በትግራይ ኮሚኒቲ ውስጥ በትግረኛ ተጽፎ ውስጥ ለውስጥ ሲሰራጭ የነበረ ጽሁፍ በሚል ወደ አማርኛ ተመልሶ የተሰራጨ መረጃ ነው። መረጃውን ያሰራጨው ስዩም ተሾመ ሲሆን ዋናውን ሰነድ በትግርኛ፣ እንዲሁም በእንግሊዘኛ ከተረጎሙት ክፍሎች ጋር አዳምሮ አቅርቧል። ይህ ለትግራይ ተቆርቋሪ ከሆኑ ወገኖች የተጻፈው ብቻ ነው።

የትግራይ ተቆርቋሪዎች የተሰጠ አስቸኳይ ማሳሰብያ!

እኛ ይህ ሃሳብ ለህዝብ እንዲደርስ የፈለግነው፤ ጀግናው የትግራይ ሰራዊት TDF ከምድረ-ገፅ ለማጥፋት እየሰሩ ያሉ ጠላቶቻችን አሸንፎ ትግራይ ከጠላቶቻችን ነፃ ካወጣበት ጊዜ ጀምሮ ድላችን የሚጎዱ እና ጥሩ ያልሆኑ ሁኔታዎች በመፈጠራቸው ነው፤

በመሆኑም ይህን ምክረ-ሃሣብ ለመስጠት ተገደናል፡፡

ይህንን ሃሳብ ያነሳን ተጋሩ ከተለያየ የህብረተሰብ ክፍል የተወጣጣን ስንሆን፤ ሃሳቡም በውጭ ሃገር ለሚኖሩ አንዳንድ ታዋቂ ግለሰቦች፤ሰራዊቱ እየመሩ ለሚገኙ የጦር አመራሮች፤ጉዳዩ ለሚያሳስባቸው የሰራዊቱ አባላት፤ እንዲሁም የሲቪክ ተቋማት ሓሳባቸውን አካተናል፡፡

ይህንን ሓሳብ ያቀረብነው ግለሰቦች ስማችን እንዳይጠቀስ የፈለግነው፤ ከሃሳብ አልፎ ወደ ግለሰቦች ፍረጃ እንዳይገባ እና ሓሳቡ ላይ ብቻ ትኩረት እንዲደረግ በማሰብ ነው፡፡

የዚህ ሓሣብ አቅራቢዎች ህዝባችንና የሚመለከታቸው አካላት በዋና ዋና ጉዳዮች ትኩረት እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡

  1. ራስን የመከላከል በድል እንዲጠናቀቅ የሁሉም ትግረዋይ አጀንዳ ሊሆን ይገባል፡፡

ጠላቶቻችን ከየትም ተሰባስበው ህዝባችን ለማጥፋት በሚንቀሳቀሱበት በራስን የመከላከል ዘመቻው ላይ ምንም ዓይነት ተፅዕኖ እንዳይፈጠር ህዝባችን መከላከሉ ላይ ትኩረት እንዲያደርግ እንጠይቃለን፡፡

  1. በተመረጡት የትግራይ ክልል መንግስት ሁላችንም መስማማት እና መግባባት ይኖርብናል፡፡ የምናነሳውን ጥያቄ ጠላቶቻችን እንዳይጠቀሙበት ሁላችንም አንድ ዓይነት አቋም ሊኖረን ይገባል፡፡

3.ለቀጣይ እያንዳንዱ ትግረዋይ መወሰን እንደአለበት ማመን አለብን፤ እነዚህን መነሻ በማድረግ በቅርቡ እየመጡ ያሉ ክፍተቶች ሁሉም ትግረዋይ ተረባርቦ በወቅቱ በማወቅ ቀጥለው ላሉት ጉዳዮች በአስቸኴይ እንዲያዩ እናሳስባለን፡፡

1.በፓርቲዎች ያሉ ፉክክሮች ጤነኛ ሆነው እንዲቀጥሉ እናሳስባለን፡፡ በሰራዊታችን እና ህዝባችን ድል ወደ መቀለ ከተመለስን በሓላ፤ ህወሓት እየፈፀመው ያሉ አንዳንድ የወታደራዊ አመራር ጉዳዮች በመከላከል ስራችን ላይ ጥቁር ነጥብ ማስቀመጡ ተመልክተናል፡፡

