«የአፋር ልዩ ሀይል ሚሊሺያና ህዝባዊ ሰራዊት ጁንታውን ከኡዋ ወረዳ በማስወጣት ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር አድርገዋል»

የአፋር ልዩ ሀይል ሚሊሺያ እና ህዝባዊ ሰራዊት ጁንታውን ከኡዋ ወረዳ በማስወጣት ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር አድርገዋል።

የህወሀት ጁንታ በፈንቲ ረሱ ያሎ በኩል ድንገተኛ ወረራ በማካሄድ ንፁሀንን በመጨፍጨፍ ወደ አፋር ክልለ ሰርጎ መግባቱ ይታወቃል። ሰርጎ ከገባም በኋላ ህዝብ ውስጥ በመመሸግ የቆየ ሲሆን የአፋር ልዩ ሀይል ሚሊሺያ እና ህዝባዊ ሰራዊት እና የሀገር መከላከያ ሰራዊት በጋራ በመሆን ካለበት እንዳያልፍና ጥበባዊ በሆነ መንገድ ህዝብ ሳይጎዳ ጁንታውን ለማስወጣት ትግል ሲደረግ ቆይተል።

በዚህ ሂደትም በዛሬው ዕለት የአፋር ልዩ ሀይል ሚሊሺያ እና ህዝባዊ ሰራዊት ጁንታውን ከኡዋ ወረዳ ሙሉ በሙሉ በማስወጣት ወረዳው ከወራሪው አሸባሪ የህወሀት ጁንታ በማስወጣት በአፋር ቁጥጥር ስር ሆኗል።

የህወሀት ጁንታ በማይሆን ስሌት ለአፋር ህዝብ ያነሰ ግምት ይዞ ቢነሳም ወረራ ባካሄደባቸው ሁሉም ግንባሮች ከባድ የሆነ ሽንፈትና ትልቅ ኪሳራ እየገጠመው ነው።

የአፋር ህዘብና መንግስት አሁንም ቢሆን ወራሪውን ሀይል ሙሉ በሙሉ ከክልሉ ወሰን ጠራርጎ ለማስወጣት ጥበብ በተሞላበት መልኩ ትግሉ የሚቀጥል ይሆናል።

ፍፁም ሰብአዊነት የማይሰማው ፣ ኢትዮጵያዊነት ፈፅሞ የማያውቀው አሸባሪው ህወሀት ሀገርን ለማፈራረስ ከተለያዩ የውጭና የውስጥ ሀይሎች ጋር ተባብሮ እየሰራ ቢገኝም ለወራሪ ሀገሩን አሳልፎ መስጠትን የማያውቀው የአፋር ህዝብ የሽብር ቡድኑን እየመከተ እና እያጠቃ በትግራይ ክልል ላሉ ወንድም የትግራይ ህዝብም ሰብአዊ ድጋፍ እንዲደርስ ጥረት እያደረገ መሆኑ ይታወቃል።

አሸባሪው የህወሀት ጁንታ ከአፋር ወሰን አንድ ስንዝር ውስጥ እሳከለ ድረስ የአፋር ልዩ ሀይል ሚሊሺያ እና ህዝባዊ ሰራዊት አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ በግድ ከክልሉ ወሰን እንዲወጣ የሚደረግ ይሆናል።

በአፋር ክልልም የሚኖሩ የትግራይ ህዝቦች እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ መብታቸው ተከብሮ፣ ግዴታቸውን እየተወጡ በሰላም እየኖሩ መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም ይህ እኩይ ቡድን ለትግራይ ህፃናት ያልራራ ለማንም የማይራራ በመሆኑ የተግራይ ህዝብም ከማንም በበለጠ ተጎጂ በመሆኑ በቃቹህ ሊል ይገባል።

See also  የሽብርተኞቹ የህወሓት እና ሸኔ ቡድን አባላት ንብረት ታገደ፤ የጀነራሎቹ ስም ተዘርዝሯል

Afra regional communication office

Leave a Reply