ውጊያው መቀለ አፍንጫ ስር ሆኗል ትህነግ “የአፋር ሃይል ጉዳት አደረሰብን” አለ- ውጊያው ወደፊት እየገፋ ነው

Image

በአፋር ጫፍ ውጊያው ከመቀለ አፍንጫ ስር ሲደርስ ትህነግ አፋርን ወንጅሏል። ይህንኑ ውንጀላ ” ጃል እንዴት እንዴት ነው ነገሩ? ‘ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሃል’ እንደሚባለው TPLF አፋርን ወሮ፣ገድሎ፣ዘርፎና አፈናቅሎ ሳለ አሁን ደሞ ተወረርኩ ይላል። እንኳን የአፋርና የትግራይ ህዝብ መብረቃዊ ጉርብትና አሁን ትዝ አላችሁ” ሲሉ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ትህነግን መግለጫ ቆርጠው በቲውተር ገጻቸው የለጠፉት ዶክተር ኮንቴ ሙሳ ናቸው።

እሳቸው ብቻ ሳይሆኑ ሌሎችም በትህነግ መግለጫና በመግለጫው በተገለጸው አግባብ መገረማቸውን እያስታወቁ ነው። ትህነግ አፋርን አስመልክቶ ” … የክልሉ ልዩ ሃይልና ታጣቂዎችን በማሰማራት በትግራይ የተለያዩ አካባቢዎች ማለትም በምላዛት፣ ዴሳኣ፣ መቻርና ጨርጨር ልዩ ቦታዎች በትግራይ ሕዝብና ሰራዊት ላይ ተደጋጋሚ ትንኮሳ በማድረግ ጉዳት አድርሷል” ሲል ከሷል።

መግለጫው አያይዞም ድርጊቱ ” በአፋርና በትግራይ ሕዝብ መካከል ለረጅም ጊዜ ተዛምዶ የኖረው ወንድማዊ ግንኙነትና የትግል አጋርነት … ለማጋጨት የታለም እኩይ ተግባር ነው” ሲል ትህነግ

” የትግራይ ሰራዊት በደረሰባቸው የአፋር ቦታዎች የሚኖረው ሕዝብ፣ የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች ደማቅ አቀባበል በማድረግ ከጎኑ እንደ ኢሰለፉ በተለያዩ ጊዜያት ገልጸዋል” የሚለው ትህነግ፣ ምን ሊያደርግ ወደ አፋር ክልል እንደዘመተ፣ ምን አድርጎ እነተባረረና ለምን የፋር ልዩ ሃይልና ሚሊሻ ትግራይ ክልል ድረስ ዘለቆ ጥቃት ለመሰንዘር እንደተነሳሳ አላብራራም።

“በሽብርተኛነት የተፈረጀው ህወሀት ከያሎ እና ጎሊና ወረዳዎች ተፈናቅለው ጋሊኮማ ጤና ጣቢያ እና ትምህርት ቤት ተጠልለው በነበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ አርብቶ አደሮች ላይ ጥቃት መፈጸሙን የክልሉ መንግስት በቪዲዮ አስደግፎ ሲያስታውቅ ትህነግ ስለ አብሮነትና ስለቆየ ትሥሥር አላሰላም ነበር ” ሲል የአፋር ክልል ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ያወታውን ዜና በመጥቀስ አስተያየት የሰጡ፣ የድርጅቱን መሪዎች ጤንነት እንደሚጠራጠሩ አመልክተዋል።


READ MORE – ዶ/ር ኮንቴ ” እውነቱን እናውቀዋለን፣ ትህነግ ጨፍጭፎናል” በአፋር የሶስት ቀን ሃዘን ታወጀ፤ ትህነግ ተጨማሪ 8 የቤተሰብ አባላት ገደለ

ቡድኑ በአፋር ክልል በፈንቲ ረሱ/ዞን በኩል ጥቃት በመክፈቱ ምክንያት ከያሎ እና ጎሊና ወረዳዎች ከቤት ንብረታቸው በመፈናቀል በጎሊና ወረዳ ጋሊኮማ የምትባል ቀበሌ በጤና ጣቢያ እና ት/ ቤት ጊዚያዊ መጠለያ ውስጥ ተጠልለው የነበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ አርብቶ አደር ማህበረሰብ ላይ በከባድ መሳሪያ (በመድፍ፣ በሞርታር እንዲሁም በታንክ) የታገዘ ድንገተኛ ጥቃት በመክፈት “እጅግ ዘግናኝ የሆነ ጭፍጨፋ ፈፅሟል” ሲል የአፋር ክልል በወቅቱ አስታውቆ ነበር። ዶክተር ኮንቴ ” ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮኻል እንዲሉ” በማለት በቲውተር ገጻቸው በትህነግ ወቅታዊ ቁመናና ልመና መገረማቸውን አስታውቀዋል።