  1. ከድል በኋል በተደረጉ ግምገማዎች ንፁሃን ተጋሩ ያለ አግባብ ተፈርጀው ለእስር ተዳርገዋል፡፡ከጊዝያዊ አስተዳደር እና “ከአብዪ አህመድ ጋር ሰርታችኋል” ተብለውም እርምጃ ተወስዶባቸው አይተናል፡፡ ከትግራይ ውጭ ያሉ ተጋሩ እየታሰሩ ነው ብለን በምንጠይቅበት ሰዓት፥ በተመሳሳይ በትግራይ ውስጥም የከፋ ችግር እየደረሰባቸው በመሆኑ ግምገማው እንዲቀዛቀዝ እንጠይቃለን፡፡ በተለይ “ባንዳ” እየተባሉ ያለምግብ የሚታሰሩ እና የሚንገላቱ አስቸኳ ፍትሕ እንዲሰጣቸው እንጠይቃለን፡፡
  2. በትግራይ ያለው የህወሓት እና የተፎካካሪ ፓርቲዎች ሽኩቻ እልባት ማግኘት አለበት፡፡ተፎካካሪዎቹ ጫካ በነበሩበት ወቅት ህወሓት ደካማ ነው የሚል አቋም ይዘዋል፡፡ህወሓት ደግሞ ጫፍ የወጣ አስተሳሰብ ነው ያላቸው በማለት ፈርጇቸዋል፡፡ሁለቱም በየራሳቸው መንገድ እየሄዱበት ያለው መንገድ አደገኛና በታኝ ነው፡፡ በመሆኑም ህወሓትም በተለያዩ ጉዳዮች እና ውሳኔዎች ላይ ሊያሣትፋቸው ይገባል፤እነሱም ጫፍ መርገጥ ትተው መከላከል ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡

4.የትግራይ ሃይል ተስማምተው ያልሰሩት ነገር ላይ ውጤት ያላመጡ ለሚድያ ሽፋን ብቻ እንዲውሉ የሚደረገው አግባብ ጥቅማቸው እንዲጠና እንላለን፡፡ ከትግራይ ሓይሎች በጋራ መስራት ሳይቻል ከኦነግ ሸኔ ጋር የሚደረገው ግንኙነት ፖለቲካችን እየጎዳው ነው፡፡በተመሳሳይ ከአገው እና ቅማንት በሚድያ ከሚወራው የዘለለ የተደረገላቸው ድጋፍ እንደሌለ ለመረዳት ችለናል፡፡ በመሆኑም ወደ ውጭ ከማየታችን መጀመርያ ራሳችንን በደንብ ብንፈትሽ እንላለን፡፡

  1. አንዳንድ የፕሮፖጋንዳ አካሄዶች እርምት እንዲደረግላቸው እንጠይቃለን፡፡ለምሳሌ የትግራይ ህዝብ በርሃብ እያለቀ እያለ ለሰራዊቱ ደጀን በመሆን ስንቅ እያዘጋጀ ገንዘብ እያዋጣ ነው የሚል ለማመን የሚከብድ ስለሆኑ በአስቸኳይ ቢታረሙ፡፡

6.ጀግና ሰራዊታችን በተቆጣጠረባቸው አካባቢዎች የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ቢከለሱ፤በሚድያ ቢካድም ኣንዳንድ ጥፋቶች እየጠፈፀሙ ስማችን እየጠፋ ነው፡፡ለምሳሌ ተቋማት ማፍረስና መዝረፍ፤ የትምክህት ሚድያዎች ተሰባስበው ትግረዋይ የሊጥ ሌባ እንዲባል የተደረገው በኛ ስሕተት መሆኑ ታምኖ እርምት እንዲደረግ እንላለን፡፡ ህዝባችን ክርስትያን በመሆኑ በቀሳውስት እና በቤተክርስትያን ተፈፀሙ የተባሉ ተጣርተው ለህዝብ ማሳወቅ አለብን፡፡ በሙስሊም ወገኖች ተፈፅሟል የተባለው ለጠላቶች ማሰባሰብያ ስለሚሆን ጥንቃቄ ማድረግ አለብን፡፡

