መከላከያ የሙትና የቁስለኛና ምርኮኛ ቁጥር ይፋ አደረገ ” ይቀፋል፣ መነገር ስላለበት እንናገራለን”

በ3 ክፍለ ጦሮች የተደራጀው ይህ የአሸባሪ ኃይል ሰሞኑን በተደረገ ውጊያ ከ5 ሺ 600 በላይ ሙት ከ2 ሺ 300 በላይ ደግሞ ቁስለኛ ሲሆኑ ፣ 2 ሺ አባላቱ ተማርከው ቀሪዎቹም ተበታትነውበታል። በጋሽና ግንባር በከ4 ሺ 100 በላይ ሙት ከ2 ሺ300 በላይ ደግሞ ቆስለዋል ። ቀሪዎቹ ጦርነቱን መቋቋም አቅቷቸው በሽሽት ላይ ናቸው።

ሌተናል ጄነራል ባጫ ደበሌ ” ይቀፋል” ነው ያሉት። አሸባሪው ትህነግ በሶስት አቅጣጫ ያሰለፈው ጦር ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን ሲናገሩ “ያሳዝናል። ግን መነገር ስላለበት እንናገራለን” ሲሉ ግልጸዋል። አየር ሃይል የቁስለኛ ማጠራቀሚያ ውስጥ ዘልቆ ገብቶ የፈጸመውንም ከገለጹ በሁዋላ የትግራይ ወጣቶች ህይወትና ቤተሰቦቻቸው የደረሰባቸውን ጉዳት ጠቁመዋል።

የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር “ነጻ አወጣዋለሁ ከሚለውና በስም ከማይወክለው ሕዝብ ክልል ወረራ ሲፈጸም በምን ያህል መጠን ሰራዊት ነበር?” በሚል በርካቶች ሲያነሱ ለነበረው ጥያቄ ምላሽ በሚሆን መልኩ ሌተናል ባጫ እንዳመለከቱት ወደ አማራ ክልል የዘለቀው የትህነግ ሃይል አራት ኮሮች ነበሩት። በአራቱ ከ1500 እስከ 200 የሚደርስ ቁጥር ያላቸው ዘጠኝ ክፍለጦሮች ተዋቅረዋል። አንደኛው ተጨማሪ ሃይል ከሱዳን የሚወረወርና “ከሃጂ በተባሉት ጀነራል የሚሰለጥንና የሚመራ ነው።

በጀነራል ምግበይ የሚመራው አርሚ አንድ ተብሎ የሚጠራው ሃይል ሙሉ ለሙሉ መደምሰሱን ሌተናል ጀኔራል ባጫ ደበሌ አስታወቀዋል። ይህ ሃይል ሁመራን ነጻ በማድረግ ከሱዳን አስፈላጊውን ሁሉ ለማስገባት ታቅዶ የተሰለፈ ሃይል ነበር።

ሌተናል ጄነራል ባጫ ደበሌ የሰራዊቱን ግዳጅ አፈጻጸም እና ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በጀነራል ምግበይ የሚመራው እና አርሚ አንድ የሚባለው ሃይል በሁመራ አካባቢ ደባርቅ እና ዳባትን በመቁረጥ ጎንደርን ለመያዝ ቢፈልግም ሙሉ ለሙሉ ተደምስሷል። የተረፈውም ቁስለኛና ምርኮኛ ሆኗል።

አርሚ ሁለት በከሃዲው ሜ/ጀነራል ዮሐንስ ወ/ጊዮርጊስ የሚመራው ሲሆን፣ ሃይሉ በጋሸና ከክምር ድንጋይ ጀምሮ በተደረገ ውጊያ ከመከላከያ የደረሰበትን ምት መቋቋም አቅቶት፣ ሁለቱ ክፍለጦሮቹ ተድምሠውበታል።

አርሚ ሦስት የሚባለው ደግሞ በብ/ጀነራል ፍስሃ የሚመራ በሽንፋ በኩል ከቅማንት ቅጥረኛ ቡድን ጋር በመተባባር ጥቃት ቢሰነዝርም ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል። የተረፈውም እየተንጠባተበ ወደመጣበት ተመልሷል። ይህ ሃይል በተለይ የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ስራ ለማስተጓጎል ቢያስብም እቅዱ በጀግናው ሃይላችን ተደምስሷል ብለዋል፡፡

በ3 ክፍለ ጦሮች የተደራጀው ይህ የአሸባሪ ኃይል ሰሞኑን በተደረገ ውጊያ ከ5 ሺ 600 በላይ ሙት ከ2 ሺ 300 በላይ ደግሞ ቁስለኛ ሲሆኑ ፣ 2 ሺ አባላቱ ተማርከው ቀሪዎቹም ተበታትነውበታል። በጋሽና ግንባር በከ4 ሺ 100 በላይ ሙት ከ2 ሺ300 በላይ ደግሞ ቆስለዋል ። ቀሪዎቹ ጦርነቱን መቋቋም አቅቷቸው በሽሽት ላይ ናቸው።

በጥቅሉ በሶስት ግንባር አስር ሺህ በላይ የትህነግ ሰራዊት መርገፉን፣ አራት ሺህ የሚጠጉ መቁሰላቸውን፣ ከ4000 በላይ ምርኮኛ መሆናቸውን በመግለጫቸው ያመለከቱት ጀነራሉ፣” በጣም ያልተጎዱና መሄድ የሚችሉት የሚከማቹበት ቦታ ድረስ ዘልቆ በመግባት መከላከያ ጥቃት ፈጽሟል” ብለዋል። ይሁንና የጉዳቱን መጠን ለጊዜው እንዳላወቁ አመልክተዋል። ከባድ ቁስለኞችን ከሁዋላ ሆኖ ራሱ ትህነግ እንደሚገላቸው አስታውቀዋል።

የውጭ ቅጥረኞችን ጭምር በመጠቀም ኢትዮጵያን ለማፍረስ እንደተነሳ የሚነገርለትን ትህነግን የማጥራትና የመደምሰሱ ስራ ተተናክሮ መቀጠሉን ያስታወቁት ጀነራሉ፣ ድሉን በቀጣይ እንደሚያበስሩ ተናግረዋል። ህዝብ በደጀንነት እያበረከተ ላለው ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።

Leave a Reply