አሜሪካ የፈራችው እየደረሰ ነው – በዞብል የትህነግ ሃይል ፈረሰ

መከላከያ የጸረ ማጥቃት እርምጃ እንዲወስድ ከታዘዘና ይህም ለሕዝብ ይፋ ከሆነ በሁዋላ ” ምን ደረሰ?” የሚሉ በርካቶች ናቸው። በትህነግ በኩል እስከ ትላንትና ድረስ ” ደሴን እንቆጣተራለን” የሚል ዜና ሲሰማ ነበር።

ራሳቸውን ይፋ ማድረግ ያልፈለጉ እንዳስታወቁት የመከላከያ ሰራዊት ዛሬ ንጋት ላይ ትህነግ የሚተማመንበትን የራያን ግንባር ሰብሮ ዞብል ተራራን በመቆጣጠር ወደፊት እያጠቃ መሆኑ ገልጸዋል። የመረጃው ባለቤቶች የግንባሮቹን ስም ለጊዜው ሳይጠቅሱ እንዳሉት ከሆነ ቆቦን በቁጥጥር ስር የማዋሉ ኦፕሬሽን ዳር ደርሷል።

በአየር ሃይል በታገዘ ጥቃት የወልደያን እርከን በመደርመስ ዞብል ተራራን የተቆጣጠረው የመከላከያ ሃይል በቀኝ በኩል ካለው አፋር ግንባር ሰራዊትና ልዩ ሃይል ጋር በመናበብ ቀለበት ሰርተው የተከበበውንና እየሸሸ ያለውን ሃይል እያሳደዱ በማጥቃት ላይ መሆናቸውንም ለማወቅ ተችሏል።

ዝግጁነቱን በተደጋጋሚ ሲያስታውቅ የነበረው የኢትዮጵያ አየር ሃይል፣ በዚህ ኦፕሬሽን ያድረገው ድብደባ እግረኛው ሰራዊት በአንስተኛ ዋጋ ድል እንዲቀዳጅ ያስቻለ መሆኑ ተመልክቷል።

ይህ በንዲህ እንዳለ በአፋር በኩል ውቅሮን ተንተርሶ እይተበቀ ያለው ሃይል በየትኛውም ሰዓት ወደ መቀለ ለማቅናት ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ተሰምቷል። ይህ መሬት ላይ ያለው እውነት እንደሆነ ያመለከቱ እንዳሉት ነገሮች ወደ መጨረሻ መስመር እየተጠጉ ነው።

ደሴን እንደሚቆጣጠር እስከ ትላንት ሲነገርለት የነበረውና ደጋፊዎቹ በስፋት ሲያራቡት የነበረውን መረጃ አስመልክቶ ” ፕሬዚዳንቷ ደሴ ሆነው ተፈናቃዮችን የሚያጽናኑት ደሴ ሰላም ስላለና ስጋት የሚባል ነገር ባለመኖሩ ለመሆኑ ማሳያ ነው” ሲሉ መልሰዋል።

ይህ እስከታተመ ድረስ መንግስትና መከላከያ በይፋ ያሉት ነገር የለም።

ውጊያው መቀለ አፍንጫ ስር ሆኗል ትህነግ “የአፋር ሃይል ጉዳት አደረሰብን” አለ- ውጊያው ወደፊት እየገፋ ነው

Leave a Reply