በአዲስ አበባ ከተማ እርምጃው ተጀመረ

1 ሺህ 886 የንግድ ድርጅቶች ታሸጉ። 657 ድርጅቶች የንግድ ፈቃዳቸውን ተሰርዟል። ከ64 በላይ በወንጀል ተከሰዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ የኢኮኖሚ አሻጥር ሲሠሩ በነበሩ የንግድ ድርጅቶች ላይ ከማሸግ ጀምሮ በወንጀል እንዲጠየቁ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ አስታወቀ።

በዚሁ ጉዳይ የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልፈታ የሱፍ መግለጫ ሰጥተዋል።

በከተማዋ የኢኮኖሚ አሻጥር ሲሠሩ የነበሩ ፦

  • 1 ሺህ 886 የንግድ ድርጅቶች ላይ የማሸግ እርምጃ ተወስድቦባቸዋል።
  • ከንግድ ህግ ውጪ ሲሰሩ በተገኙ 657 ድርጅቶች የንግድ ፈቃዳቸው የመሠረዝ እርምጃ ተወስዷል።
  • ከ64 ላይ የሚሆኑ በወንጀል እንዲከሠሡ መደረጉን ጠቁመዋል።

በተጨማሪም የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ 369 መጋዘኖችን የመፈተሽ ስራ መሰራቱን እና በ20 መጋዘኖች ከፍተኛ የምርት ክምችት በመገኘቱ ታሽገዋል፤ የተከማቹት ምርቶችም ለተጠቃሚ እንዲደርስ ተደርጓል።

በነዚህ መጋዝኖችም ከፍተኛ መጠን ያለው የግንባታ ዕቃዎች በተለይም፦

  • ፌሮ ብረት፣
  • የምግብ ሸቀጦች፣
  • ጨው፣
  • በርበሬ፣
  • ዘይት፣
  • ጥራጥሬ የመሣሠሉት ክምችት የተገኘ ከመሆኑም ባሻገር ለጤና ደህንነት ጠንቅ የሆኑ የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው የጁስ ምርቶች በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

አቶ አብዱልፈታ በመግለጫቸው ፥ አንዳንድ ኃላፊነት የጎደላቸው ስግብግብ ነጋዴዎች ትክክለኛ ባልሆነ የመስፈሪያ መሣሪያዎች ምርቶችን እየሸጡ መሆኑ ተደርሶበት ሲሠሩበት የነበሩ 19 የመስፈሪያ መሣሪያዎች ተሠብስበው እንዲወገዱ መደረጉን አሳውቀዋል።

አዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ሌሎች ከተሞችም ለተመሳሳይ እርምጃ ራሳችሁን ማዘጋጀትና ወደ ስራ መግባት ይኖርባችኋል።

Via Addis Ababa communication office

See also   ኢትዮጵያ ዘመናዊ የባህርሃይል መገንባቷንና ጠላት ሁለቴ አንዲያስብ የሚያስገድድ ቁመና ያለው ጦር አንዳላት አስታወቀች

Leave a Reply