ እንዲገዙ አሳሰበ