የገቢዎች ቢሮ ደረሰኝ ብቻ በመሸጥ መንግስት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሱ አካላት በቁጥጥር ስር ዋሉ

አገልግሎት ሳይኖራቸው ደረሰኝ ብቻ በመሸጥ መንግስት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደደረሱ አካላት በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

ከዚህ ቀደም እቃ ወይም አገልግሎት ሳይኖራቸው ደረሰኝ ብቻ በመሸጥ መንግስት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ ነው በሚል ጥቆማ ቀርቦባቸው እና መረጃ ተሰባስቦባቸው የቆዩ ድርጅቶች ላይ በተከናወነው ኦፕሬሽን ተጠርጣሪዎቹ ሲጠቀሙባቸው የነበሩ ሁለት የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያዎች፣ በሁለት ደረሰኞች ብቻ 29 ሚሊየን 940 ሺህ 135 ዋጋ ያለው ደረሰኝ ሲሸጡ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በተሰራ ኦፕሬሽን እጅ ከፍንጅ ሊያዙ ችለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ለህገ-ወጥ ተግባሩ የሚጠቀሙበት ፕሪንተር፣ ኮምፒውተር፣ የተለያዩ ሰነዶች፣ በድርጅቱ ስም እና በተለያዩ ድርጅቶችና ግለሰቦች ስም የተዘጋጁ 16 ማህተሞች ሊያዙ ችለዋል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘም ሶስት ተጠርጣሪዎች ተይዘው ፖሊስ ምርመራ እያካሄደባቸው እንደሚገኝ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Leave a Reply