የመንግስት ምስረታው እና ከፊቱ የተቀመጡ ከበባድ የቤት ሥራዎች

የጁንታው ህውሃት ግፍና የውድ ወገኖቻችን የዕለት ተዕለት ሰቆቃ እያየን ፣ እየሰማን እንዱሁም እየሆነብን ሁሉንም በትዕግስት ችለን እዚህ ደርሰናል::

ከዚህ በኃላስ?


ስልጣንን ለእንጀራ መበያነት ብቻ ሳይሆን ሀገር ወገንን ለማገልገል ነው የሚለውን አስበልጣችሁ ወስዳችሁ ስማችሁን በደማቅ ቀለም ፃፉ::

ስኬታማ የመንግስት ምስረታ ዕለትና በተግባር ውጤት የሚደመደም የአመራር ዘመን እንዲሆን ተመኘሁ::
ነጻ አስተያየት – የምስራች አጥናፍ


“ድንጋዩ ደግሞ ዳቦ እናደርገዋለን” ይሉን የነበሩትን አብዛኛው ከወረዳ እስከ ከፍተኛው የስልጣን እርከን ድረስ ያሉ መሪዎቻችን ትክሻችን እየተንገዳገደም ቢሆን ተሸክመናቸው እዚህ ደርሰናል::

ብዙ አስፈሪ፣ ለመስማት የሚከብዱ ኩነቶችን አስተናግደናል። ኢትዮጵያዊያን ግን ዛሬም “ኢትዮጵያ ትቅደም” በማለት ለኢትዮጵያ ግንባራቸውንም ልባቸውንም በመስጠት እዚህ ደርሰናል:: በዚህ ሁሉ ውጣውረድና መስዋዕትነት ውስጥ “አሼሼ ገዳሜ” ባዮችም አልጠፉም።

ከነገ ሹም ሽር በኃላስ?

• የተራበውን:
• የተሰደደውን:
• የተፈናቀለውን:
• የዕለት ጉርስ ማግኘት ፈተና የሆነበት:
• ወደ ሥራ ለመሄድ እና ወደ ቤቱ ለመመለስ በሰልፍ ወገቡ የሚንቀጠቀጠውን ትራንስፖርት ጠባቂን:
• አንዲት 50 ግራም ዳቦ በሶስት ብር የሚሸምተውን ነዋሪ:

• ትምህርት ቤት ልጁን መላክ ያቃተው ወላጅ:
• ከዓመት እስከ ዓመት ብርድ ንፋስ ፀሀይ የሚፈራረቅበት ጎዳና ላይ የወደቀውን ወገንን: …
• ሆስፒታል መሄጃ አጥቶ በቀላሉ ሊድን በሚችል በሽታ ቤቱ ተኝቶ የሚሰቃየውን
• በውሃ መጥፋት ጀሪካውን ተሸክሞ ከሚንከራተት ዜጋ
• በመብራት መቆራረጥ የሚሰቃየውን ዞጋ:
• የመጠለያ እጦት ከግራ ቀኝ ከታች እላይ የሚሯሯጠው እና የሚሳቀቀው ወገንን:
• የተጀመሩ የመሰረተ ልማት ተግባራትን አጠናክሮ መቀጠል:
• በዲፕሎማሲው ዘርፍ አንጉታችንን እንድንደፋ የሆነበትን ሁኔታ አጢኖ ሥር ነቀል ለውጥ ማድርግ:
• የህዳሴ ግድቡን ለማጠናቀቅ ዜጎቭ በምንም ያክል የኑሮ ችግር ውስጥ ቢሆኑ እንኳን ከድህነት ለመውጣት ዋነኛ መንገዳችን የህዳሴ ግዱቡ ነውና ተጨማሪ የሀብት:የጉልበትና የቁሳቁስ ድጋፎችን በማስተባበር ግድቡ ተጠናቆ የኢትዮጵያዊያን ዕድገት ማረጋገጫ እንዲሆን ማድረግ:
• በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ የኢትዮጵያ ምርጥ ልጆችን የጁመሩትን ለሀገር ህልውና መሟገት ባሻገር ለሀገራቸው ህዝብ ልምዳቸውን ዕውቀታቸውን የሚያውሉበት መንገድ ማመቻቸት የቢሮክራሲ ውጣ ውረዱን ማስተካከል:
• በፍትህ ርትዕ እጦት እግዚኦ ሲል የሚውለውን ኢትዮጵያዊ የጠየቀው እና
የሚፈልገውን የሀገር ትከሻ እስከ ሚችለው ድረስ መመለስ እንችላለን… እንመራለን ብላችሁ ወንበሩ ላይ የወጣችሁ ሰዎች ከላይ የተዘረዘሩ ጥልቅ ችግሮችን ትኩረት ሰጥታችሁ የኢትዮጵያዊያንን የኑሮ ፍዳ ተመልክታችሁ ለመቅረፍ ቁርጠኛ መሆን አማራጭ የሌለው የመሪነት ዘመን ግዴታችሁ ነው::

