በሰሜን ወሎ ትህነግ በተቆጣጠራቸው ቦታዎች የሚበላ የለም፤ ዜጎች ህይወታቸው እያለፈ ነው

“አሸባሪው ቡድን ወረራ በፈጸመባቸው አካባቢዎች በህክምናና በምግብ እጦት ንጹሀን ዜጎች ህይወታቸው እያለፈ ስለመሆኑ በተጨባጭ መረጃ ተረጋግጧል›› ሲሉ
የወልዲያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ መሐመድ ያሲን ተነግረዋል። የሚበላ እንደሌለ አመልክተዋል።

የአሸባሪው ህወሓት ወረራ በፈፀሙባቸው የሰሜን ወሎ አካባቢዎችና የወልዲያ ከተማ በምግብ፡ በህክምና እና መድሃኒት እጥረት የተነሳ በርካታ ንጹሀን ህይወታቸው እያለፈ ስለመሆኑ በተጨባጭ መረጃ ማረጋገጣቸውን ያስታወቁት ከንቲባው፣ ” በሰሜን ወሎ አሸባሪው ህወሓት በተቆጣጠራቸው ቦታዎች ላይ የሚበላ ነገር የለም” ብለዋል።


ተጨማሪ ይህን ያንብቡ

ከንቲባው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢዎች እንደተናገሩት፤ አሸባሪው ህወሓት በተለይም በሰሜን ወሎ ዞን ላይ የፈጸመውን ወረራ ተከትሎ አዛውንቶች፣ ህፃናት፣ ሴቶች እና አቅመ ደካሞች ለከፍተኛ ችግርና እንግልት ከመዳረጋቸውም በላይ ቡድኑ የህክምና ተቋማትን በመዝረፉና በማውደሙ በህክምና እጦት ምክንያት ህይወታቸው እያለፈ መሆኑ ታቃውቋል።

ሰሜን ወሎ ከ18 ሺ በላይ የስኳር ታካሚዎች፣ ከ20 ሺህ በላይ የፀረ ኤችአይቪ መድኃኒት ተጠቃሚዎች፣ 1145 የቲቢ ታካሚዎች አሉ። እነዚህ የዕለት ተዕለት መድሃኒት፣ ሕክምና፣ ክትትልና ድጋፍ የሚያሻቸው ሰዎች እጣ ፈንታ አይታወቅም።

እንደ አቶ መሐመድ ገለጻ፤ በአሁኑ ወቅት በሰሜን ወሎ አሸባሪው ህወሓት በተቆጣጠራቸው ቦታዎች ላይ የሚበላ ነገር የለም፡፡ መብራት፣ ውሃ እና የእህል ወፍጮም የለም፡፡ የባንክ አገልግሎት ባለመኖሩን ገንዘብ ያላቸው አውጥተው መሥራት አልተቻለም፡፡

አሸባሪው ህወሓት በአማራ ህዝብ ላይ ሂሳብ አወራርዳለሁ ብሎ በፈጸመው ወረራ በርካታ ታጣቂዎቹ የተደመሰሱበት፣ ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት የደረሰበት በመሆኑ ጭምር ህልዝቡን በበቀል ስሜት አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን የመዝረፍ፡ የማውደም፡ ንጹሃንን የመግደል፡ ሴቶችን የመድፈርና ሌሎችንም የሽብር ወንጀሎችን ፈጽመዋል ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት በዚህ ወራሪ አሸባሪ ቡድን ላይ እየተወሰደ ባለው እርምጃ ጥሩ ውጤት እየተገኘ መሆኑን ጠቁመው፤ ዳግም ስጋት የማይሆንበት ደረጃ ለማድረስ ሁሉም አካል መረባረብ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

በተመሳሳይ ዜና በትግራይ በረሃብ ምክንያት ሰዎች እንደሞቱ ክልሉን እየመራ ያለው ትህነግ ማስታወቁ አይዘነጋም። 500 ገደማ ከባድ መኪኖች ዕርዳታ ጭነው ወደ ትግራይ ማምራታቸው ቢገለጽም ትህነግ ችግሩ አሳሳቢ እንደሆነ አመልክቷል። በተመሳሳይ ትግራይ ከገቡት ተሽከርካሪዎች መካከል ከ36 በስተቀር የተቀሩት እንዲመለሱ አለመደረጉን ጠቅሶ የተመድ እርዳታ ለማሰራጨት እንደሚችገር ማስታወቁን መዘገባችን ይታወሳል።

See also  ሱዳንና ኢትዮጵያ በቁልፍ ጉዳዮች መስማማታቸው ተሰማ- "የትህነግ መጨረሻ ግልጽ እየሆነ ነው"

Leave a Reply