አዲስ አበባ ከ27 ሺህ በላይ ዘብ አደራጀች

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወንጀል መከላከል ያሰለጠናቸውን ከ27 ሺህ በላይ በጎ ፈቃደኞችን አስመረቀ።የአካባቢ ሠላምና ፀጥታን ለማስጠበቅ መሰረታዊ የፖሊስ ስልጠና የወሰዱ 27 ሺህ 540 በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ምረቃ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ተከናውኗል።ወጣቶቹ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንና በሌሎች ተቋማት አስተባባሪነት “እኔ ለከተማዬ ሠላም ዘብ ነኝ” በሚል መሪ ሃሳብ ስልጠናቸውን ተከታትለዋል፡፡

ስልጠናው በወንጀል መከላከል፣ በስነምግባር፣ በጎ ፍቃደኝነት፣ የሠላም እሴት ግንባታ እና ሁለንተናዊ ሠላም፣ በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ነው የተሰጠው።በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም በተካሄደው የምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል ሀላፊ አቶ መለሰ አለሙ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋውና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

Leave a Reply