ስልጣንን ለእንጀራ መበያነት ብቻ ሳይሆን ሀገር ወገንን ለማገልገል ነው የሚለውን አስበልጣችሁ ወስዳችሁ ስማችሁን በደማቅ ቀለም ፃፉ::

በዚህ ቁርጠኝነታችሁ ስርዓቱ ቢተፋችሁ እንኳን የኢትዮጵያ ህዝብ ውለታችሁን አንድ ሁለት ብሎ ቆጥሮ ይከፍላችኃል:; ይህንንም የቀድሞ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ( ነፍስ ይማር) እና አቶ መላኩ ፊንታን ተሞክሮ ተመልከቱ::

ስርዓቱ እኔን አላገለገላችሁኝም ብሎ አውጥቶ ሲጥላቸው ፣ ሲያስራቸው እውነታቸውና ፅናታቸው በመጨረሻው ሰዓት ዋጋቸውን ከፍሏቸዋል።

  • ወንበር ዘለአለማዊ አይደለም። ግፉ ቢል የእጅ ጣቶቻችንን ቁጥር እንኳን አይዘልቅም።
  • ንኢትዮጵያዊያን ክፉውን የመከራ ጊዜ እየገፉ ነው።
  • 2010 ዓ.ም. አዲስ ተስፋ የተወለደበት ዓመተ ምህረት ነበር።
  • ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ ወደ ስልጣን መጡ።
  • ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሞከራሉ ፣ ወይም ይሆናሉ ተብለው የማይጠበቁ ተግባራትን አከናወኑ።
  • ከፖትሪያርክ እስከ አሸባሪ እስከተባሉ ፖለቲከኞች የህሊና እስረኛች ጋር ሰላም ይቀድማል ኢትዮጵያ የሁሌችንም ናት በሚል ትልቅ ተግባር አከናወኑ።
  • በአንፃሩ ወደ ሥልጣን በመጡበት ሰዓት ብዙ ቃል የገቡልን እኛም ተስፋ ያደረግናቸው የትየለሌ የሆኑ ጉዳዮች ነበሩ::

⁃ ባለስልጣን አይደለንም :: እኛ ህዝብ አገልጋዮች ነን :
⁃ ቪ8 በመንዳት የሀገር ነዳጅ አናባክንም:
⁃ ስብሰባ እንቀንሳለን ብቻ ሳይሆን ከተገልጋዩ ሰዓት ውጪ እናደርጋለን:
⁃ ብክለትን እንከላከላለን:
⁃ ተጠያቂነትን እናሰፍናለን:
⁃ ግልፅነትን እናዳብራለን:
⁃ ታማኝነትን እናጠነክራለን.. የሚል ሲሰሙዋቸው ልብ የሚያሞቁ ተስፋዎች ሰጥተውን ነበር::

ይሁንና ይህን ሁሉ ለመቋደስ እና ለመመዘን የማንችልበት አጣብቂኝ ውስጥ በህውሃት እና በተላላኪው ሸኔ ምክንያት ገባን:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያሉትን ያህል ተግባራዊ ለማድረግ ቀላል የማይባል ተግዳሮት እንደገጠማቸው የአደባባይ ምስጢር ነው:: በተባለው ልክ አይደለም ሀገር እንደ ሀገር በበዛ ወከባ እና ምስቅልቅሎሽ ውስጥ ወደቀች::