“ተፈናቃዮቹ በጊዚያዊነት ተጠልለውበት የነበረውን ጤና ጣቢያ እና ትምህርት ቤት በማቃጠል በንፁሀን ህዝብ ላይ አረመኔያዊ ጥቃት በመፈፀም አስከፊ እልቂት አስከትሏል” የተባለው ትህነግ ያቆሰላቸውና ሆስፒታል የተኙ ሲመሰክሩ እንዳሉት የሆነው ሁሉ እጅግ ዘግናኝ ነው።

በቅርቡ ተፈናቅላ ጥላው ከሄደችው በአፈር የተሰራ ደሳሳ መኖሪያ ቤት ስትመለስ ምንም ነገር እንዳላገነች የገለጸች የሶስት ልጆች እናት ” ካሁን በሁዋላ እዚህ እንዴት እኖራለሁ? ስትል እያነባች አንድ ኩባያ እንኳን ሳይቀር የተዘረፈውን ቤቷን እያሳየች ስታለቅስ፣ የትህነግ ሰዎች ስለ አብሮነት አያስቡም ነበር ሲሉ ቁጣቸውን የገለጹ ጥቂት አይደሉም።

በጋሊኮማ የሚገኘውን የምግብ መጋዘን በከባድ መሳሪያ አጋይቶ፣ በመጋዘኑ ውስጥ የነበረ ከ30,000 በላይ ለሚሆኑ ስደተኞች የቀረበ አስቸኳይ የምግብና አልባሳት እርዳታ ሙሉ በሙሉ ያወደመው ትህነግ፣ ከአፋር ክልል ተመቶ እስኪሰናበት ድረስ ትንህርት ቤቶች፣ የጤና ጣቢያዎች፣ የመሰረት ለማቶች፣ የመንግስት ተቋማት፣ የአርብቶ አደሮችን ፍየሎች፣ ግመሎችና ቁሳቁስ ጥርግ አድርጎ መዝረፉን ሰለባዎች በቪዲዮ የተደገፈ ምስክርነት በመስጠት ሲያረጋገጡ እየታየ ፤ ትህነግ የአፋር ህዝብና የሃይማኖት አባቶች በጭብጨባ ተቀበሉን” ሲል ስለ የትኛው የአፋር ህዝብ እንደሚናገር ሊገባቸው እንዳልቻለ አስተያየት የሰጡ አመልክተዋል። በትግራይ ሕዝብና በፋር ሕዝብ መካከል ችግር እንደሌለ፣ ነገር ግን የትህነግን መመሪያ የተቀበሉና አፋርን ወረው ያወደሙና የዘረፉ ግን ቅጣት ቢቀበሉ አግባብ መሆኑን አስተያየት የሰጡ ተናግረዋል።

በተመሳሳይ ዜና ከላይ ከተጠቀሱት ስፍራዎች በተጨማሪ የፋር ልዩ ሃይልና መከላከያ በግራ እየተቆጣጠሩና ወደ መቀለ ለማምራት በሚያስችል ዝግጅት ላይ መሆናቸው ተሰምቷል። ከወልደያ ግንባር እያጸዳ የሚሄደው ሃይል ስራውን ሲጨርስ ሁለቱ ግንባሮች ተናበው ቀጣዩን ተግባር እንደሚፈጽሙ እየተነገረ ነው። ትህነግ ግን የአፋር ሃይል የተቀሳቸውን ቦታዎች ተቆጣጥሮ እየገፋ መሆኑንን እየገለጸ፣ በተመሳሳይ ደግሞ በርካታ ድል ማስመዝገቡን እያስታወቀ ነው።

በመጨረሻ በተገኘ ዜና ወደ መቀለ መዳረሻ ምላዛት ላይ ትህነግ ክፉኛ ሽንፈት ገጥሞታል።


Leave a Reply