በሰሜን ጎንደር የጅምላ ጭፍጨፋ ተፈጸመ፤ 120 በላይ ተገለዋል

የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር ትህነግ በሰሜን ጎንደር ዳባት ወረዳ ጭና ተክለሃይማኖት በነሃሴ 26ና 27 ሁለት ቀን ብቻ ከመቶ ሃያ በላይ ንጹሃንን መጭፍጨፉ ከአካባቢው መረጃ እየወጣ ይገኛል። ትህነግ ለምን ጭፍጨፋውን እንደፈጸመ መረጃዎቹ እስካሁንዝርዝር አላቀረቡም። ይሁን የቀብር ስፍራዎችን በፎቶ ማስረጃ ይፋ እየሆኑ ሲሆን፤ በጅምላ የተጨፈጨፉት ወገኖች ማንነት እየተለየ መሆኑ ታውቋል። ትህነግ የአማራና የአፋር ክልልን ከወረረ በሁዋላ በርካታ የጅምላ ጭፍጨፋና የነብስ ወከፍ ግድያ መፈጸሙ ይፋ እየሆነ ነው።

ዛሬ በጭና ተፈጸመ ስለተባለው ጭፍጨፋ በበቂ ደረጃ መረጃ እየተሰበሰበት መሆኑ ተሰማቷል። በቲውተር መረጃዎች መሰራጨት ከጀመሩ በሁዋላ ክልሉ የሚከተለውን በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በኩል ገልጿል። እንዳለ አቅርበነዋል።

“አረመኔውና ጨፍጫፊው ትህነግ በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ ጭና ተክለኃይማኖት ቀበሌ ከ100 በላይ ንፁሃንን ጨፍጭፏል” አቶ ግዛቸው ሙሉነህ የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ያስተላለፉት መልዕክት። “የጀግኖቻችንን የተቀናጄ ጥቃት ሲቀምስ፣ በየጫካው እየተፋለሙት ያሉትን ጀግኖችን መቋቋም ያልቻለው ወራሪ በየቤታቸው የነበሩ አዛውንቶችን፣ ህፃናትንና እናቶችን በያሉበት መንደርና ሰፈር በመግባት፣ ቀሳውስትን ቤተ ክርስትያን ውስጥ ገብቶ የፍጥኝ በማሰር ከ100 በላይ ንጹሃንን ጨፍጭፏል። የትግራይ ወራሪ ቡድን ቀደም ሲል በሰሜን ወሎ፣ በአፋር ክልል የፈፀመውን አይነት ዘግናኝ ጭፍጨፋ በሰሜን ጎንደር በዳባት ወረዳ በጭና ተክለኃይማኖት ቀበሌ በድጋሜ ፈፅሟል። ይህ ሰይጣናዊ ቡድን ከወረራቸው አካባቢዎች በአፋጣኝ ግብዓተ መሬቱ እስካልተፈፀመ ድረስ ሌሎች ጭፍጨፋዎችን እንደሚፈፅም ግልፅ ነው። በጥላቻ የናወዘውና ጭፈጨፋን የዕለት ተዕልት ተግባሩ ካደረገው የትግራይ ወራሪ አድማስ የነካ በደል፣ ሰቆቃና የግፍ ፅዋ ሕዝባችንን ለመታደገ ፍጥነታችንን ጨምረን ማርሻችንን ቀይረን ከያለበት ግብዓተ መሬረቱን በመፈፀም ሕዝባችን ልንታደግ ይገባል። ሚዲያዎቻችንም ይሄንን እውነት ዓለም እንዲያውቀውና ከወራሪውና ጨፍጫፊው ጋር በምናደርገው ትግል አብረውን እንዲቆሙና ድርጊቱንም እንዲያወግዙት በፍጥነት መዘገብና ቦታው ድረስ በመሄድም ሁኔታውን ማስረዳት ይገባናል። በንፁሃን ወገኖቻችን ላይ የደረሰው አሰቃቂ ጭፍጨፋ የትግራይን ወራሪ ቡድን ግብዓተ መሬቱን በማፋጠንና ለሕዝባችን ዳግም ስጋት እንዳይሆን በማድረግ ደማቸውን እንደምንመልስ ጥርጥር የለውም። የትግራይን ወራሪ ኃይል ከየገባበት እየመታን ባለንበት ወቅት የቤተሰብና የወገንን ሀዘን የምንጠግነው በትግራይ ወራሪ ኃይል መቃብር ላይ ይሆናል!!!!

READ MORE STORIES

Related posts:

ደብዳቤ ለኢትዮጵያ - ከቢልለኔ ስዩም
የዓለም ባንክ የ300 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ፈረመ
"እናቴ ፍጹም እስር ቤት እንድትገባ አልፈግም" ብሎ እግሩን ያጣው ወጣት ምስክርነት ለሮይተርስ
"አልዘምትም" ወይም "ከጠላት ጎን እሰለፋለሁ" ማለት ሲቻል ማውሰብሰብና ማድበስበስ አይገባም!
አብዱላሂ ፋርማጆ ለአዲሱን ፕሬዝዳንት «ሁሉም ወገኖቼ እንዲደግፉህና እንዲጸልዩልህም እጠይቃለሁ»
መንግስ የጸጥታ ሃይሎች ለየትኛውም ዓይነት ትንኮሳ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ
በትግራይ 5.2 ሚሊዮን ሕዝብ ዕርዳታ እየደረሰ ነው፤ ከሺህ በላይ የጭነት መኪኖች ታግተዋል፤ 76 ቢሊዮን ብር ወደ ትግራይ ተልኳል
የደህንነት ጥናት አዲሱ ምዕራፍ - ጂኦስፓሻል ኢንተለጀንስ
ዳግም ጦርነት እንዳይጀመር ስጋት የገባው ኢሰመኮ የማስጠንቀቂያ ጥሪ አሰማ
"ህሊናን የሚፈታተን" የተባለ ሪፖርት ይፋ ሆነ - አማራ ክልል በተወረረበት ወቅት ግብረርሰዶም መፈጸሙ ተገለጸ
ፊንላንድ 3.6 ሚሊዮን ሕዝብ የሚይዙ ዋሻዎች አዘጋጀች - ለኢትዮጵያውያን ጠቃሚ የጥንቃቄ መረጃ
"አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድንና የጥፋት ኃይል ዳግም ከሞከረ የማያዳግም ቅጣት ይጠብቀዋልʺ
ሻዕቢያና ትህነግ - ሰሞኑን ይህ ሆነ
ትህነግ ጦርነት እንደሚከፍት ይፋ አደረገ፤ አማራ ክልል "ለክተት ተዘጋጁ"አለ፤ መከላከያ በተጠንቀቅ ላይ ነው
ወልቃይት "የወር ስንቅህን አዘጋጅተህ ለክትተ ጥሪ ተዘጋጅ”

Leave a Reply