የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት በ800 ሚሊዮን ብር 10 የዳቦና ዱቄት ፋብሪካዎችን ለማስገንባት ስምምነት ተፈራረመ

የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት በ800 ሚሊዮን ብር 10 የዳቦና ዱቄት ፋብሪካዎችን ለማስገንባት ከሚድሮክ ኢንቬስትመንት ግሩፕ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ


የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት በ800 ሚሊዮን ብር ወጪ በ10 የሀገሪቱ ከተሞች የዳቦ እና ዱቄት ፋብሪካዎችን ለማስገንባት ከሚድሮክ ኢንቬስትመንት ግሩፕ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

ስምምነቱን ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና የሚድሮክ ኢንቬስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጀማል አህመድ ተፈራርመዋል፡፡

በሰመራ፣ ጅግጅጋ፣ ሐረር፣ ነቀምት፣ ጎንደር፣ ደሴ፣ አሶሳ፣ ሐዋሳ፣ ወላይታ ሶዶ እና ቦንጋ የሚገነቡት ፋብሪካዎቹ እያንዳንዳቸው በቀን 400 ኩንታል ዱቄት እና 300 ሺህ ዳቦ የማምረት አቅም ይኖራቸዋል ተብሏል፡፡

ለግንባታ የ1 ዓመት ጊዜ ብቻ የተያዘላቸው ፋብሪካዎቹ የከተሞቹን የዳቦ ፍላጎት ከማሟላት ባሻገር ለ1 ሺህ 200 ሰዎች የስራ ዕድል እንደሚፈጥሩ ተገልጿል፡፡ EBC

በሞላ አለማየሁ

See also  ውጊያው መቀለ አፍንጫ ስር ሆኗል ትህነግ "የአፋር ሃይል ጉዳት አደረሰብን" አለ- ውጊያው ወደፊት እየገፋ ነው

Leave a Reply