ለህልውና እንኳን ፈታኝ ወደ ሆነው መስመር ውስጥ ተንደርድራ እንድትገባ በግራ ቀኝ: በፊት በኃላዋ ተዋከበች:: ከገባችበት አረንቋ ለመውጣት ልጆቿ ከህይወት መስዋዕትነት ጀምሮ ማንኛውንም መስዋዕትነት እየከፈሉ ይገኛሉ:: ይህ መስዋዕትነት ፍሬ እንዲያፈራ ኢትዮጵዬዊያን አብረው መቆማቸው ከባለፈው የመከራ ጊዜያቸ ውስጥ እጥፍ አብሮነት የበቅባቸዋል:: በዚህ ፈተና ውስጥም ብትሆን ኢትዮጵያችን ቀጥላለች :: ትቀጥላለችም::

ሰሞኑን የክልሎች መንግስት ምስረታ ተካሂዷል:: ከአማራ ክልል በስተቀር ሁሉም ርዕሰ መስተዳድሮቹ የነበሩት እንዲቀጥሉ አድርገዋል:: አዲስ አበባ ከተማ መስተዳድርም ምክትል ከንቲባ ሆነው ሲያስተዳድሯት የነበሩትን የምክር ቤቷ አባል በማድረግ ከንቲባዋ እንዲሆኑ ወ/ሮ አዳነች አበቤን ከንቲባዋ አድርጋ ሰይማለቸዋለች:: ነገ ደግሞ የፌደራል መንግስት ምስረታ ይካሄዳል:: ህዝብ ከነገው መንግስት ምስረታ ማግስት ጀምሮ ከገባበት የድህነት አረንቋ እንዲሁም የጦርነት ቅርቃር ውስጥ የሚያወጣውን ቁርጠኛ የሆነ አመራርን ይሻል::

ጦርነቱን በአፉጣኝ እንዲቋጭ እስካሁን የነበረውን የትብብር መንፈስ በማጉላት በተለይም መከላከያው ሁሉንም ግዳጅ በኃላፊነት በመምራት በአፋጣኝ የጦርነት የሰብአዊ ፍጡር ሞት: የቁስ ውድመት እና የስነ ልቦና ቀውስ በአጭር ጊዜ መቋጨት ለነገ የማይባል የሚመሰረተው መንግስት የቤት ሥራው ነው::

• የወደሙ መሰረተ ልማቶችን አቅም በሚፈቅደው ልክ እንዲገነባ: ተጎጂዎችን አለንልህ ማለትና መልሶ የማቋቋም የዘመቻ ተግባር የብልፅግና ፖርቲ አስፈፃሚውን በአቅምም በቁርጠኝነትም ሀገሩ ኢትዮጵያን የሚታደግ አመራርን መመደብ ብቻ ሳይሆን ተጠያቂነትን ሚስፈን ግድ ይለዋል::
ዜጎችን በማስተባበርና በማሰማራት ከአይቀሬው የምዕራባዊያን ዛቻና የድጋፍ ተአቅቦ ተፅዕኖ ሀገርን የመታደግ ኃላፊነት ከባድ ቢሆንም ለተግባራዊነቱ አቅምም ፈቃደኝነቱም ያላቸውን አመራሮች ወደሥልጣን ማምጣት ይጠበቅበታል::

ከውጪ እና ከውስጥ ያሉ ግፊቶችን ከዜጎች ጋር እንደ አንድ አፍ ተናጋሪ: እንደ አንድ ልብ ዘካሪ በመሆን : ልዩነቶችን በማጥበብ እስካሁን የነበረውን ሂደት አጠናክሮና እና በቁርጠኝነት ተጋፍጦ በሀገር ላይ የተንሰራፋውን የመከራን ጊዜ ማሳጠር ከመንግስት የሚጠበቅ ዋነኛው እና ቀዳሚው አጀንዳ መሆን ይኖርባታል::

ስኬታማ የመንግስት ምስረታ ዕለትና በተግባር ውጤት የሚደመደም የአመራር ዘመን እንዲሆን ተመኘሁ::
ነጻ አስተያየት – የምስራች አጥናፍ

Leave a Reply