አዳነች አቤቤ ሹመት ሰጡ – ዶ/ር ቀነአ ያደታ አሉበት

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቀጣይ የስራ ዘመናቸው ለአዲስ አበባ ሕዝብ በገቡት ቃለ መሰረት ቃላቸውን መፈጸም እንዲያስችላቸው ያዋቀሩትን ስብስብ በየዘርፉ በቢሮ ለይተው ለሹመት አቅርበው አጸድቀዋል። ከንቲባዋ ይፋ ባደረጉት ሹመት ዶ/ር ቀነአ ያደታ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ መሆናቸው ታውቋል።

በአዲሱ ሹመት መሰረት

1. ዶ/ር ቀነአ ያደታ –የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ፣

2. ዶ/ር ሂሩት ካሳው –የባህል፣ቱሪዝምና ኪነ ጥበብ ቢሮ ኃላፊ፣

3. ወይዘሮ ጽዋዬ ሙሉነህ —የፍትህ ቢሮ ኃላፊ፣

4. አቶ ጀማል አብዩ —የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ፣

5. አቶ ዳዊት የሽጥላ—- የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ፣

6. ኢንጂነር አያልነሽ ሃብተማሪያም —የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊ፣

7. ዶ/ር ሙልቀን ሃብቱ —የስልጠና፣ቴክኒክ እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሃላፊ፣

8. ዶ/ር ዮሃንስ ጫላ —የጤና ቢሮ ኃላፊ ፣

9. አቶ አደም ኑር አብዱል ፈታ —የንግድ ቢሮ ኃላፊ፣

10. ዕጩ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ —የትምህርት ቢሮ ኃላፊ፣

11. ወይዘሮ ሃና የሽንጉስ —የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ፣

12. አቶ ሙሉጌታ ተፈራ— የጊቢዎች ቢሮ ኃላፊ፣

13. አቶ አብረሃም ታደሰ —የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ፣

14. ዕጩ ዶክተር ዮናስ ዘውዴ –የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ

15. ወይዘሮ ጽገሬዳ ወርቁ —የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ፣

16. ዶ/ር ዳዲ ወዳጆ —የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ፣

17. አቶ ግርማ ሰይፉ ( የኢዜማ አመራር የነበሩ) —የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ቢሮ ኃላፊና

18. አቶ የሱፍ ኢብራሂም (የአብን አመራር የነበሩ)— የመንግስት የግዢና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል፡፡

ተሿሚዎቹ ምክር ቤት በመቅረብ ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።

Leave a Reply