ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የቻይናው አቻውን ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግን ለማግኘት ያደረገው ሙከራ አልተሳካም

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የቻይናው አቻውን ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግን ለማግኘት ያደረገው ሙከራ አልተሳካለትም ምክንያቱም ዢ ጂንፒንግ የጆ ባይደንን የጉብኝት ጥያቄ ውድቅ ስላደረገበት !

ቻይና ምእራባውያኑን በሁሉም መልኩ ሰቅዛ አቅማቸውን እያዳከመች ትገኛለች ። አሁን ቻይና ሁሉንም ሀገራት በኢኮኖሚ ጡንቻዋ እያስፈራራች ትገኛለች ። በዶናልድ ትራምፕ ዘመን አሜሪካ ቻይናን አሸንፋለሁ ብላ የከፈተቺው የንግድ ጦርነት ራሷን የመምታት ያክል ሆኖባት ከፍተኛ ኪሳራን አከናንቧታል ። በአንፃሩ ቻይና የአሜሪካ የንግድ ጦርነት እንኳንስ ሊገታት ይቅርና አሁንም የአለምን የኢኮኖሚ ግስጋሴ በእጇ ተቆናጣ እየገሰገሰች ትገኛለች ።

በወታደራዊው መስክ የቻይና እመርታ ሁሉንም ያስደነገጠ ነው ። አሁን ቻይናን አሜሪካን በሚሳኤሎቿ ለማደባየት ፖስፊክ ውቅያኖስን እንኳ ማቋረጥ አይጠበቅባትም ። እዚያ ከቻይና ጣቢያዋ ሆና ከድምፅ በብዙ እጥፍ የሚፈጥኑትን አስር ሺህ ኪሎሜትሮችን የሚምዘገዘጉትን Hypersonic ሚሳኤሎቿን መላክ ብቻ ነው ። በደቂቃ ውስጥ ከእይታ በተሰወረው ተልእኳቸው አሜሪካን ዘይረው ይመለሳሉ ።

ከሁሉ በላይ ግን አሜሪካን የሚያስጨንቃት ቻይና የማታውቀው ወታደራዊ ሚስጥር ያለመኖሩ ነው ። ቻይና በሳይበር መንታፊዎቿ አማካኝነት የአሜሪካ የጦር አቅም ፤ የዘመቻ እቅድ ፤ የበጀት ሁኔታ ፤ የመሳሪያ አይነትና ጥራት ሁሉም መረጃዎች አሏት ። እናም አሜሪካ ከቻይና የተደበቀው ወታደራዊ ሚስጥሯ አናሳ ነው ። ቻይና በየ አመቱ በጣም ብዙ ቴራባይት ሚስጥራዊ ዳታዎችን ከአሜሪካ ትሰርቃለች ።

ቻይና መረጃ ከመመንተፍ አልፋ አሜሪካ የምትራቁቅባቸውን የጦር መሳሪያዎች አሰራር በመመንተፍ ከአሜሪካ አሻሽላ በመስራት የአሜሪካ ቅዤት ከሆነች ቆየች ። አሜሪካ የሆነ መሳሪያ ፈጥራ በድብቅ ብትይዝም ቻይና ሰርቃ የተሻለውን መሳሪያ ይፋ ታደርጋለች ።

በአንፃሩ ግን የቻይና የጦር ቴክኖሎጂ የሚታወቀው ቻይና ይፋ ስታደርገው ብቻ ነው ። በዚህች አለም ላይ የቻይናን ያክል ሚስጥራዊ ሀገር የለም ። የቻይናን ወታደራዊ አቅም ፤ የጦር ልህቀት ፤ ወታደራዊ በጀት በትክክል የማያውቅ የለም ።

በወታደራዊም ሆነ በኢኮኖሚው ዘርፍ ቻይናን ማስቆምና መቋቋም ያቃታት አሜሪካ ከቻይና ጋር የእንነጋገር ጥያቄጰዘ ብታቀርም በቻይና ውድቅ ተደርጎባታል ።

ፕሬዘዳንት ባይደን ለፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒን ያቀረበው ግብዣም በፕሬዚዳንት ዢ ውድቅ ተደርጎበታል ። ሌሎች ሀገራት ላይ ስትደነፋ የኖረቺው አሜሪካ ከቻይና ጋር ስትደርስ ትእቢቷ እየሟሸሸ መጥቷል ። ተለምነው እሺ የማይሉት የአሜሪካ መሪዎች ዛሬ የቻይና መሪዎችን ለምነው እንኳ ማግኘት አልቻሉም ።

Seid_Mohammed_Alhabeshiy

Leave a Reply