ትህነግ መከላከያን ሲያጠቃ አስቀድሞ 2 ሚሊዮን ሰራዊት አዘጋጅቶ ነበር፤ ዜናው በርካቶችን አስደንግጧል

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ለመጨረሻ ጊዜ የተገነባው በባድመ ጦርነት ወቅት ነው። እንደ ባዕድ እንዲበተን ከተደረገ በሁዋላ አገሪቱ ብሄራዊ ሰራዊት አልነበራትም ማለት ይቻላል። ከባድመ ጦርነት ጋር ተያይዞ ሕዝብ ሲነሳ ሰራዊቱ ዳግም ተዋቀረ። የተገፉና የተባረሩ ባለሙያዎችና ከፍተኛ መኮንኖች ዳግም ትሪ ተደረገላቸው። አንድ ዓመት ዝግጅት ተደርጎ ሰራዊቱ ተገነባ። ያለቀው አልቆ ድነበሩን በኢትዮጵያዊ ስሜት አስከበረ። ኮንቪክሽናል ጦርነት የማያውቁት የትህነግ ጦር መሪዎች መሳቂያ በሆኑበት አውድ የተጣሉት የኢትዮጵያ ልጆች የችግር ጊዜ ወርቅ ሆኑ።

ስማቸውን እንዳንገልጽ የጠየቁ የመከላከያ መኮንን እንዳሉት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ባለፉት ሃያ ሶስት ዓመታት ውስጥ በከፍተኛ የሰው ሃይል የተገነባው አንዴ በባድመ ጦርነት ወቅት ነው። ይህ ማለት ዛሬ የሰራዊቱ አብዛኛው አባላት እድሜ ሃምሳዎቹ ግድም ወይም ከዛ በላይ ነው። በሌላ በኩል ግን ትህነግ ለራሱ በጎን ሲያደራጅ የነበረው ሃይል ወጣቶችና በቁጥር ከመከላከያ በላይ የነበሩ መሆናቸው ሲነገር ” አናምንም” ለሚሉ ሁሉ ጊዜው ደርሶ ከትህነግ አንድበት መሰማቱ መልካም አጋታሚ እንደሆነ ያስረዳሉ።

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር “ነጻ አውጪ” ሆኖ 27 ዓመታት አገር ከመራ በሁዋላ በህዝብ ተቃውሞና ከውስጥ እህት ድርጅቶች ባካሄዱት ትግል መንበሩን ከለቀቀ በሁዋላ ወደ ስልጣን ለመመለስ ይረዳው ዘንዳ ያዘጋጀው ሰነድ ይፋ መሆኑ ተሰምቷል። በዚህ ሰነድ እንደተገለጸው ድርጅቱ ሁለት ሚሊዮን ሰራዊት ለስትራቴጂው አፈጻጸም እንዲረዳ አድርጎ አደራጅቶ እንደነበር ተመልክቷል።

ከለውጡ በሁዋላ ቀስ በቀስ የሰላማዊውን መንገድ በመተው የሃይልና ” ማንም ምንም አያገባውም፤ ጠያቂም ተጠያቂም የለም” ሲሉ የነበሩ አንዳንድ የተቃዋሚ መሪዎችና፣ በራሱ በመንግስት ውስጥ የነበሩ አገልጋዮች ልባቸው የሸፈተው ትህነግ ይህን ያህል ሃይል በማደራጀቱ ወደ ስልጣን ይመለሳል የሚል እምነት ስለነበራቸው እንደሆነ አስተያየት እየተሰጠ ነው። እነዚህ ሃይሎች መሃል አገር ተቀምጠው ልክ እንደ ትህነግ ቀን ቆርጠው ” መንግስት የለም” ሲሉ የነበሩ መሆናቸው ይታወሳል።

በወጉ ያልተደራጁ የተለያዩ ተቃዋሚዎችን የትጥቅ ትግል እንዲጀምሩ ማስታጠቅና ማደራጀት ከስትራቴጂዎቹ መካከል አንዱ አድርጎ የነበረው የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር፣ መስከረም 2013 እንዳዘጋጀው በተነገረለት ሰነድ መሰረት የኢትዮጵያን መከላከያ የመበተንና የማፈራረስ ዕቅድ ነበረው። መንግስት ውስጥም እጁን በማስረግ ለመፈርከስ ዝግጅት እንደነበረው ተመልክቷል።

“እንግዲህ ይህን ሁሉ ዝግጅት አድርጎ ነበር መከላከያን የወጋው፣ ከጀርባ ሆኖ ያረደው” ሲሉ መኮንኑ ይናገራሉ። ከበረሃ ዳግም ወደ መቀለ የተመለሰው ሃይል “በቅጽበት ሰፊ የአማራንና የአፋርን ክልል እንዴት ሊወር ቻለ” በሚል ለሚነሳ ጥያቄ ” የሰው ማዕበል በማጉረፍ” እንደሆነ ሲገለጽ ጉዳዩ ሚዛን እንዳልደፋ ሲተቹ ለነበሩ ወገኖች ሰነዱ ጥሩ መልስ እንደሆነ ያክላሉ። በርካቶች ይህን ሲሰሙ መደንገታቸውን አንስተው ” አሁን አልፈነዋል” በማለት መከላከያ በውስን ሃይል የከፈለውን መስዋዕትነት ያስታውሳሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በፓርላማ ንግግራቸው በተደጋጋሚ ” መከላከያን ተቀላቀሉ” ሲሉ ስላልገባቸው ብዙም ቁብ ያልሰጡ ዜጎች ይህን ሰነድ ሲያነቡና ሲሰሙ ወደ ሁዋላ ተመልሰው የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ ማስታውሳቸውን ያመለከቱት መኮንኑ፣ ባለፉት ሁለት ሶስት ወአርት ብቻ መከላከያ ራሱን በሰው ሃይል በብቃት አደራጅቶ አቅሙን ለማመጣተን ላቀረበው ጥሪ የተሰጠውና እየተሰጠ ባለው መልስ ኢትዮጵያ የጦር ሃይሏ ከወራት በፊት ከነበረው በአስር እጥፍ እንዳሳደገች አመልክተዋል። ይሁን እንጂ አስር እጥፍ ሲሉ ስንት እንደሆነ አላብራሩም።

አንባቢያን ሙሉ ሰነዱን ከፍለጋችሁ በቴሌግራም አድራሻ ጠይቁን እናደርሳለን። አድራሻችን

https://t.me/zagol_news

Leave a Reply