7.ከሰራዊት ምልመላ ጋር ተያይዘው የሚነሱ ክፍተቶች በአፋጣኝ እንዲታረሙ እንጠይቃለን፡፡ አርዳታ አታገኙም ብሎ ከማስፈራራት ፤የህልውና ጉዳይ ነው ብሎ ማስረዳት ይቻላል፡፡የተወሰኑ የሰራዊቱ አባላት በጅምላ የተቀበሩበት፤ወደ ወንዝ የተጣሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ፤በክብር ማረፍ ሲገባቸው በዚህ መልኩ ከተከናወነ ተጣርቶ ለቀጣይ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ እንጠይቃለን፡፡

8.ትግላችን ፍትሓዊ፤ለነገ የዲሞክራሲ መግብያ በር ነው፡፡ይሁን እንጂ ከህዝባችንልምድ የወጡ አካሄዶች ይሥተዋላሉ፡፡ወደ መቀሌ ከተመለስን በኋላ ሴቶች እየተደፈሩ ነው፡፡ከተቆጣጠርንባቸው አካባቢዎች የሚመጡ ማተርያሎች እና ገንዘቦች ለተቸገሩ ከማዋል ይልቅ ለካድሬዎች እና ቤተሰቦቻቸው ጥቅም ብቻ እየዋሉ ነው፡፡ በመሆኑም ቶሎ መቆም አለበት፡፡

9.ጠላቶቻችን በትግራይ ህዝብ ላይ ሁሉን ዓይነት ጥቃት ፈፅመዋል፤ይህም ዝግጅት ባለመደረጉ ብዙ ጉዳቶች ደርሰዋል፡፡ይህም አዲስ አበባ እንገባለን በማለት ብቻ መረጃ አንጠባጥበው ወደ በረሓ በመግባታቸው ነው፡፡የአንድ ህዝብ ስትራተጂካዊ አካሄድ የሚተነብይ፤የትግል ሰነድ የያዘ፤ በጠላት እጅ ገብተው ችግር እየፈጠሩ ይገኛሉ፡፡በዚህ ጉዳይ ጥልቅ ግምገማ ተካሒዶ ለቀጣይ አንድ የመከላከል አቅጣጫ መከተል ይኖርብናል፡፡

10.በአሁኑ ሰዓት ከትግራይ ጋር የቆዩ የውጭ ወዳጆች አሉ፡፡ይሁን እነጂ ለውጮች ልናሳምናቸው የምንችለው በራሳችን ዓቅም ነው፡፡ከዚህ ውጭ ለውጭ ሓይሎች ብቻ ማመን ጉዳት ይኖረዋል፡፡ለምሳሌ በክልላችን ገብተው እርዳታ የሚሰጡ፤ተለያዩ ስራዎች የሚሰሩ ህዝባችን የሚጠቅሙ እንዳሉ ሁሉ ይህንን ተጠቅመው ከጠላቶቻችን ጋር የሚሰሩም አሉ፡፡ለዚህም የኤምባሲ ምንጮቻችን ጠቁመውናል፡፡በመሆኑም በራሳችን አቅም ተማምነን፤ባልደረቦቻችን በጥንቃቄ ልንመለከተው ይገባል፡፡

11.ሁሉም ተጋሩ አንድነታቸው እንዲያጠናክሩ መጠየቅ አለብን፡፡ በተለይ ከድል በኋላ የሚታየው የስልጣን ሽኩቻ፤ራሰስህን ማግለል ትቶ የጋራ እንዲሆን መጠየቅ እንወዳለን፡፡ በውጭ የምትኖሩ ወገኖች ከጀግናው ሰራዊታችን ሳትለያዩ፤የውጭ ዲፕሎማሲ ይዛችሁ፤እየተሰደባችሁ ለህዝባችሁ ፀንታችሁ በመቆማችሁ የተገኘው ድል ፤በተወሰኑ አካላት እንዳይቀለበስ የትግራይ ቀጣይ እጣፈንታ ላይ የራሳችሁን አስተዋፅኦ እንድታበረክቱ ጥሪ እናቀርብላቹ አለን፡፡ ሚድያዎች በውስጥ የትግራይ ጥቅም ብቻ በማሰብ ከማንኛው ውግንና ወጥተን የድርሻችን እንድናበረክት ጥሪያችንን አቅርበናል፡፡

ትግራይ ታሸንፋለች

ከ የትግራይ ተቆርቋሪዎች!

10/01/2014

Leave a Reply