ባይደን በኢትዮያ ሕዝብ ላይ ፈረዱ፤በውጭ ሃብት ያካበቱ የትግራይ ተወላጆች ሃብታቸው አደጋ ላይ ወድቋል

ጆ ባይደን ዛሬ በፈረሙት የትዕዛዝ ደብዳቤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እንደፈረዱ የተረዱ እንደማይመስላቸው፣ ትዕዛዙ በውጭ አገር ሃብት ያካበቱ የትግራይ ተወላጆችን የሚጎዳና ሃብታቸውን የሚያስነጥቅ እንደሆነ የህግ ባለሙያ ለኢትዮ12 ገለጹ።

ደብዳቤን ” ለሎቢስቶች ሲባል የተሰራ የድል ዜና” ሲሉ የገለጹት የህግ ባለሙያው ባይደን ራሳቸውን በራሳቸው መቃረናቸውን አስታውቀዋል። በትዕዛዙ ላይ ጦርነቱ እንዲባባስ፣ በመሳተፍ፣ ሎጂስቲክ በማቅረብ፣ ደጀን በመሆን፣… ወዘተ ተሳትፎ ያላቸው በሙሉ ቅጣት እንደሚጣልባቸው ተመልክቷል። በተዘረዘሩትና በሌሎችም ተግባራት ከጦርነቱ ጋር ንክኪ ያላቸው በአሜሪካ ንብረታቸው እንደሚነጠቅና ቪዛ እነሚከለከሉ ይገልጻል። “የኢትዮጵያ ሕዝብ ጦርነቱን ይደግፋል። ልጁን መርቆ ይልካል። ገንዘብ ያዋጣል። በደጀን ሆኖ ስንቅ ይሰጣል። ከዚያም በላይ ራሱ ይዘምታል። ባይደን እንግዲህ የፈረዱት እዚህ ሁሉ ህብብ ላይ ነው” የሚሉት የህግ ባለሙያ ” ባጭሩ ባይደን ዲቪ ከልክለዋል” ቢባል ይቀላል ብለዋል።

ጉዳዩ አዲስ መንግስት ሳይመሰረት የሚደረግ ሩጫ ሆኖ እንደሚሰማቸው ያመለከቱት የህግ ባለሙያ ” አዲስ መንግስት ከተመሰረተና ፓርላማ አዲስ ውሳኔ ከወሰነ፣ ውሳኔ የህዝብ ሆኖ ይጻናል። ስለዚህ ጸባቸው በገሃድ ከህዝብ ጋር ይሆናል” ሲሉ የድርድር ጫና የተፈጠረበትን ምክንያት ይገልጻሉ። አክለውም የኬረን ባስ ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ውስጥ ብዙ ጉዳይ እንደሚኖር አመልክተዋል። ባስ የኢትዮጵያ መንግስት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ሊያነጋገሯቸው እንደፈቀዱና በቅርብ ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጡ ቴዎድሮስ ተሾመ ባነጋገራቸው ወቅት ማረጋገጣቸው ይታወሳል።

ኦባማ በስርዓት ለውጥ ሰበብ ሊቢያን እንዳወደሙ በማስታወስ ባይደን ውሳኔያቸውን ባስቸኳይ እንዲከልሱ፣ የኢትዮጵያንም ሉአላዊነት እንዲያከበሩ ላውረንስ ፍሪ ማን አስጠንቀቅዋል።

ቫን ባተን የሚባለው የትህነግ የህዝብ ግንኙነት ስራ ወኪልና ወስዋሽ ” የትግራይ ልጆች አትረበሹ ” ሲል ኬረን ባስ ከሌሎችም ኢትዮጵያዊያን ጋር ቢነጋገሩም አቋማቸውን እንደማይቀይሩ በቲውተር ገጹ ማስፈሩ ያታወሳል። ዛሬም ባይደን ዋይት ሃውስ ያሰራጨውን የባይደን ትዕዛዝ ተከትሎ ” ኳሱ በጠቅላይ ሚኒስትሩ እጅ ነው” የሚል ሃሳብ አሰራጭቷል።

