የለካቲት 11ዱ እና የወይ ፍንክች ኮፍያ አጥላቂው ግለሰብ (ገሬ) ሴራ

የኢትዮጵያ መንግስት ቀደም ብሎ የሽብር ቡድኑ በጦር ግንባር እየሞቱ ያሉ ወታደሮቹን አስክሬን በመጫን እየወሰደ መሆኑን እና በቀጣይ ለሚሰራቸው ድራማዎች መጠቀሚያ ሊያደርገው እንዳቀደ ጠቅሶ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ይህንኑ የመንግስት መረጃ ትክክለኛነት የሚያረጋግጥ ዘገባ ሲ ኤን ኤን በማንኛውም ብዙሃን መገናኛዎች ሽፋን ያልተሰጠው “በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ የትግራይ ተወላጆች አስክሬን ቀደም ሲል በተከዜ አሁን ደግሞ በሁመራ ወንዝ ዳርቻ ተጥለው በምርመራ አገኘሁ” የሚል የሀሰት ዘገባ አቀረበ፡፡

የመንግስትን የቀደመ መረጃ ትክክለኛነት ሊያረጋግጡ የሚችሉ በርካታ ጥያቄዎችን በማንሳት መሞገት የሚቻል ቢሆንም መረጃው ለሲ ኤን ኤን ብቻ እንዲሰጥ ለምን ተፈለገ? ማንስ ሰጠ? በምርመራው ላይ እነማን በእማኝነት ቀረቡ? በእነማን እንደተገደሉ የሚሳይ መረጃ ምን አለ? እና መሰል ወንጀሎችን በመፈጸም የቀደመ ልምድ እና ተሞክሮ ያለውስ ማነው? የሚሉትን አንስቶ ግልጽ ማብራሪያ መሻት የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ባህሪ ነው፡፡

በዘገባው ላይ በመረጃ ሰጪነት፣ በማብራሪያ አቅራቢነት፣ ግርፋቱን እና ግድያውን በተመለከተ በእማኝነት እና አካባቢውን ከፊት ሆኖ በመጠቆም ጭምር ሲሳተፉ የሚታዩት የአካባቢው ተወላጆች መሆናቸው ዘገባውን ተዓማኒ አያደርገውም፡፡

የሽብር ቡድኑ አባል መሆኑንም በቃለ-መጠይቁ ላይ ሲቀርብ ያጠለቀው ባርኔጣ “ለካቲት 11 እና ወይ ፍንክች” የሚል ጽሁፍ ከፊት እና ከኋላ ተጽፎበት ይታያል፡፡

ሆኖም በዚህ ድራማ ላይ በዋና ተዋናይነት የተሳተፈው ግለሰብ የህወሓት ሽብር ቡድኑ አባል እና የዚህ ድራማ አቀናባሪ ብሎም አስተባባሪ የሆነው ገሬ የተባለ ግለሰብ ነው፡፡

የዚህ ዘገባ ደራሲ እና ተዋናይ የሆነው ገሬ “በሱዳን ባህር ዳርቻ የትግራይ ተወላጆች ተገድለው ተጥለዋል” የሚል መረጃ ለጥቅም ተጋሪዋ ለሲ ኤን ኤን ጋዜጠኛ ኒማ ኤልባጊር ሲሰጥ እና ስለግርፋቱ፣ ስለአገዳደሉ አጠቃላይ ስለሁኔታው ሲያብራራ እንዲሁም ሲመዘግብ ይታያል፡፡

ገሬ የተባለው የአሸባሪ ቡድን አባል መረጃውን ከየት አገኘው የሚል ጥያቄ መጠየቅ ብሎም የሰውየውን ተሳትፎ መጠርጠር ይቻላል።

የሲ ኤን ኤን ጋዜጠኛ የምርመራ ዘገባ ያሉትን ለማቅረብ ሲንደረደር “የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ተጠያቂ ያልሆኑበትን ድብቅ ወንጀል ነው” በማለት ዘገባ እንደሰሩ አስታውሷል፤ ይህ በምን ተረጋገጠ? ሚዲያውንም በሀሰት እና ባልተረጋገጠ እንዲሁም መረጃ ባልቀረበበት ዘገባ ላይ ተመርኩዞ የቀረበ ዘገባ በመሆኑ በስም ማጥፋት ወንጀል የሚያስጠይቅ ነው።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጠቀሙ፤ https://www.ena.et/?p=143143

Related posts:

ደብዳቤ ለኢትዮጵያ - ከቢልለኔ ስዩም
የዓለም ባንክ የ300 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ፈረመ
"እናቴ ፍጹም እስር ቤት እንድትገባ አልፈግም" ብሎ እግሩን ያጣው ወጣት ምስክርነት ለሮይተርስ
"አልዘምትም" ወይም "ከጠላት ጎን እሰለፋለሁ" ማለት ሲቻል ማውሰብሰብና ማድበስበስ አይገባም!
አብዱላሂ ፋርማጆ ለአዲሱን ፕሬዝዳንት «ሁሉም ወገኖቼ እንዲደግፉህና እንዲጸልዩልህም እጠይቃለሁ»
መንግስ የጸጥታ ሃይሎች ለየትኛውም ዓይነት ትንኮሳ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ
በትግራይ 5.2 ሚሊዮን ሕዝብ ዕርዳታ እየደረሰ ነው፤ ከሺህ በላይ የጭነት መኪኖች ታግተዋል፤ 76 ቢሊዮን ብር ወደ ትግራይ ተልኳል
የደህንነት ጥናት አዲሱ ምዕራፍ - ጂኦስፓሻል ኢንተለጀንስ
ዳግም ጦርነት እንዳይጀመር ስጋት የገባው ኢሰመኮ የማስጠንቀቂያ ጥሪ አሰማ
"ህሊናን የሚፈታተን" የተባለ ሪፖርት ይፋ ሆነ - አማራ ክልል በተወረረበት ወቅት ግብረርሰዶም መፈጸሙ ተገለጸ
ፊንላንድ 3.6 ሚሊዮን ሕዝብ የሚይዙ ዋሻዎች አዘጋጀች - ለኢትዮጵያውያን ጠቃሚ የጥንቃቄ መረጃ
"አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድንና የጥፋት ኃይል ዳግም ከሞከረ የማያዳግም ቅጣት ይጠብቀዋልʺ
ሻዕቢያና ትህነግ - ሰሞኑን ይህ ሆነ
ትህነግ ጦርነት እንደሚከፍት ይፋ አደረገ፤ አማራ ክልል "ለክተት ተዘጋጁ"አለ፤ መከላከያ በተጠንቀቅ ላይ ነው
ወልቃይት "የወር ስንቅህን አዘጋጅተህ ለክትተ ጥሪ ተዘጋጅ”

Leave a Reply