ወታደር የሌለው ጄነራል አይኖረውም❗”ፀሀይ መማር ትወዳለች” የልጆች ፊልም በኩል አጭር ሙቪ ላዘጋጅልህ

በየበረሀው የሚዋደቀውን ሰራዊት በመተቸት ለህዝቡ ከእሱ በላይ ተቆርቋሪ መስሎ ለመታየት የሚሞክሩትን ታዝበናል።በየአውደ ግንባሩ የሂዎት እና የአካል ዋጋ እየከፈሉ ያሉ ወታዶሮችን ለማጠልሸት የሚሞክረውን የሰፈር አውደልዳይ በያዘው ከዘራ ግንባሩን ብሎ የሚጥል ጎበዝ እንዴትስ ጠፋ ብለን ጠይቀናል?!

“እነ አቶ ወንዳፍራሽ ቄዬ ምንም ወታደር ደርሶ የማያውቀው እሳቸው እንደ ሁለተኛ ዜጋ ተቆጥረው ነው ወይ?!!! ጋሽ አያ እከሌ መንደር ጁንታው ሲገባ ሰራዊቱ የማንን ጎፈሬ እያበጠረ ነበር?! የቄስ አጥናፉ ፍየል በጠራራ ፀሀይ በጁንታው ስትታረድ! የወይዘሮ ስንቄ ጭር ያለች ዶሮ እንቁላሎቿ ተጠብሰው ሲበሉ ሰራዊቱ ያልደረሰላቸው!እነሱ ምን ሀጢያት ቢሰሩ ነው?! አየር ሀይሉ ውጊያውን እርግፍ አድርጎ ትቶ የመንገደኞች መጓጓዣ አገልግሎት መስጠት ጀምሮ ይሆን?! ወረዳችን ሲታመስ ያልደረሰው?!ዱሮኗ የማንን የሙዚቃ ቪዲዮ እየቀረፀች ዘገየች?! ወይስ እኛ ቀበሌ ብትመጣ አዙሮ ይጥላታል?! “አይነት ትችት ይሰነዝራል።

“በአስራ አምስት ቀን መቀሌን የተቆጣጠረው ጦር ጁንታው ከተቆጣጠራቸው አንዳንድ አከባቢዎች ጠራርጎ ማሶጣት አልቻለም!!” የሚሉ ደፋሮች በየ ገፆቻቸው ፅፈውም አንብበናል።

በጣም አስገራሚው ደሞ እሄን የሚሉት ወጣቱ ወደ ተቋሙ እንዳይቀላቀል ከሁለት ሶስት አመታት በፊት በማጥላላት ዘመቻ ለይ ተጠምደው የነበሩ ናቸው። የጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ “ሀገሪቷ ያላት ጦር መቶ ሚሊዮን ህዝብ በሚመጥን ደረጃ አይደለም!” በማለት በህዝብ ተዎካዮች ምክር ቤት ተናግረው ነበር።
በወቅቱ እነዚህ ሰዎች በዚህ ደረጃ መልዕክቱ ሲተላለፍ ችግሩ ግዙፍ በመሆኑ ነው ብለው ከመረዳት ይልቅ ” እንዴት የሀገር ሚስጥር በዚህ መልኩ ይነገራል? “ማለታቸውን ዘንግተውታል።

አንዳንድ ጂሎች ደሞ አሉ። ሰራዊቱ ከሁመራ ተነስቶ መቀሌ እስኪገባ ድረስ እንደ አዲስ አበባ አዳማ የፍጥነት መንገድ ጉዞ ሽው ብሎ የሄደም ያደርጉታል። መቀሌን በአስራ አምስት ቀን ስንቆጣጠር ጓዶቻችን እየተሰው እየቆሰሉ የአካል ዋጋ እየከፈልን መሆኑን ነጋሪ ይፈልጋሉ።ከሁመራ መቀሌ ከመቀሌ ተንቤን የነበረው ሂደት ከሙሽራው ወደ ሙሽሪት ቤት የሚደረግ ጉዞ አይነት ይመስላቸዋል።በአጀብ በክላክስ አደባባይ ባገኘን ቁጥር ሁለት ሶስቴ እየተሽከረከርን የተጓዝን!

በፓርላማ ሳይቀር የሰራዊቱ ቁጥር አነስተኛ ነው ተብሎ የተነገርህን አስታውስ።ከዚህ በዃላ የተካሄዱትን እልህ አስጨራሽ ጦርነቶች ተገንዘብ።በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ብቻ ሳይሆን በሌሎች የሀገራችን አከባቢዎች ጦርነቶች መኖራቸውን ልብ በል! መንግስት የህልውና ዘመቻ በመሆኑ ክተት ሰራዊቱን ልዩ ሀይሉን አጠናክር ሲልህ ምን ማለት ፈልጎ እንደሆነ ተረዳው።በዚህ መልኩ ተነግሮህ መረዳት ካልቻልክ አልገባኝም በለኝ እና በቀጣይ በሚመጥንህ “ፀሀይ መማር ትወዳለች” የልጆች ፊልም በኩል አጭር ሙቪ ላዘጋጅልህ።

ለማንኛውም ዛሬ የተፈጠረው ነገ እንዳይደገም የፀጥታ ተቋሞቻችንን እናጠናክር።ከዚህ ባለፈም ወደፊት ጄነራልነቱን ሁሉ በአንድ ብሄር ሞላው ብለህ በለመደብህ የለቅሶ ፖሎቲካ ላለማላዘን ዛሬ ልጆችህን መርቀህ ላክ።ተረኞች ባንኩንም ታንኩንም ያዙት ብለህ እየተብሰከሰክ እድሜ ልክህን በቅናት እንቅልፍ ላለማጣት ወጣቶችህ ተቋሙን እንዲቀላቀሉ መክረህ ገፅፀህ ሸኛቸው።

ከአሁን በዃላ በእውቀት በአገልግሎት በልምድ እንጂ እንደወያኔ ስርአት በብሄር አስተዋፆ የሚሰጥ ማዕረግ የለም።
➻ወታደር የሌለው ጄነራል አይኖረውም❗”

Zerihun Nuri Abote Fb

Leave a Reply