” ግሸን ደብረ ከርቤ ዓመታዊ ንግስ በዓል “

በየዓመቱ መስከረም 21 በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ የግሸን ደብረ ከርቤ (ግሽን ማርያም) ዓመታዊ የንግስ በዓል ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝበ ክርስቲያን በሚገኝበት ይከበራል።

የዘንድሮውም የንግስ በዓል በሠላም እንዲጠናቀቅ ፌዴራል ፖሊስ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን ገልጿል።

ፖሊስ የፀጥታው ሥራ አጠናክሮ እየሰራ በመሆኑ ከደብረ ብርሃን ጀምሮ እስከ ግሸን ማሪያም ድረስ ከፍተኛ የቅኝት (የፓትሮል ) ውጠራ ሥራ በመስራት ላይ ይገኛል።

በአሁኑ ወቅት በአካባቢው ላይ ምንም ዓይነት የፀጥታ ችግር አለመኖሩን ፌዴራል ፖሊስ ያሳወቀ ሲሆን በቀጠናው ላይ የሚገኙ ፦

– የአትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የሰሜን ፈጥኖ ደራሽ

– የአማራ ክልል ልዩ ኃይል

– የከተማው ፓሊስ ጋር በመቀናጀት ምንም አይነት የፀጥታ ችግር እንዳይፈጠር አካባቢውን በጥምረት እየጠበቁ እንደሆኑም አመልክቷል።

ህብረተሰቡ በአካባቢው ለፀጥታ ስጋት የሆኑ ተግባሮች ሲያጋጥሙት በፍጥነት አቅራቢያው ላሉ የፀጥታ አካላት ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል።

በሌላ በኩል ፥ የዘንድሮው የግሽን ደብረ ከርቤ ዓመታዊ በዓል ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅና እንግዶችን በወሎ የእንግዳ አቀባበል በማስተናገድ የተሳካ በዓል ማሳለፍ እንደሚገባ የደሴ ከንቲባ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከንቲባው አቶ አበበ ገብረ መስቀል ትላንት ለኤፍ ቢ ሲ በሰጡት ቃል ÷ ደሴ ከተማ በርካታ የበዓሉ ተጓዦች የሚያርፍባት በመሆኑ በተለይ የከተማው ነዋሪ እንግዶችን ሊንከባብ ይገባል ብለዋል።

በዓሉን ተከትሎ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ምንም አይነት የዋጋ ጭማሬ እንዳያደርጉ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

Ena

Leave a Reply