Site icon ETHIOREVIEW

ማርከህ “ያስፈታኸውን ውረስ፣ለሰራኸው ጀብዱና ጀግንነት ሽልማት ይሁንህ” ደቡብ ጎንደር

” ከግንባር ጠላት ሸሽቶ ሲወጣ ከቦ በመደምሰስ አንድም ጠላት እና በጠላት እጅ ያለ ንብረትና ትጥቅ እንዳይወጣ በማድረግ ማርከህ ያገኘኸውን ትጥቅ ለሰራኸው ጀብዱና ጀግንነት ሽልማት ይሁንህ። ወጥተህ ደምስስ!! ታሪክን በደማቅ ቀለም ጻፍ!!” ሲሉ የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቀለመወርቅ ምህረቴ አወጁ።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ “በጀግናው መከላከያ ሠራዊት፣ ልዩ ኀይል ፣ ፋኖ፣ ጀግና አርበኛ እና የደቡብ ጎንደር ሕዝብ በጋራ ጥምረት የሕዝባችን እና የሀገራችን አረሞች እየነቀለ እና ቀብራቸውን እያፋጠነ ይገኛል።” ካሉ በሁዋላ አክለውም “በሚያጋጥሙን ትንንሽ ችግሮች የተሸነፍን የሚመስለው የጠላት ኀይል እንደ እብድ ውሻ ሆኗል። የእብድ ውሻ መጨረሻው ደግሞ ይታወቃል” ሲሉ አመልክተዋል።

በሰሜን ወሎ በኩል ከወደ ወገልጤና አቅጣጫ እያጠቃ ባለወ የወገን ኃይል እስታይሽ ቀበሮ ሜዳ እና ጋሸና በቁጥጥራችን ስር በመዋላቸው ጠላት የስንቅና ትጥቅ አቅርቦት ተዘግቶበታል። እንዲሁም የሰው ኀይል ድጋፍ የሚያገኝበት በሩ ስለተዘጋ መፈርጠጡ አይቀሬ እንደሆነ አቶ ቀለመወርቅ አመልክተዋል። ስለሆነም ” የጋይንት፣ የጉና፣ የፋርጣ እና የእስቴ ነዋሪዎች እየሠራችሁት ያለው ገድል አይረሴ ነው እና እየከፈላችሁት ላለው መሰዋእትነት ከልብ የመነጨ ምስጋናየን አቀርባለሁ” በማለት ሕዝቡ አገሩንና አካባቢውን ለማስጠበቅ ከጠላት ጋር እያደረገ ያለውን ትንቅንቅ አድነቀዋል።

አስተዳዳሪው አክለውም “ከግንባር ጠላት ሸሽቶ ሲወጣ ከቦ በመደምሰስ አንድም ጠላት እና በጠላት እጅ ያለ ንብረትና ትጥቅ እንዳይወጣ በማድረግ ማርከህ ያገኘኸውን ትጥቅ ለሰራኸው ጀብዱና ጀግንነት ሽልማት ይሁንህ። ወጥተህ ደምስስ!! ታሪክን በደማቅ ቀለም ጻፍ!!” ሲል ጥሪና ክብር ሰጥተዋል።

Exit mobile version