አምስት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በቻይና ቤጂንግ በተካሄደው የአለም ሮቦት ቴክኖሎጂ ውድድር ሻምፒዮና የወርቅ፣ የብርና የነሐስ ሜዳሊያ በማምጣት ማሸነፋቸው ተገለጸ።

በቻይናዋ ርዕሰ መዲና ቤጂንግ እ.ኤ.አ የ2021 የሮቦት ቴክኖሎጂ ውድድር መካሄዱን የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በዚህም በቻይና ቲያን ጂን ዩኒቨርስቲ የሚማሩ አምስት ኢትዮጵያውያን በውድደሩ አምስት ሜዳሊያ እንዳሸነፉ በቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክትር ጄኔራል ዉ ፔንግ አስታውቀዋል።

ዳይሬክተሩ እንደገለጹት ኢትዮጵያውያኑ የሮቦት ውድድሩን ያሸነፉት አንድ ወርቅ፣ ሁለት የብርና ሁለት የነሐስ ሜዳሊ በማምጣት ነው።

አክለውም ለመላው ኢትዮጵያውያንና ለአሸናፊዎቹ ከፍተኛ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ማስተላለፍ እፈልጋለሁ ብለዋል። via (ኢዜአ)

Leave a Reply