በድንገተኛ የሞተር ብልሽት የፖላንድ አውሮፕላን አዲስ አበባ አረፈ

በድንገተኛ የሞተር ብልሽት ምክንያት የፖላንድ አውሮፕላን አዲስ አበባ ማረፉን የፖላንድ መንግስት አስታወቀ፡፡

ንብረትነቱ የኢንተር አየር መንገድ (የኢንተር ኤር) የሆነ አውሮፕላን በሞተር ላይ በገጠመው ድንገተኛ ብልሽት ምክንያት በኢትዮጵያ የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ለማረፍ መገደዱን የፖላንድ መንግስት አስታውቋል።

አውሮፕላኑ ከኬንያ ሞምባሳ ከተማ 167 ሰዎችን አሳፍሮ እየተጓዘ በነበረበት ወቅት በአንደኛው የሞተር ክፍሉ ላይ የተሳሳተ መረጃ በመነበቡ ምክንያት አዲስ አበባ እንዲያርፍ ተገዷል ብለዋል።

በአውሮፕላኑ ሞተር ላይ በገጠመ ብልሽት ምክንያት የተሳፈሩ ሰዎች ለእንግልት እንዳይዳረጉ ተተኪ አውሮፕላን ከፖላንድ መላካቸውን የሀገሪቱ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፒዮትር ዋውርዚይክ ተናግረዋል።

ምክትል ሚኒስትሩ አክለውም ተተኪው አውሮፕላን ዛሬ ከሰዓት አዲስ አበባ እንደሚደርስ ጠቁመው እስከዛው ተጓዦቹ በሆቴል መቆየት የሚያስችላቸውን የኢትዮጵያ ቪሳ እንዲያገኙ በአዲስ አበባ የሚገኙ የፖላንድ ጉዳይ አስፈጻሚዎች እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ገልጸዋል።

አውሮፕላኑ ተሳፋሪዎቹን ጭኖ ስለመነሳቱ በቂ መረጃ ሰጥቶን ነበር ያሉት የፖላንድ አየር መንገድ ሃላፊ፤ የሞተሩ ቴክኒካዊ ብልሽት ምክንያት ምን እንደሆነ እየተመረመረ መሆኑንም ተናግረዋል።

ኢንተር ኤር የተባለው አየር መንገድ በፖላንድ ግዙፉ የግል አየር መንገድ ሲሆን፤ እኤአ በ2019 ብቻ ሁለት ነጥብ አምስት ሚሊየን ደንበኞችን ከሰላሳ ሀገራት በላይ ማጓጓዙን ዘ ፈርስት ኒውስ የተባለ ድረገጽን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል።

በድንገተኛ የሞተር ብልሽት የፖላንድ አውሮፕላን አዲስ አበባ አረፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በድንገተኛ የሞተር ብልሽት ምክንያት የፖላንድ አውሮፕላን አዲስ አበባ ማረፉን የፖላንድ መንግስት አስታወቀ፡፡

ንብረትነቱ የኢንተር አየር መንገድ (የኢንተር ኤር) የሆነ አውሮፕላን በሞተር ላይ በገጠመው ድንገተኛ ብልሽት ምክንያት በኢትዮጵያ የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ለማረፍ መገደዱን የፖላንድ መንግስት አስታውቋል።

አውሮፕላኑ ከኬንያ ሞምባሳ ከተማ 167 ሰዎችን አሳፍሮ እየተጓዘ በነበረበት ወቅት በአንደኛው የሞተር ክፍሉ ላይ የተሳሳተ መረጃ በመነበቡ ምክንያት አዲስ አበባ እንዲያርፍ ተገዷል ብለዋል።

በአውሮፕላኑ ሞተር ላይ በገጠመ ብልሽት ምክንያት የተሳፈሩ ሰዎች ለእንግልት እንዳይዳረጉ ተተኪ አውሮፕላን ከፖላንድ መላካቸውን የሀገሪቱ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፒዮትር ዋውርዚይክ ተናግረዋል።

ምክትል ሚኒስትሩ አክለውም ተተኪው አውሮፕላን ዛሬ ከሰዓት አዲስ አበባ እንደሚደርስ ጠቁመው እስከዛው ተጓዦቹ በሆቴል መቆየት የሚያስችላቸውን የኢትዮጵያ ቪሳ እንዲያገኙ በአዲስ አበባ የሚገኙ የፖላንድ ጉዳይ አስፈጻሚዎች እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ገልጸዋል።

አውሮፕላኑ ተሳፋሪዎቹን ጭኖ ስለመነሳቱ በቂ መረጃ ሰጥቶን ነበር ያሉት የፖላንድ አየር መንገድ ሃላፊ፤ የሞተሩ ቴክኒካዊ ብልሽት ምክንያት ምን እንደሆነ እየተመረመረ መሆኑንም ተናግረዋል።

ኢንተር ኤር የተባለው አየር መንገድ በፖላንድ ግዙፉ የግል አየር መንገድ ሲሆን፤ እኤአ በ2019 ብቻ ሁለት ነጥብ አምስት ሚሊየን ደንበኞችን ከሰላሳ ሀገራት በላይ ማጓጓዙን ዘ ፈርስት ኒውስ የተባለ ድረገጽን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል።

FBC

Leave a Reply