See also  አማራ ክልል "ተወረሩ" ያላቸውን ስፍራዎች እያስለቀቀና እያጸዳ መሆኑንን አስታወቀ

መንግስት ሙሉ ካቢኔው፣ ክልሎች፣ ፓርላማው፣ የፓርቲው አባላትና ሕዝብ በተደጋጋሚ በአንድነት “የደገፉት የህግ ማስከበር ዘመቻ” አግዘዋል። ወይም ደጀን ሆነዋል። ወይም ስንቅ ሰጥተዋል … በሚል አሜሪካ መቶ አስር ሚሊዮን ሕዝብ እንዴት ልትወነጅል እንደምትችል የህግ ባለሙያው እንደማይገባቸው አስታውቀው ” ትዕዛዙ የኢትዮጵያን ህዝብ አይመለከትም ወይም ለመጉዳት አይደልም” ምን ለማለት ተፈልጎ እንደሆነ እንደማይገባቸው አመልክተዋል። አክለውም ኢትዮጵያ ባንክ ባለ የራሷ ገንዘብ ግብይት እንዳትፈጽም መታገዷን በማንሳት ባይደንን ” ካረጁ አይበጁ” ሲሉ ሁሉንም ጉዳይ በእውቂያ ስለመስራታቸው ጥርጣሬ እንዳላቸው አመልክተዋል።

የመንግስት፣ የአማራ ክልል፣ የኤርትራና የትግራይ ባለስልጣናትና የጦር አመራሮችን እንደሚወነጅል ያሳሰበው ደብዳቤ፣ አሁን ስልጣን ላይ ካሉት የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ይልቅ በሃብት እግድና ወረሳ ረገድ የትህነግ ደጋፊ ዲያስፖራዎችን፣ እንዲሁም በውጭ አገር የትህነግን ንግድ ድርጅቶችን የሚመሩና ራሳቸው ሃብት ያላቸው ባለስልጣናት እንደሚጎዳ ጠቁመዋል።

አቶ አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ አሁን ስልጣን ላይ ያሉት የአማራ ክልል ባለስልጣናት በውጭ አገር ያከማቹት ሃብት ይኖራል ብለው እንደማያስቡ፣ የኤርትራ ባለስልጣናትም ቢሆኑ አሜሪካ አገር ሃብት እንደሌላቸው ያመላከቱት የህግ ባለሙያ፣ ማን እንደሚጎዳ ወደፊት የሚታይ ይሆናል ብለዋል። የወጣው የባይደን ትዕዛዝ ከአዲስ መንግስት ምስረታ በፊት እሽቅድምድም የተያዘ መሆኑንን አመልክተዋል።

የባይደን ውስኔ አሜሪካ እንደ ልማድዋ በአንድ አገር የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የመግባትና የማፈራረስ ውጤት ማስመዝመዝገብ በመሆኑ ጉዳዩ በቀላል የሚታይ እንደማይሆን በርካቶችም እያሳሰቡ ነው።

ሕዝብ ከትህነግ ጋር ድርድር ሊደረግ እንደማይገባ በስፋት ይወተውታል። ድርድርም ካለ መከላከያን ያረዱና ያሳረዱ ቅድሚያ ለህግ እንዲቀርቡ መደረግ እንደሚገባቸው ህዝብ ያምናል። በይግራይም ሆነ በአማራና አፋር ክልሎች ነጹሃን ላይ ግፍ የፈጸሙ በህግ እንዲጠየቁ ሳይደረግ ወደ እርቅ መመለስ ከባድ እንደሆነ የሚያምኑ ያሉትን ያህል ጦርነቱ ቆሞ ገለልተኛ አጣሪ ኮሚሽን እንዲመረመረው የሚጠይቁም አሉ።

ከትህነግ በኩል አሁን ደርጅቱን እየመሩ ያሉ፣ ጦርነቱን የሚያስፈጽሙ እንዲሁም የበላይ መኮንኖች ጉዳይም ሌላው በህግ የሚታይ መሆኑ እርቁን ያወሳስበዋል የሚሉ ልምድ ያላቸው፣ ዕርቅ በራሱ ሂደት በመሆኑ አንድ ቦታ ላይ ሊጀመር እንደሚገባው ያሳስባሉ።

See also  ምዝበራ የጎላባቸው የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ይፋ ሆኑ፤ 4 ቢሊዮን ብር ያህል ባክኗል

Leave a Reply