“በአማራ ሰማይ ላይ ከሚንሳፈፉት ጭልፊቶችና ከኢትዮጵጵያ አየር ኃይል ንስሮች የበለጠ ማን ሊናገር ይችላል..??…ማንም!!”

የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት

አይቀሬው ድል አድራጊነታችን በሁሉም የጦር ግንባሮች ከአስደናቂ ጀብደኞች ጋር ፍንትው ብሎ መታየት ጀምሯል፡፡
በአሸባሪው የትህነግ ቡድን ላይ የምንቀዳጀው ድል የሚለካው የሽብርተኛ ቡድኑን ታጣቂዎችና አዝማቾቻቸውን ተራራ ለተራራ ባሳደድናቸው የኪሎ ሜትር ርቀት መጠን የሚለካ እንዳልሆነ ደጋግመን ተናግረናል፡፡

ዛሬ ያገኘነውም ሆነ ነገ የምንቀዳጀው ድላችን የሚመዘነው የትህነግ ታጣቂዎች እግራቸው በረገጠበት በእያንዳንዷ የኢትዮጵያ ምድር አካል ላይ በህይወት እንዳይኖሩና ለህግ እንዲቀርቡ በማድረጋችን ብቻ ነው፡፡

በዚህ የድል መለኪያችን ሚዛን መሠረት አይበገሬው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ እና ፋኖዎች በእያንዳንዱ አውደ ውጊያዎች ላይ በሰነዘሩት የማያዳግም እርምጃ የአሸባሪው ትህነግ ቡድን ታጣቂዎች በደብረ ዘቢጥ፣ በጋሸ፣ በጊራናና አካባቢው፣ በጫንቅ፣ ጭና፣ አጅሬ ጃኖራ፣ በወቅንና በመሳሰሉት በሁሉም ግንባሮች ደመከልብ ሆነው ቀርተዋል፡፡ ቀሪው ኃይልም በሚገባው ልክ በጀግኖች እየተመታ ይገኛል።

የወገን ኃይል በአውደ ውጊያ ግንባሮች ከሚያስወነጭፈው የሞት ማዕበል የተረፈው የታጣቂ ቡድን በሁሉም ግንባሮች በሽሽትና መውጫ አጥቶ ላይና ታች በማለት ላይ ይገኛል፡፡

የዚህ ሽሽታቸውና አቅጣጫ የመቀያየር የማደናገሪያ ከንቱ ዘዴ የመቀበሪያ አድራሻቸውን ለመቀየር ያስችላቸው ካልሆነ በስተቀር በደረስንባቸው ቦታዎች ላይ ግን ከመቀበር የሚያስጥላቸው አይደለም፡፡ ግባችን እነሱን ማሯሯጥ ሳይሆን በተገኙበት ሥፍራ ሁሉ እስትንፋሳቸውን ማቋረጥ ነውና።

ይህን የማያወላዳ እርምጃችንንም በተግባር ስለሚያውቁት የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች በአሁኑ ሠዓት በሽሽት የመልስ ጉዟቸው የሚያቋርጡባቸው ቦታዎችና አካባቢው ሁሉ አርሶ አደር እና ወጣቶች ራሳችሁን ለመከላከል በሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች ላይ ተገቢውን ቅጣት በመስጠት “መውጣት” እንደ መግባት የቀለለ አለመሆኑን ልታስተምሩ ይገባል፡፡

ለዚህ ጀብድ አብነት ይሆኑ ዘንድ በሠቆጣ ግንባር ተከዜን ተሸግሮ ወደ ዋግ ለመግባት በሞከረው የትህነግ ሽብርተኞች ላይ የዋግ አርበኞች ግንባር ግንባሩን እየነደሉ የተከዜ ወንዝ ሲሳይ እያደረጉ መሆኑን አስታውሱ፡፡

አሁንም ቢሆን አሸባሪውን ቡድን በመደምሰስ ላይ ያነጣጠረው ፍልሚያችን በሰሜን ወሎ በኩል ውርጌሳ፤ ሊብሶ፤ ማህል አምባና ሲሪንቃ ላይ ጀግናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፤ የአማራ ልዩ ኃይል፤ ሚሊሻ እና ፋኖዎቻችን አይቀሬውን ድል አድራጊነታችንን በአጭር ግዜ ውስጥ ለማረጋገጥ ቀን ከሌሊት እየለበለቡት ይገኛሉ፡፡ በሰሜኑ ግንባርም ተመሳሳይ ጀብድ እየተፈፀመ ይገኛል።

የወገን ጦር በአሸባሪው የትህነግ ታጣቂዎች ላይ እየሰነዘረ የሚገኘው እንደወላፈን የሚለበልብ ክንድ እንኳንስ ሥጋ ለባሽ የሆነ አሸባሪውን ቀርቶ፤ እሳት እራሱ ተዳፍኖ ከመጥፋት ውጭ በእሳትነት ፍጥረቱ ለአፍታ ያህል እንዳልቆየ በአማራ ሰማይ ላይ ከሚንሳፈፉት ጭልፊቶችና ከኢትዮጵጵያ አየር ኃይል ንስሮች የበለጠ ማን ሊናገር ይችላል..??…ማንም!!፡፡

ድል ለኢትዮጵያ !!!
ድል ለአማራ !!!

Leave a Reply