ኤርትራ “ትንኮሳ ሰልችቶኛል” ስትል አስጠነቀቀች

የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳልህ ትህነግ አገራቸው ወደ ጦርንርት እንድታመራ እየገፋፋ መሆኑንን አመልክተዋል። ሚኒስትሩ በጥቅሉ ” ትንኮሳ ስልችቶናል” የሚል መልዕክት ነው ያስተላለፉት። በተለይም አሜሪካና የአውሮፓ አገራት ትህነግ ዳግም ወደ ስልጣን ለመመልሰ የሚያደርጉትን ድጋፍ ኮንነዋል።

ከሶስት ዓመት በፊት ኢትዮጵያና ኤርትራ የደረሱበትን የሰላም ስምምነት ትህነግ ሊቀለብሰው እንደሚፈልግ በማስታወቅ በተቀረጸ ቪዲዮ ለተመድ 76 ጉባኤ ንግግር ያደረጉት ሚኒስትሩ “ትህነግ ኤርትራን በማጥቃት ለጦርነት እየገፋፋ ነው” ሲሉ ክስ አሰምተዋል። ማስጠንቀቂያ አቅርበዋል።

ትህነግ ለኤርትራ፣ ለኢትዮጵያና ለምስራቅ አፍሪቃ ስጋት የሆነ ድርጅት መሆኑንን ሚኒስትሩ አመልክተዋል። አያይዘውም እንዲህ ያለውን ድርጅት ከማውገዝ በተቃራኒ ሉዓላዊ አገርንና ሕዝብን ለመጠምዘዝ መሞከር ተቀባይነት እንደሌለው አመልክተዋል።

አሜሪካና የአውሮፓ ወዳጆቿ የትህነግን የከፋ አካሄድ ለመደገፍ የሚያደርጉትን ግልጽ ርብርብ ኮንነዋል። ኤርትራ በተደጋጋሚ አድልዎ በተሞላበት ማዕቀብ ስትጎዳ መቆየቷን ያወሱት ሳላህ፣ ይህ ከአሁን በሁዋላ ሊቀጥል እንደማይገባው አስታውቀዋል።

የበህዳሴ ግድብ አስመክቶ ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ የጋራ ጥቅም ን መሰረት ባደረገ በቀናነት ሊያከናውኑት የሚገባ መሆኑን አመልክተዋል። ዓለም አቀፍ ተቋማት በህዳሴ ግድብ ያላቸው ሚና አግባብነት የጎደለው መሆኑንም ጠቁመዋል።

ሚኒስትሩ የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ፈጽመውታል በሚል በሚከሰሱባቸው የሰብአዊ መብት ጥሰት ጉዳይ በንግግራቸው አላነሱም። ሚኒስትሩ ለተናገሩት ንግግር ከትግራይ ህዝብ ነሳ አውጪ ግንባር የተሰጠ ምላሽ ለጊዜው የለም። አቶ ጊታቸው ረዳ ግን የኢርትራን መንግስት የማስወገድ ሙሉ አቅም እንዳላቸውና ይህንንም ተግባራዊ እንደሚያደርጉት ማስታወቃቸው ይታወሳል።

ሰሞኑንን ይፋዊ ካልሆኑ መረጃዎች እንደሚሰማው ከሆነ ኤርትራ ሃይሏን በተጠንቀቅ እንዲቆም ማዘዟ ተሰምቷል። የኤርትራ ወታደሮች መሳሪያ ስለመተኮሳቸው በይፋ የተሰማ ነገር ባይኖርም በየትኛውም ሰዓት ከትህነግ በኩል ጥቃት ከተፈጸመ አጻፋ ለመውሰድ እንደሚገደዱ ተመልክቷል። ይህ ግን በይፋ ከኤርትራ መንግስት አልተገለጸም። በትህነግ በኩል ተመሳሳይ ትንኮሳና ወረራ በኤርትራ በኩል እንደሚፈጸም በተደጋጋሚ ሲገለጽ መቆየቱ ይታወሳል።

Leave a Reply