አዲስ አበባ ከወግ አጥባቂና ፅንፈኛ ዝንባሌዎች፣ አፍርሶ ከሚገነባ አስተሳሰብ ተጸዳለች

መሪዎቼን እመርጣለሁ’ ብሎ ዝናብ እና ጸሃይ ሳይበግረው እስከ ውድቅት ሌሊት ለሰአታት ተሰልፎ የስልጣን ውክልናውን የሰጠንን የአዲስ አበባ ህዝብ እጅግ እያመሰገንኩ፤ በከንቲባነት ሃላፊነቴ ደከመኝ፣ ሰለቸኝ ሳልል የምችለውን ሁሉ ሰርቼ የጣላችሁብኝን አደራ በታማኝነት ለመወጣት ቃል እገባለሁ”

አዳነች አቤቤ

ሰሞኑንን መነሻው ከየት የማይሆን የሹመት ድልድል ዝርዝር የያዘ ሰነድ ሲነሸራሸር ነበር። አዳነች አቤቤ ከአዲስ አበባ እንደሚነሱ የሚጠቁመው ይህ ሰነድ የረከሰበት አዲስ ሹመት ይፋ እየሆነ ነው። ከአዲስ አበባ ይባረራሉ የተባሉት ወይዘሮ “አዲስ አበባ ከተማን ለሁሉም ዜጎች የምትሆን፣ ነዋሪዎቿ ሁሉ ተደስተውባትና ምቾታቸው ተጠብቆ የሚኖሩባት ለማድረግ በብርቱ እንሰራለን”ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከንቲባ ሆነው ከተመረጡ በኋላ ባደረጉት የመጀመሪያ ንግግራቸው አዲሱ የከተማ አስተዳደር፡ “ከተማዋ ለሁላችንም ትበቃለች” የሚል ጽኑ እምነት ይዞ፣ የእጦት እና ስግብግብነት አስተሳሰብን በመሻገር፣ ለሁሉም ዜጎች የምትሆንና ነዋሪዎቿ ሁሉ ተደስተውባትና ምቾታቸው ተጠብቆ የሚኖሩባት ከተማ ለማድረግ በብርቱ እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።

“ከንቲባዋ ከወግ አጥባቂና ፅንፈኝነት ዝንባሌዎች እንዲሁም አፍርሶ ከሚገነባ አስተሳሰብ በመላቀቅ መካከለኛውን መንገድ ይዞ ሁሉም ኢትዮጵያውያንን የሚያሰባስብ አካታች ፖለቲካዊ ጉዞ ተግባራዊ እናደርጋለን” ሲሉም ቃል ገብተዋል።በቴክኖሎጂ የተደገፉ፣ ንፁህ፣ ምቹ የሥራ አካባቢ የሚፈጠርበትን አቅጣጫ በመከተል፣ የመንግሥት ተቋማት ተቋማዊ አሰራርን ተከትለው ነፃና ገለልተኛ፣ ከሙስና የፃዳ አገልግሎት በመስጠት ተግባራዊ ውጤት የሚያስመዘግቡበት፣ ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት አሠራር የሚጎለብትበትን አካሄድ በመከተል የከተማዋን ትልቅነትና የነዋሪዎቿን ክብር የሚመጥን አገልግሎት ለመስጠት በቁርጠኝነት እንሚተካም ወ/ሮ አዳነች ገልፀዋል።

ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በከፍተኛ ድህነት ውስጥ የሚኖረውንና የኑሮ ውድነቱ ዋና ገፈት ቀማሽ የሆነውን የህብረተሰብ ክፍል ጊዜያዊ ችግሮቹን እየፈታን መላ ህዝቡን በዘላቂነት ከድህነት ለማውጣት የገባነውን ቃል ወደተግባር ለመቀየር በቁርጠኝነት እንተጋለን ሲሉም ነው የገለፁት።

ከዛሬ ሶስት ዓመት ገደማ ጀምሮ በህዝብ ግፊት እና በለውጥ ኃይሎች ሳቢነትና መሪነት፡ የዘመናት ትግልና የለውጥ መሻት እውን ወደመሆን እየተሸጋገረ መጥቷል ሲሉ ገልጸዋል። ዛሬ እያካሄድን ያለነው የመንግስት ምስረታ ጉባኤ፡ የለውጡ ፍሬ መገለጫ የሆኑ፣ የሀሳብ ብዘሃነት፣ ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች መከበር፣ የብዘሃ-ሚድያ ማበብ፣ አዳጊ የትርክት ለውጥ፣ የህዝብ ተሳትፎ መጎልበት፣ ፕሮጀክቶችን ጀምሮ የመጨረስ፣ የማድረግ አቅም መጎልበት፣ የወደቁ ማህበራዊ ዕሴቶች መንሰራራት፣ እውነተኛ የፌዴራል ሥርዓት እውን መሆን መገለጫ እንደሆነም ከንቲባዋ ተናግረዋል።

ከንቲባዋ ከተማችን የአሁኑንና የመጪውን ትውልድ ጥቅምና ፍላጎት የሚያስከብር አስተማማኝ መሠረት ላይ የተገነባ ዘላቂ ሰላም ተጠቃሚ የሚያደርግ፣ ዴሞክራሲ፣ ኅብረ-ብሔራዊ አንድነት፣ የዜጎች ክብር፣ ፍትሕ እና ብልጽግና የተረጋገጠባት ከተማ እንድትሆን ለማድረግ የምንቆጥበው ጊዜ፣ እውቀትና ሀብት የለም ብለዋል።የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ወቅታዊና ጥራት ያለው አገልግሎት በክብር የማግኘት መብት አላቸው ያሉት ከንቲባዋ የከተማዋን ኢኮኖሚያዊ የብልጽግና ጉዞ ለማሳካት፣ የህብረተሰቡን ሁለተናዊና አዳጊ ፍላጎቶችን በማጤን አሁናዊ የኢኮኖሚ ፍላጎት በሟሟላት ወደ ሌላ የፍላጎት ከፍታ ለማሸጋገር እና ወደ ተሻለ የኑሮ ደረጃ ለማድረስ በትጋት እንሰራለን ብለዋል። መነሻ ዜና ኢቢሲ

Leave a Reply