ትህነግ ኢትዮጵያን ለመበተን የነደፈው አዲስ ዕቅድ ተገኘ፤ ማተራመስ፣ መከላከያን መከፋፈል፣ ድርድርን ለጊዜ መግዣ …

“የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ነኝ” የሚለውና ለግማሽ ምዕተ ዓመት በዚሁ ስም የጸናው ትህነግ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የነደፈው አዲስ እቅድ መንግስት እጅ መግባቱ ተሰማ። “አሸባሪው ህወሓት ኢትዮጵያን ለማፍረስ ያዘጋጀው ስትራቴጂክ ሰነድ የኢፕድ ታማኝ ምንጮች እጅ ገብቷል” ተብሏል።

አሸባሪው ህወሃት አገር ለማፍረስ በጸጥታ አካላት ላይ ጥቃት መፈጸም፣ ሁከትና ብጥብጥ በተለያዩ አካባቢዎች እንዲቀሰቀሱ ማድረግን ጨምሮ የተለያዩ ችግሮችን ለመፍጠር ስትራተጂ ነድፎ መንቀሳቀሱን የሚያጋልጥ ሰነድ ከቡድኑ እጅ ሾልኮ ወጣ።

የቡድኑ ጽህፈት ቤት ‘የትግል ልዩ ምዕራፍ እድገቶች እና የምከታችን ቀጣይ ስትራቴጂዎች፣ ስልቶች እና አቅጣጫዎች (ቁጥር – ሁለት)’ በሚል ርዕስ ያዘጋጀው በጥብቅ የሚያዝ ሰነድ እንዳጋለጠው ቡድኑ አገርን የማፍረስ ግቡን ለማሳካት አራት ስትራተጂዎችን ነድፎ ነበር።

ስትራተጂው በጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በአገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመው የአሸባሪው ቡድን ጥቃት ዝግጅት የተደረገበት ስለመሆኑም ያመላከተ ነው።

ለኢዜአ የደረሰው ይህ ምስጢራዊ ሰነድ አሸባሪ ‘ጠላት’ ብሎ የፈረጀውን የለውጥ መንግስት ለመጣል ዝግጅት ስለማድረጉም በግልጽ አስቀምጧል።

ተነሳሽነትን ጨምሮ የጠላትን ወታደራዊ ሚዛን አንገዳግዶ/አዛብቶ የሚንድ ስትራቴጂን ጨምሮ የተቀናጀ ፖለቲካዊ ጥቃት እንደ ቁልፍ ስትራቴጂ፣ በትጥቅ የታገዘ ህዝባዊ አመጽ እና ሁከት/ ብጥብጥ እንዲሁም ድርድር እንደ ጠላት ማሰናበቻ ስትራቴጂ ብሎ ተዘጋጅቶ ሲንቀሳቀስ እንደነበር ይፋ ሆኗል።

‘ተነሳሽነትን ጨምሮ የጠላትን ወታደራዊ ሚዛን አንገዳግዶ/አዛብቶ የሚንድ ስትራቴጂ’ ብሎ በነደፈው ስትራተጂ መሰረት ለዓመታት ሲጠብቀው በኖረው የአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ክህደትና ጥቃት በመፈጸም መተግበሩ ይታወሳል።

በዚህ ስትራተጂው “ጠላትን ለማሰናበት/ለማጥፋት በሚደረገው ርብርብ ተነሳሽነትን ያካተተ ወታደራዊ ስትራቴጂያዊ ማዛባትን /ማንገዳገድን እና ማጥቃትን (ስትራቴጂክ ኦፌንሲቭ) እንዲሁ እንደ ጠቃሚ ስትራቴጂ መውሰድም የግድ ይሆናል” ብሏል፡፡

የተቀናጀ ፖለቲካዊ ጥቃት ስትራተጂው ደግሞ የሴራ ገመድ በመግመድ አገር እንዳትረጋጋ ሲያደርግ መቆየቱን አመላክቷል።

“በተወሰነ ኪሳራ ድልን ለመጎናፀፍ የሚያስችል አደረጃጀት፣ የሰው ሃይል እና ሀብት ስምሪት ማስተካከያዎችን በማድረግ” የሚለው ሰነድ የአሸባሪውን ህወሃት ሴራ አጋልጧል።

በትጥቅ የታገዘ ህዝባዊ አመጽ እና ሁከት/ ብጥብጥ ማስነሳት የሚል ስትራተጂ የነደፈው ቡድኑ፤ የለውጡ መንግስት ተገዶ ስልጣኑን እንዲያስረክብ አልሞ እንደነበር ገልጿል።

See also  ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሚሚ አለማየሁ የትዊተር የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ሆና ተመረጠች

‘ድርድር እንደ ጠላት ማሰናበቻ ስትራቴጂ’ በሚል ያስቀመጠው አገር የማፍረሻ ስትራተጂ ቡድኑ እኔ ያልገዛኋት ኢትዮጵያ ትፍረስ የሚለው አቋሙን ያጋለጠ ሰነድ ሆኗል።

“በበኩላችን ይህንን የትግል አግባብ ተጠቅመንም ቢሆን ጠላትን የምናንበረክክበት ጠቃሚ መሳሪያ አድርገን በስፋት ልንሰራበት የሚገባን ነው” ያለው ሰነዱ፤ የሰላም እና ሀገር የማዳን ጥሪ በሚል ማደናገርን አንድ ስልት አድርጎ እንደሚጠቀምበት የአሸባሪው ቡድን በስትራተጂው አመላክቷል።

“በመሰረታዊ ጉዳዮች ማዕቀፍ ውስጥ ሆነን ከሁኔታዎች ጋር የሚተጣጠፍ የድርድር ስትራቴጂ መታገያችን ነው” ብሏል በሰነዱ፡፡

Leave a Reply