የኮይሻ ፕሮጀክት “ሀላላ ክላስተር” በአካባቢው የሚፈጥረው ዕድል

በዳውሮ ዞን የገበታ ለሀገር ኮይሻ ፕሮጀክት ሀላላ ክላስተር እየተሰራ ያለው ፕሮጀክት የንጉስ “ሀላላ” የመከላከያ ድንጋይ ካብ በዓለም እንዲተዋወቅ ትልቅ እድል እንደሚፈጥር የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ተክሌ በዛብህ ገለጹ፡፡

ዋና አስተዳዳሪው ፕሮጀክቱ አከባቢውን በሀገር አቀፍ ደረጃ ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ ከማድረግ ባሻገር ለበርካታ ስራ አጥ ወጣቶች የስራ እድል የሚፈጥር ስለሆነ መላው የዳውሮ ህዝብ የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው አሳስበዋል።

የፕሮጀክቱ ማናጀር ኢንጂነር በላይነህ ተክለማሪያም በክላስተር ግንባታ ባለአምስት ኮከብ ሌግዠር አለም አቀፍ ሎጅና ሁለት ፕሬዝደንሻል ቪላ ቤትን ጨምሮ በርካታ ግንባታዎች በፍጥነት እየተገነባ መሆኑን ገልጸው፣ ከውጭ በሚገቡ እቃዎች ላይ መስተጓጎል ካልተፈጠረ ፕሮጀክቱ በ9 ወራት ይጠናቀቃል ብለዋል።

የዞኑ የብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ መንግስቱ መኩሪያ በበኩላቸው፣ ፕሮጀክቱ የለውጡ መንግስት ውጤት መሆኑን ገልጸው፣ ለፕሮጀክቱ የሚደረገውን ድጋፍ በማጠናከር የፕሮጀክቱን አኩሪ ታሪክ ማስቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል።

የዳውሮ ዞን ምክር ቤት አፌ ጉባኤ ፀሐይ ገሉ ፕሮጀክቱ ከዳውሮ ህዝብ አልፎ መላው የኢትዮጵያ ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሀገራዊ ፕሮጀክት ስለሆነ የዞኑ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል።

በፕሮጀክቱ ጉብኝት የዳውሮ ዞን ምክር ቤት አባላት፣ የክልል፣ የዞንና የወረዳ የመንግስትና የብልፅግና ፓርቲ የስራ ኃላፊዎችና የሚዲያ አካላት መሳተፋቸውን ከዞኑ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ (walta)

DONATE US – ቢረዱን አስፍተን ለመስራት አቅም ይፈጥሩልናል

About topzena1 2657 Articles
A journalist

Be the first to comment

Leave a Reply