የእናት አገር ጥሪ ምላሽ – ከአንድ ቤተሰብ አራት ወንድማማቾች ከአርሲ

ዘይኑ ኑር፣ ታጁ ኑር፣ ቃሲም ኑር እና እዳሶ ኑር ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን ከአንድ ቤተሰብ የመጡ ወንድማማቾች ናቸው፡፡ ወጣቶቹ በአሁኑ ወቅት በብርሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና ስልጠና ትምህርት ቤት በመሰልጠን ላይ ይገኛሉ፡፡

ወንድማማቾቹ የህውሓት የሽብር ቡድን በኢትዮጵያ ግዛታዊ አንድነት ላይ የደቀነውን አደጋ ለመቀልበስ አካላዊና ስነልቦናዊ ዝግጅት ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

ሌሎች ወጣቶች የመከላከያ ሰራዊትን በመቀላቀል የኢትዮጵያን ዘላቂ ሰላም እንዲያረጋግጡ አራቱ ወንድማማቾች ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በተመሳሳይ ሳሙኤል ከበደ፣ ታርቆ ከበደ እና ዳዊት ከበደ ከደቡብ ብሔር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ጊዲዮ ዞን ገደብ ወረዳ ከአንድ ቤተሰብ የመጡ መንትያ ወንድማማቾች ናቸው፡፡ እነዚህ ሶስቱ መንትዮች በአሁኑ ወቅት በብርሸለቆ መሰረታዊ የውትድርና ስልጠና በመውሰድ ላይ ናቸው፡፡

መንትዮቹ የህውሓት የሽብር ቡድንን ለመደምሰስ ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

በሰለሞን ጸጋዬ

EBC

See also  የአማራ ክልልን የትጥቅ ትግል የሚመሩት ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ " ኢትዮጵያ የአማራ ብቻ ናት" ማለታቸው ቁጣን አስነሳ

Leave a Reply