የዘመድኩን በቀለ እስረኞች !

መምህር ዘመድኩን በቀለ ጅልና ነፈዝ ካገኘ የተዋጣለት አዕምሮ ዘዋሪ ነው። ብዙ ቅን የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ምዕመናን ዘመድኩንን የእነርሱ ድምጽ አድርገው ያስቡታል እናም ለእምነታቸው ካላቸው ቀናኢነት የተነሳ የእርሱን ሀሳብ መመርመርና መፈተሽ እምነታቸውን የመጠራጠር ያህል አድርገው የሚወስዱ ጥቂት አይደሉም።

ዘመድኩን የእምነት ሰው አይደለም። ሰውየው እንጀራ ፈላጊ ፣ ኑሮ ቤተክርስትያን ደጅ ጥላው ስብከተ ወንጌልን በሆነ አጋጣሚ የደመዎዝና የኑሮ መንገድ አድርጎ የወሰደ ባተሌ ነው። በግሌ ብዙ የደመወዝና ኑሮ ነገር ሆኖባቸው መምህርነትን የተቀላቀሉ አስተማሪዎች አውቃለሁ ፣ ሌላ ዕድል እስኪመጣ በተማሪዎቻቸው ህይወት የሚቀልዱ የሀሰት መምህራን። ዘመድኩንም እንዲሁ እግር ጥሎት ስብከተ ወንጌል ውስጥ የገባ ክፉ ሰው ነው።

ስለዘመድኩን ዛሬ ያነሳሁት ብዙ ሰዎች ኦሮሚያ ውስጥ በግፍ የሚገደሉትን አማሮች ሽመልስ አብዲሳ ነው የሚያስገድላቸው የሚል ከንቱ ከዘመድኩን የተቀዳ እምነት ስላላቸው ነው።

፩. ኦሮሚያ ውስጥ ንጹሀንን እየገደለ ያለው ኦነግ ሸኔ ብሎ ራሱን የሚጠራ ሀይል ነው። ህወሃት በቅርቡ በለቀቀው ሰነዱ ኢትዮጵያን በተለጣፊ የብሄር ድርጅቶች ቀውስ ውስጥ ለመክተት እየሰራ እንደሆነ ግልጽ አድርጓል።

፪ .ኦነግ ንጹሀንን የሚፈጀው የአቢይ አስተዳደር ከአማራ ህዝብ ተቃውሞ እንዲነሳበት በወጠነው ስትራቴጂ ነው። ለዚህ ስትራቴጂ ስኬት ደግሞ ብዙ መገናኛ ብዙሃን አስተዋጽኦ አድርገዋል። አቢይና ኦነግ ተናበው ነው የሚሰሩት የምትለው አንካሳ ስብከት እነ ዘመድኩን አርግዘዋት ፣ ርዕዮት ሚዲያ ወልዷት ሀብታሙና ኤርምያስ ጡጦ እያጠቡ ሲያሳድጓት ከርመዋል። በተዘዋዋሪ የህወሃት ኦነግን አቢይን የማዳከምና ህዝባዊ ቅቡልነቱን የማሳጣት ስራ ሲሰራ ተከርሟል። ብዙ ህዝብ አሁንም ይሄን የጅል ትርክት ተሽክሞ ይዞራል።

፫. በቅርቡ ኦነግ ሸኔና ህወሃት ኦፌሴል ጥምረት ፈጥረዋል። ይኼ ማለት ከእያንዳንዱ ንጹሀን ግድያ ጀርባ የእነዚህ ሀይሎች እጅ አለበት። እነ ሽመልስ አብዲሳና ፌዴራል መንግስቱ ላይ ወቀሳ ከተነሳ ወቀሳው ግድያውን ለመከላከል ዳተኝነት ማሳየተቸው ላይ ሊሆን ይገባል እንጂ ሽመልስ አማራን አስገደለ የሚለው ክስ ውሃ አይቋጥርም።

፬. ከላይ ያለው ሀተታ ውስጥ ሀልጊዜም ሊካተት የሚገባው የግብጽ ሱዳንና አረብ ሀገራት መንግስትን ለማዳከም የሚጭሩት የተልዕኮ ጦርነት proxy war ነው። ግብጽና ሱዳን በአሁኑ ወቅት ኦነግንና የቤኒሻንጉል አማጽያንን በመረጃ ፣ ፋይናንስና ወታደራዊ ቁሳቁስ ያግዛሉ። እነ ሽመልስም ይሁን ፌዴራል መንግስቱ እየተከላከሉት ያለው ሀይል እጅግ ውስብስብና ከባድ አቅም የሚፈልግ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል።

ለማጠቃለል ያህል የዚህ ጽሁፍ አላማ ፌዴራል መንግስቱንም ይሁን እነ ሽመልስ አብዲሳን ንጹሀንን ከፍጅት መከላከል ላይ ያሳየትን ደተኝነት ማስተባበል አይደለም። ነገር ግን አንድም ይሁን ሁለት የዘመድኩን በቀለን ምርኮኞች ” አቢይና ኦነግ አንድ ናቸው ” ከሚለው ሙትቻ ሀሳብ ማላቀቅ ነው። ይሄን የሞተ መከራከሪያ የሙጥኝ ብለው ኦሮሞ ሁሉ ኦነግ ሸኔ ነው የሚል ሰንካላ ሎጂክ ማነብነብ የሚመርጡ እንዳሉ አውቃለሁ። እነዚህን አይነት ሰዎች በሀሳብ ከማሳመን ራሱ ዘመድኩንን የእውነት አማኝ ማድረግ ይቀላል።

Via Samson Michailovich

Leave a Reply